Get Mystery Box with random crypto!

፩ ሃይማኖት

የቴሌግራም ቻናል አርማ and_haymanot — ፩ ሃይማኖት
የቴሌግራም ቻናል አርማ and_haymanot — ፩ ሃይማኖት
የሰርጥ አድራሻ: @and_haymanot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.62K
የሰርጥ መግለጫ

ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-12-16 09:45:12 ገድለ ተክለሃይማኖት እና ተዓምረ ማርያም ላይ ያሉ ጥያቄዎች በአባቶች በስፋት ሲመለስ የኖረ ነው እኛም መልሰን እንዳስሰዋለን ዝግጁ ናችሁ???? ጥያቄ ላለባቸው ሼር በማድረግ እና ወደቻናላችን እንድትጋብዙልን አንላለን
@And_Haymanot
505 views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 11:08:47 እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

@And_Haymanot

ይህን ትምህርት የምታነቡ ሁሉ በማስተዋል እና በጽሞና ትረዱ ዘንድ አሳስባችኋለሁ፡፡ ለዘመናት የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዘለዓለማዊ ድንግልና ለመቃወም ዲያቢሎስ ያዘመታቸው መናፍቃን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ሁሉ የማያዳግም መልስ በዝርዝር እና በአንድምታ ቀርቧል ፡፡ ከጌታ ውጭ ከቅዱስ ዮሴፍ ልጅወልዳለች ብለው ለተሰናከሉ ሁሉ በዚሁ አጋጣሚ ስለ ዮሴፍ ማንነት ጭምር ትምህርቱ በጥቂቱ ይዳስሳል መልካም ንባብ ፡-

‹‹‹ አረጋዊው ዮሴፍ ማነው ?

መናፍቃን ድንግል ማርያም ከጌታ ውጭ ከዮሴፍ እንደወለደች ሲናገሩ እንሰማለን ማስረጃ ባይኖረውም ፡፡ ነገር ግን የዮሴፍን ማንነት በጥቂቱም ቢሆን መረዳት ለስህተታቸው ማሰታገሻ መድኃኒት ነውና እነሆ ፡- አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ሀገሩ ናዝሬት ሲሆን ሐናፂም ነጋዴም ነበር ፡፡ ዘሩ ከዳዊት ወገን ነው ፡፡ ሦሰት ሴቶች እና አምሥት ወንዶች ልጆች ነበሩት ፡፡ ልጆቹ ገሚሶቹ ከ12ቱ ሐዋርያት ገሚሶቹ ደግሞ ከ72ቱ አርድዕት ውስጥ የነበሩ ሲሆን ከሚስቱ ጋር 52 ዓመት ፤ ሚስቱ ከሞተች በኋላ
ደግሞ 40 ዓመት ኖሯል ፡፡ በድምሩ 92 ዓመት ከኖረ በኋላ ለእመቤታች ጠባቂ ሆኖ ተመረጠ ፡፡ ከእመቤታችን እና ከጌታ ጋር ደግሞ በስደት ፣ በመከራ 22 ዓመታትን አሳልፏል ፡፡ ሊጠብቃትም ሲመረጥ ከ1,985 ሽማግሌዎች
ውስጥ ዕጣ ደርሶት ነው ፡፡ በፈቃደ እግዚአብሔርም የከተሰበሰቡት ሁሉ የርሱ በትር ለሦስት ጊዜ ያህ በተደጋጋሚ አብባና ለምልማ ተገኘች ፡፡ አረጋዊ ዮሴፍ በ114 ዓመቱ ሐምሌ 26 ቀን አርፏል ፡፡ ከማረፉ በፊት ግን ጌታችንን ‹‹ ሥጋዬን በዚህ ምድር አታስቀረው ›› ብሎ ለምኖት ነበርና ዛሬም ድረስ ዮሴፍ መቀበሩን እንጂ ቅዱስ ሥጋው የት እንዳለ የሚያውቅ የለም ጌታ ስለ ጸሎቱ (ስለልመናው) ሰውሮታልና ፡፡ ‹‹‹ አረጋዊው ዮሴፍ ለምን ተመረጠ ? *ይህ ጻድቅና ንጹሕ አረጋዊ ዮሴፍ ድንግል ማርያምን ሊጠብቅ ስለተመረጠበት ምክንያን አስረጋጭ

ማስረጃዎች እነሆ ፡፡

1ኛ) አገልጋይዋ ተላላኪዋ ሆኖ
ሊጠብቃት ፡፡

2ኛ) መከራዋን እንዲጋራ ፡፡ አንድም ዮሴፍ ዘመዷ ነው መከራን ለብቻ አይዘልቁምና በልጇ አማካኝነት የሚደርስባትን ስደት እና መከራ አብሯት እንዲካለፈል ነው ፡፡ ዝምድናቸው ሲዘረዘር የሚከተለውን ሃቅ ያስረዳናል ፡- + ግንዱ ‹‹ አልዓዛር ›› በሁለት
ወገን የሚከተሉትን ወልዷል ፡-
* ማታን = * ቅስራ*
* ያዕቆብ = * ኢያቄም *
* ዮሴፍ = * ድንግል ማርያም
(የነዚህ የዘር ሐረጋት ግንዱ ከላይ እንዳየነው * አልዓዛር * ነው ስለዚህ የዘር ሃረጋቸው አንድ ነውና ሊጠብቃት እንጂ ሊያገባት አይችልም)

3ኛ) ከመደብደብ ሊያድናት ፡፡ በኦሪ.ዘኁ 5፥19 በተጠቀሰው መሠረት አንዲት ሴት ከባልዋ ውጭ ጸንሳ ብትገኝ ማየ ዘለፋ ያጠጥዋት ነበር ፡፡ እንዲሁም አንዲት ሴት ባል ሳታገባ ብትጸንስ በሙሴ ሕግ መሠረት ደብድበው ይገድሉአት ነበር
፡፡ ስለዚህ እመቤታችን ለዮሴፍ ሳትታጭ ቀርታ ቢሆን ለድብደባ ባበቁአት ነበር ፡፡

4ኛ) ትንቢቱ እንዲፈጸም ነው ፡፡ ጌታ ከዳዊት ቤት እና ወገን እንዲወለድ ኢሳ 11፥1 ፣ 10 ላይ ትንቢት ነበር ፡፡ ዮሴፍም የዳዊት ዘር ነውና ክርስቶስ በዮሴፍ የዳዊት ልጅ ተብሎ እንዲቆጠር ነው ፡፡ ምነው በእናቱ የዳዊት ልጅ አይባልምን? ቢባል አይሁድ ሴትን ከትውልድ ቁጥር አግብተው አይቆጥሩምና ነው ፡፡

5ኛ) ኃይለ አርያማዊት (ከሰማይ ወረደች እንጂ ምድራዊት አይደለችም) የሚሉ ወገኖች ነበሩና ምድራዊት መሆኑኗን ለማጠየቅ ነው ፡፡ ሆኖም
ከምድር መገኘቷን ለመግለጽ እንጂ ድንግል ማርያም በክብሯ ሰማያዊት ናት ፡፡ የባሕርያችን መመኪያ መባሏም ከሰው ዘር መገኘቷን ልብ እንዲሉ ነው ፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያም ለዮሴፍ መታጨቷ ስለዚህ እና ይህን ለመሰለ ምክንያት ነው እንጂ ለሚስትነት አልነበረም ፡፡ አንድም ዮሴፍ እመቤታችን ሊጠብቃት በተመረጠ ጊዜ ጀርባው ጎብጦ ፣ ጉልበቱ ዝሎ ፣ ዓይኑ ሞጭሙጮ ነበር 92 ዓመት አልፎት
ነበር አረጋዊ(ሽማግሌ) መባሉም ለዚህ ነው ፡፡ በሆኑም አረጋዊ ዮሴፍ ስለነዚህ ምክንያት ድንግል ማርያም ሊጠብቃት ተመረጠ እንጂ ሊያገባት አይደለም፡፡ ሊያገባት የተመረጠ ቢሆን ኖሮ ድንግል ማርያም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሊያበሥራት ሲመጣ ‹‹ ወንድ ስለማላውቅ እንዴት ይሆናል ›› ባላለችውም ነበር ፡፡ ሊያበሥራት የተላከው ለዮሴፍ ከታጨች በኋላ ነውና ፡፡ በዚህም ንግግሯ ለዮሴፍ የታጨችው ሊጠብቃት እንጂ ሊያገባት እንዳልሆነ አረጋግጣለች፡፡ ዛሬ የተነሱ መናፍቀን ምሥጢር ይጎድላቸዋልና ዮሴፍን እንደወጣት ሰው ቆጥረው ድንግል ማርያምን ሊያገባ እንደታጨ በደካማ ጎናቸው ያስባሉ እውነቱ ግን ይሄ ነው ፡፡
ይቆየን ....
ወስብሀት ለእግዚአብሔር

፩ ሃይማኖት ተዋህዶ

✞_✞_✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
227 views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 11:07:28 "ቅድስት ድንግል ማርያምን መውደድ ከሚገባኝ መጠን በላይ አልፌ ወድጄያት ይሆን? ብለህ ሥጋት አይግባህ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከወደዳት በላይ ልትወዳት አትችልምና"
ቅዱስ ማክሲሚሊያን ኮልብ
@And_Haymanot
232 views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 18:38:30
ለዮናታን እና ለመሰሎቹ ከተሰጡ ድንቅ ምላሾች እነሆ

እንዲህ በጥበብ የተሞላ ምላሽ አላት ተዋህዶ

በስሙ ትርጉም እንኳን ወጥመድ ውስጥ ገባ
ልቦናን ይስጥልን

ሼር አርጉልን የመናፍቃንን ምላሽ በስፋት እንዳሰሳለን ተወዳጆች
@And_Haymanot
467 views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 15:13:18 ሰላም ተወዳጆች ዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው በተለያዩ አካላት ለሚጠይቁት መልሥ ነው
የኃልዮ ሀጢአት ምንድነው?
ካህኑ የኃጢአት ማሠርያ እግዚአብሔር ይፍታህ ካለ ለምን የንስሃ አባት አሥፈለገ?
እመቤታችን የአለም ቤዛ አትባልም ለሚሉ የተሠጠ መልሥ
   @And_Haymanot
191 views12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 19:25:12 ጽዮን በመፅሐፍ ቅዱስ ማን ናት??

...የቀጠለ
ልክ አንደ ሙሴ በሲና ተራራ አስርቱን ህግጋትን ከአምላክ ለአለም
መተዳዳሪያ እንዲሆን የአለም ተወካይ(የሰው ልጆች ተወካይ) ሆኖ እንደተቀበለው ፡፡
~~በዚህ ከተስማማን በትንቢተ ኢሳያስ
60 ፤14 የተፃፈው ቃል “””””የአስጨናቂዎችሽም ልጆች
አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ
ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።” የተባለው ከላይ ከተጠቀሱት አራት በጽዮን ስያሜ ከተጠሩት
በማያሻማ መልኩ ፤በትክክል ትንቢቱ የተነገረው፤ለቅድስት፤ድን ግል፥ማርያም፤እንደሆነ፤ማንም፤ህሊና፤
ለው፤ሰው፤መፍረድ ፤ይችላል፡፡ምክንያቱም፤ወደ እግርሽ፤ጫማ፤ተብሏልና፡፡

~~~ነገር ግን በዘመናችን የተነሱት መናፍቃን፤ለድንግል ማርያም፤ምንም ክብር ፤አይገባትም፤ብለው ስለሚያሰስተምሩ፤ይሄን ፤ትንቢት ከላይ
አንደጠቀስኩት ለዳዊት ከተማ ና ተራሮች ሰጥተው፤ይተረጉማሉ፤እዚህ ጋር ግን ሶስት ጥያቄ
አለኝ ~~~
1ኛ ከተማና ተራራ እግር ና ጫማ አላቸው???ካለቸው ይሄ
በአለማችን አዲስ ግኝት ነው ማለት ነው፡፡
2ኛ የዳዊት ከተማ ና ተራራዎቹዋ ሊሰገድላቸው ነው ማለት
ነው?????
3ኛ በእውነቱ የህወይት ምግብና መጠጥ የሆነውን ፤የጽድቅ
ፀሀይ የተባለውን ፤ኢየሱስ፤ክርስቶስን ከማህጸኗ እንካችሁ ብላ የሰጠችን እናት
ግዑዛን ከሆኑት ከዳዊት ከተማና ተራራዎች አንሳ ነው የክብር ስግደት የማይገባት?????? መልሱን ህሊና ላለው ሰው ብቻ ትቻለው…

~~~በመጨረሻም እግዚአብሔር አምላክ በዚህች ቅድስት
ንጽህት በሆነች ሐይማኖት እስከመጨረሻው፤ያጽናን፡፡የእመቤታችን የቅድሰት ድንግል ማርያም፤ረድኤትና
በረከት፤አማላጅነት፤አይለየን፡፡አሜን~~~ ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
               Join
     @And_Haymanot
              Join
     @And_Haymanot
              Join
     @And_Haymanot
    
    የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
732 viewsedited  16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 14:39:34 ጽዮን በመፅሐፍ ቅዱስ ማን ናት??

@And_Haymanot

የተሐድሶ መናፍቃን ከሚያነሱት መከራከሪያ አንዱ በትንቢተ ኢሳያስ 60 ፤14 የተፃፈው ቃል ነው “”””የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ የእግዚአብሔርም
ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።””””ይሄ ቃል
የተነገረው ለድንግል ማርያም አይደለም።እንደዛ ከሆነ አሉ፤እንደዛማ ከሆነ እናንተ ኦርቶዶክሶች ድንግል ማርያምን እየተሳደባችሁ አይደላችሁም ፤ምክንያቱም ፤ሌላ ስለ ጽዮንእንዲህ ተብሎ ተጽፏል እኮ በማለት እንዚህን ጥቅሶች ይጠቅሱልናል……

፩ኛ) ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 3 ከቁጥር 16 .ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ የጽዮን ቈነጃጅት
ኰርተዋልና፥ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፥ ፈንጠርም እያሉ፥ በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉና 17.ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት አናት በቡሀነት ይመታል፥
እግዚአብሔርም ኀፍረተ
ሥጋቸውን ይገልጣል።

፪ኛ)ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 52፤2
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያሽን አራግፊ ተነሺ፥ ተቀመጪ ምርኮኛይቱ
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።እነዚህንና የመሳሰሉትን በመጥቀስ
እናንተ ኦርቶዶክሶች ….ጽዮን የሚለውን ስያሜ ፤ዝም ብላችሁ ለማርያም ከሰጣችሁ፤እነዚህን ጥቅሶችስ አላነባባችሁም ማለት ነው ይሉናል።

፨በመጀመሪያ “””ጽዮን/ZION ”””” የሚለው ቃል የዕብራይስጥ
ሲሆን ትርጉዋሜውም፤”””አንባ፤መሸሸጊያ፤መጠጊያ””””፤ማለት ነው፡፡
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 11፤5፦ ዳዊት ግን አምባይቱን ጽዮንን ያዘ እርሷም የዳዊት ከተማ ናት።መረጃ---፩
ትንቢተ ኢሳይያስ 14፡32 ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መመለስ ይገባል? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደ መሠረተ፥ የሕዝቡም ችግረኞች
በእርስዋ ውስጥ እንደሚጠጉ ነው።
መረጃ --፪ ~ሲቀጥል በመጽሀፍ ቅዱስ ጽዮን የሚለው ቃል ለ አራት፡(4)ነገሮች ነው የተነገረው……..

1ኛ ለዳዊት ከተማ እና በውስጧ ያሉትን ተራራዎቹዋንም ጭምር
2ኛ ለሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም.
3ኛለህዝበ/ቤተ እስራኤል.
4ኛ ለእናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ነው……

~~~ማስረጃ፦፦፦
1ኛ ለዳዊት ከተማ ና ተራራዎቹዋ ከ 76 ጊዜ በላይ..ጽዮን በሚለው ስያሜ በመጽሀፍ ቅዱስ ተጠርተዋል.
፩ኛ. መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 5:2፦ ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ
አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች የአባቶቻቸውን ቤቶች መሳፍንት፥ ንጉሡ ሰሎሞን ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም
ሰበሰባቸው።…
፪ኛ .መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 11፤5 ዳዊት ግን አምባይቱን ጽዮንን ያዘ እርሷም የዳዊት ከተማ ናት
፫ኛ .መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 19፤31 ከኢየሩሳሌም ቅሬታ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይወጣሉና የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።……..እና ለመሳሰሉት….ተጨማሪውን አንብቡ

~~~ማስረጃ ፦፦፦2ተኛው ለሰማያዊቷ ኢሩሳሌም (ለ 7ተኛዋ ሰማይ) 14 ጊዜ ጽዮን በሚለው ስያሜ በመጽሀፍ ቅዱስ ተጠርታለች፡፡
፩ኛ .ወደ ዕብራውያን 12፤22 ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት
መላእክት፥
፪ኛ.የዮሐንስ ራእይ 14፤1 አየሁም፥ እነሆም፥ በጉ በጽዮን ተራራ
ቆሞ ነበር፥ ከእርሱም ጋር
ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ። መዝሙረዳዊት 50፤2 ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር
ግልጥ ሆኖ ይመጣል።………እና
ለመሳሰሉት….ተጨማሪውን አንብቡ

~~~ማስረጃ 3ተኛው ለህዝበ/ለቤተ እስራኤል(ለእስራኤል ልጆች)፤ጽዮናውያን/ ZIONIST ተብለው ይጠራሉ፤ ከ 46 ጊዜ በላይ በመጽሀፍ ቅዱስ ጽዮን በሚለው ስያሜ
ተጠርተዋል.
፩ኛ. ትንቢተ ኢሳይያስ 52፤2 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያሽን አራግፊ፡ተነሺ፥ ተቀመጪ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።፤8 እነሆ፥ ጕበኞችሽ ጮኸዋል እግዚአብሔር
ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ በአንድነትም ይዘምራሉ።
፪ኛ.ትንቢተ ኢሳይያስ 3፤16 -17 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ የጽዮን ቈነጃጅት ኰርተዋልና፥ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፥ ፈንጠርም እያሉ፥
በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉና
ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት አናት በቡሀነት ይመታል፥ እግዚአብሔርም ኀፍረተ ሥጋቸውን ይገልጣል።
፫ኛ.ትንቢተ ኢሳይያስ 4፤3-4 ጌታም የጽዮንን ቈነጃጅት እድፍ ባጠበ ጊዜ፥ የኢየሩሳሌምንም ደም በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስ ከመካከልዋ ባነጻ
ጊዜ፥ በጽዮን የቀረ በኢየሩሳሌምም የተረፈ፥ በኢየሩሳሌም ለሕይወት የተጻፈ ሁሉ፥ ቅዱስ ይባላል።
፬ኛ. ትንቢተ ሚክያስ 4፤10-13
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ በዚያም
ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።
11፥ አሁንም። ርኩስ ትሁን፥ ዓይናችንም በጽዮን ላይ ይይ የሚሉ
ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።
13፤ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ
አደርጋለሁና ተነሺ ሂጂ ብዙ
አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ።………………እና ለመሳሰሉት….ተጨማሪውን አንብቡ……..

~~~ማስረጃ ……4ተኛው ጽዮን የሚለው ስያሜ በመጽሃፍ ቅዱስ የተሰጠው ስሟ ከማር ከወተት ይልቅ ጥዑም የሆነ ፤ክብሯ፤ከፈጣሪ በታች ነገር ግን ከፍጡራን ሁሉ በላይ የሆነ፤
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ፤ጽዮን በሚለው ስያሜ ተጠርታለች ፤ መረጃ ከማቅረቤ በፊት ለምን ቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን በሚለው ስያሜ ነብያቱ ትንቢት ተናገሩላት ካልን ፤ካላይ
ለመግለረጽ እንደሞከርኩት “””ጽዮን”””” የሚለው ቃል ፤ቃሉ፤የዕብራይስጥ ሲሆን
ትርጉዋሜውም፤”””አንባ፤መሸሸጊያ””””፤ማለት ነው፡፡ ስለሆነም እናታችን ለህዝብ ልጆች ሁሉ በዘመኑ ፍፃሜ(በሀዲስ
ኪዳን) ከልጅዋ ምህረትን ፈልገው ሲመጡ አንባ፡ ጥላ፤ መሸሸጊያ ፤መጠጊያ፤እንደምትሆን፤አ ስቀድመው ነቢያት መንፈስ ቅዱስ ስለገለጸላቸው፤እናታችንን፤ ጽዮን በሚለው ስያሜ ጠርተዋታል፡፡

~~ማስረጃ~~፩ኛ.መዝሙረ ዳዊት 53፡6 መድኃኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን በሰጠ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት
ያደርጋል። ይሄ ትንቢት ሲሆን ተርጉሞ የነገረን ግን ቅዱስ ጳውሎስ ነው
እንዲህ በማለት ሮሜ 11፡26 መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል።ስለዚህ መዳኒት የተባለው ንጉስ ክርስቶስ
ሲሆን ጽዮን ተብላ የተጠራችሁ ደግሞ እናታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ናት፡፡
፪ኛ.መዝሙረ ዳዊት 87፡2 ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።ይሄ ትንቢት ደግሞ ቀራንዮ ላይ ተፈጽሟል ፡፡
የዮሐንስ ወንጌል 19፤27 ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።ቅዱስ ዮሐንስ አለምን ወክሎ አስቀድሞ ነብዩ ዳዊት፤
በትንቢቱ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል ብሎ የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ድንግል ማርያምን የአለም ተወካይ(የሰው ልጆች ተወካይ) ሆኖ ለአለሙ እናት እንድትሆን እናት አድርጎ ተቀበለ ።
ይቀጥላል...
997 viewsedited  11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 16:39:02
የብሉይ ኪዳን ታቦት የለንም።
@And_Haymanot
47 views13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 13:58:10 በሀገረ አሜሪካ ለወርቃማው ገዳም ቦታ መግዣ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት በፌስቡክ በቲክቶክ በዩትዩብ ። 1,000,000 ዶላር ሳንሞላ አንወጣም.
GoFundMe : https://gofund.me/donkeytubeforeotc
Bank of America Account Number : 325176793117
Transfer with Zelle using : donkeytube@saintjtbm.org

Share
148 viewsedited  10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ