Get Mystery Box with random crypto!

፩ ሃይማኖት

የቴሌግራም ቻናል አርማ and_haymanot — ፩ ሃይማኖት
የቴሌግራም ቻናል አርማ and_haymanot — ፩ ሃይማኖት
የሰርጥ አድራሻ: @and_haymanot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.62K
የሰርጥ መግለጫ

ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-08-08 10:22:51
ጾሙን የበረከት ያድርግልን

@And_Haymanot
2.5K views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 06:35:57 ​​ጾመ ፍልሰታ


ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገው ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት ኦርቶዶክሳዊያን የሚጾሙት ጾም ነው።

ፍልሰታ የግዕዝ ቃል ሆኖ ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል።
እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለሆነ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን 48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች።
ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት ወደ መኖሪያ ቤቷ (የዮሐንስ ቤት) መጥተው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች አስከሬኗን ገንዘውና ከፍነው ወስደው
ለመቅበር ወደ ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንም ማድረግ
የፈለጉት የሐዋርያት ትምህርት የጌታችን ከሞት መነሣትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ
እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። የፈሩት ይነግሣል የጠሉት ይወርሳል እንዲሉ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት
አይቀሬ ሆኗል።

አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፊኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ
ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነትና ክብር ለመመስከር በቅቷል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር ይቀመጥ እንጂ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር
ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ዮሐንስ ስለሥጋዋ ነግሯቸዋል።
ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ለስድስት ወራት ከአሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህ በኋላም ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው
ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን
አምጥቶ ስለሰጣቸው ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች።

ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት
አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ ፪፥፲/።
እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ /ሕንድ/ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ
ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በስተቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት
እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን /የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።
ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ
ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት
አስረዱት። እርሱ ግን ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን
ለማሳመን መቃብሯን ለማሳየት ወሰዱት ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት
የነበረውን ጨርቅ/ የራሱን ድርሻ አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው ዛሬም ካህናቱ ከእጅ መስቀላቸው ጋር መሐረብ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ
ነው። ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት
በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለሁለተኛ ጊዜ ለሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ
ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል።

በአጠቃላይ የእመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት መታየት፣ የሥጋዋና የነፍሷ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፍልሰት ሲባል ከዚህ የተነሣ የነሐሴ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ሐዋርያት ያገኙትን በረከት ለማግኘት ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በዶ/ር ሙሉጌታ ማርቆስ
@And\
Haymanot
@And_Haymanot_bot
6.1K views03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 12:34:53
3.1K views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 08:57:40 ፀሎት ለሞተ ሰው ለምን ይደረጋል የሚሉ ሰዎች ክርስቶስ የሞተውን
ሀጢአተኛው ለዛውም በሲኦል ውስጥ ያለውን አዳም ሀጢአቱን ፍቆ ነፃ
እንደአወጣው የረሱ ናቸው፤የኢየሱስ ምሕረቱም ከሞት በኃላም አይቋረጥም !
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
4.9K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 13:46:34 አንድ ጠያቂ እንዴት ወደ ድንግል ማርያም ልመና ይቀርባል ብሎአል:: በምድራዊ ኑሮ እርስ በእርሳችን በተለያየ ምክንያት እንዲህ አድርግልኝ ብለን ወንድሞቻችንን እኅቶቻችንን እንለምናለን:: ሀብት ሥልጣንና እውቀታቸው ከፍ ያለ ሰዎችን ደግሞ የበለጠ እንለምናለን:: ትብብራቸውን ምክራቸውን እንጠይቃለን:: በመንፈሳዊው ዓለም ደግሞ ወንድሜ በጸሎት አስበኝ አስቢኝ እንላለን:: ለእግዚአብሔር ቅርብ የሆኑት የበለጠ ልመና ይቀርብላቸዋል::

ዝናም እንዳይዘንም ብትፈልግ ለእኔ ዓይነቱ ደካማ ሰው "እስቲ ዝናም እንዳይዘንም ጸልይልኝ" ትለዋለህ:: ይጸልይልሃል:: ጸሎቴ አልሰምር ካለ አብሬህ እጠለላለሁ::

በእኔ ፋንታ ነቢዩ ኤልያስ ቢጸልይልህ ግን "የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች:: ኤልያስ እንደኛው ሰው ነበረ ዝናም እንዳይዘንም አጥብቆ ጸለየ በምድር ላይ አንድ ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም ሁለተኛም ጸለየ ሰማዩ ዝናብ ሰጠ" ያዕ. 5:16

አዎ ብዙ ልመና በመጽሐፍ ቅዱስ ለፍጡራን ቀርቦአል::

“አብርሃም አባት ሆይ ማረኝ" 16:24
"አሮንም እንዲህ አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ ቍጣህ አይቃጠል፤ ይህ ሕዝብ ክፋትን እንዲወድድ አንተ ታውቃለህ" ዘጸ. 32:22

ኦሪት ዘኍልቍ 12
11፤ አሮንም ሙሴን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ስንፍና አድርገናልና፥ በድለንማልና እባክህ፥ ኃጢአት አታድርግብን።

2ኛ ነገሥት 2
9፤ ከተሻገሩም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፦ ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን፡ አለው፤ ኤልሳዕም፦ መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ፡ አለ።

"እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፡ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን" ሐዋ.16:15
የምንለምነው ከፈጣሪ በተሠጣቸው ጸጋ እንዲፈውሱን እንዲጎበኙን እንዲጸልዩልን እንዲያማልዱን ነው::
ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
እንኳን አደረሳችሁ
7.3K viewsedited  10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 13:45:52
4.1K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 14:31:45 ለምን አንጾምም?

ተወዳጆች ሆይ የተሃድሶ መናፍቃን በዓለ ሃምሳን ለምን አትፆሙም ሲሉ ይደመጣሉ ከዛም አልፎ በዓቢይ ጾም የጾማችሁትን ለማካካስ ነው በማለት ይተቻሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንስ ምን ትላለች?

ጥያቄ:- በበዓለ ሃምሳ ለምን አንጾምም?
በፍትሐ ነገሥት ላይ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ አለ፦ "ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር" /ዐንቀጽ 15:566/።

"የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ" /ዐንቀጽ
15:603/። የዐቢይ ጾምን ፍቺ ተከትሎ ለ50 ቀናት የማንጾምበት ምክንያት
ብዙ ጥልቅ ምሥጢር ያለው ሥርዓተ ሃይማኖት ነው። በምሳሌ ለማስረዳትም ፦ ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ብለን የምናስበው ዘመነ ኦሪት እንደሆነ በማሰብ ነው።
በዚኸ ሳምንት ከሌሎች ድርጊቶች በተጨማሪ መስቀል አንሳለምም። ይኸ የሆነበት ምክንያት በዘመነ ኦሪት መስቀል በክርስቶስ መለኮታዊ ደም ተባርኮ አልተሰጠም'ና ነው። ልክ
እንደዚሁ ከትንሣኤ ዕለት ጀምሮ አስከ በዓለ ጰራቂሊጦስ (አስከ የሐዋርያት ጾም መግቢያ ድረስ) ያሉት 50 ቀናት እንደ አንድ ቀን ነው የሚታዩት። ይህም ማለት ሰው ከትንሣኤ በኃላ ፍጹም
ያለ ድካም እንደሚኖር ለማስተማር ጾም እና የንስሐ ቀኖና አይሰጡም።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
4.5K views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 08:02:21 ✟ክርስቶስ ተንስዓ ሙታን✟
✟አብይ ሀይል ወበስልጣን✟
✟አሰሮ ለሰይጣን✟
✟አግአዞ ለአዳም✟
✟ሰላም✟
✟እምይዜየሰ✟
✟ኮነ✟
✟ፍስሀ ወሰላም✟

"ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም"ሉቃ፦24፥5

"እንደተናገረ ተነስቷልና በዚህ የለም የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ" ማቴ፦28፥6

እንኳን አደረሰን መልካም በዓል ለሁላችንም!!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
4.9K views05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 11:26:38 ሰላምታ እና ሰሙነ ሕማማት

በሰሙነ ሕማማት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምና የትከሻ ሰላምታ መለዋወጠን አይፈጽሙም፡፡
@And_Haymanot
ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት፣ አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማክሰኞ መከሩ አልሠመረላቸውም፡፡ ምክራቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ አያንሾካሾኩ “ እንስቀለው … አንግደለው ” ብለው ይማከሩ ነበር፡፡ ያንን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ መስቀልም አንሳለምም፡፡ ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሰላምታ የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ ይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ “እኔ የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት” ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት
አይደለም፤ ተንኮል የተሞላበት እንጂ፡፡ የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሔዋንን “ ሰላም ለኪ” ብሎ ነው ያታለላት፣ የዲያቢሎስ እና የይሁዳ ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ
ሕማማት ሰላምታ ልውውጥ የለም፡፡ ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኸው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ሥርወ መሠረቱ ይህ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል ይቀጥላልም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
6.0K viewsedited  08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 21:20:08 ሆሳዕና
.
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ.
12÷12-15
.
የዘንባባ ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን
የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ
ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና
በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡
የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ
ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።
.
በዓሉን በዓለ ክብር ፣ በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ አ ሜ ን !!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
6.5K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ