Get Mystery Box with random crypto!

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት? @And_Haymanot ይህን ትምህርት የምታነቡ ሁሉ በማስተዋ | ፩ ሃይማኖት

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

@And_Haymanot

ይህን ትምህርት የምታነቡ ሁሉ በማስተዋል እና በጽሞና ትረዱ ዘንድ አሳስባችኋለሁ፡፡ ለዘመናት የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዘለዓለማዊ ድንግልና ለመቃወም ዲያቢሎስ ያዘመታቸው መናፍቃን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ሁሉ የማያዳግም መልስ በዝርዝር እና በአንድምታ ቀርቧል ፡፡ ከጌታ ውጭ ከቅዱስ ዮሴፍ ልጅወልዳለች ብለው ለተሰናከሉ ሁሉ በዚሁ አጋጣሚ ስለ ዮሴፍ ማንነት ጭምር ትምህርቱ በጥቂቱ ይዳስሳል መልካም ንባብ ፡-

‹‹‹ አረጋዊው ዮሴፍ ማነው ?

መናፍቃን ድንግል ማርያም ከጌታ ውጭ ከዮሴፍ እንደወለደች ሲናገሩ እንሰማለን ማስረጃ ባይኖረውም ፡፡ ነገር ግን የዮሴፍን ማንነት በጥቂቱም ቢሆን መረዳት ለስህተታቸው ማሰታገሻ መድኃኒት ነውና እነሆ ፡- አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ሀገሩ ናዝሬት ሲሆን ሐናፂም ነጋዴም ነበር ፡፡ ዘሩ ከዳዊት ወገን ነው ፡፡ ሦሰት ሴቶች እና አምሥት ወንዶች ልጆች ነበሩት ፡፡ ልጆቹ ገሚሶቹ ከ12ቱ ሐዋርያት ገሚሶቹ ደግሞ ከ72ቱ አርድዕት ውስጥ የነበሩ ሲሆን ከሚስቱ ጋር 52 ዓመት ፤ ሚስቱ ከሞተች በኋላ
ደግሞ 40 ዓመት ኖሯል ፡፡ በድምሩ 92 ዓመት ከኖረ በኋላ ለእመቤታች ጠባቂ ሆኖ ተመረጠ ፡፡ ከእመቤታችን እና ከጌታ ጋር ደግሞ በስደት ፣ በመከራ 22 ዓመታትን አሳልፏል ፡፡ ሊጠብቃትም ሲመረጥ ከ1,985 ሽማግሌዎች
ውስጥ ዕጣ ደርሶት ነው ፡፡ በፈቃደ እግዚአብሔርም የከተሰበሰቡት ሁሉ የርሱ በትር ለሦስት ጊዜ ያህ በተደጋጋሚ አብባና ለምልማ ተገኘች ፡፡ አረጋዊ ዮሴፍ በ114 ዓመቱ ሐምሌ 26 ቀን አርፏል ፡፡ ከማረፉ በፊት ግን ጌታችንን ‹‹ ሥጋዬን በዚህ ምድር አታስቀረው ›› ብሎ ለምኖት ነበርና ዛሬም ድረስ ዮሴፍ መቀበሩን እንጂ ቅዱስ ሥጋው የት እንዳለ የሚያውቅ የለም ጌታ ስለ ጸሎቱ (ስለልመናው) ሰውሮታልና ፡፡ ‹‹‹ አረጋዊው ዮሴፍ ለምን ተመረጠ ? *ይህ ጻድቅና ንጹሕ አረጋዊ ዮሴፍ ድንግል ማርያምን ሊጠብቅ ስለተመረጠበት ምክንያን አስረጋጭ

ማስረጃዎች እነሆ ፡፡

1ኛ) አገልጋይዋ ተላላኪዋ ሆኖ
ሊጠብቃት ፡፡

2ኛ) መከራዋን እንዲጋራ ፡፡ አንድም ዮሴፍ ዘመዷ ነው መከራን ለብቻ አይዘልቁምና በልጇ አማካኝነት የሚደርስባትን ስደት እና መከራ አብሯት እንዲካለፈል ነው ፡፡ ዝምድናቸው ሲዘረዘር የሚከተለውን ሃቅ ያስረዳናል ፡- + ግንዱ ‹‹ አልዓዛር ›› በሁለት
ወገን የሚከተሉትን ወልዷል ፡-
* ማታን = * ቅስራ*
* ያዕቆብ = * ኢያቄም *
* ዮሴፍ = * ድንግል ማርያም
(የነዚህ የዘር ሐረጋት ግንዱ ከላይ እንዳየነው * አልዓዛር * ነው ስለዚህ የዘር ሃረጋቸው አንድ ነውና ሊጠብቃት እንጂ ሊያገባት አይችልም)

3ኛ) ከመደብደብ ሊያድናት ፡፡ በኦሪ.ዘኁ 5፥19 በተጠቀሰው መሠረት አንዲት ሴት ከባልዋ ውጭ ጸንሳ ብትገኝ ማየ ዘለፋ ያጠጥዋት ነበር ፡፡ እንዲሁም አንዲት ሴት ባል ሳታገባ ብትጸንስ በሙሴ ሕግ መሠረት ደብድበው ይገድሉአት ነበር
፡፡ ስለዚህ እመቤታችን ለዮሴፍ ሳትታጭ ቀርታ ቢሆን ለድብደባ ባበቁአት ነበር ፡፡

4ኛ) ትንቢቱ እንዲፈጸም ነው ፡፡ ጌታ ከዳዊት ቤት እና ወገን እንዲወለድ ኢሳ 11፥1 ፣ 10 ላይ ትንቢት ነበር ፡፡ ዮሴፍም የዳዊት ዘር ነውና ክርስቶስ በዮሴፍ የዳዊት ልጅ ተብሎ እንዲቆጠር ነው ፡፡ ምነው በእናቱ የዳዊት ልጅ አይባልምን? ቢባል አይሁድ ሴትን ከትውልድ ቁጥር አግብተው አይቆጥሩምና ነው ፡፡

5ኛ) ኃይለ አርያማዊት (ከሰማይ ወረደች እንጂ ምድራዊት አይደለችም) የሚሉ ወገኖች ነበሩና ምድራዊት መሆኑኗን ለማጠየቅ ነው ፡፡ ሆኖም
ከምድር መገኘቷን ለመግለጽ እንጂ ድንግል ማርያም በክብሯ ሰማያዊት ናት ፡፡ የባሕርያችን መመኪያ መባሏም ከሰው ዘር መገኘቷን ልብ እንዲሉ ነው ፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያም ለዮሴፍ መታጨቷ ስለዚህ እና ይህን ለመሰለ ምክንያት ነው እንጂ ለሚስትነት አልነበረም ፡፡ አንድም ዮሴፍ እመቤታችን ሊጠብቃት በተመረጠ ጊዜ ጀርባው ጎብጦ ፣ ጉልበቱ ዝሎ ፣ ዓይኑ ሞጭሙጮ ነበር 92 ዓመት አልፎት
ነበር አረጋዊ(ሽማግሌ) መባሉም ለዚህ ነው ፡፡ በሆኑም አረጋዊ ዮሴፍ ስለነዚህ ምክንያት ድንግል ማርያም ሊጠብቃት ተመረጠ እንጂ ሊያገባት አይደለም፡፡ ሊያገባት የተመረጠ ቢሆን ኖሮ ድንግል ማርያም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሊያበሥራት ሲመጣ ‹‹ ወንድ ስለማላውቅ እንዴት ይሆናል ›› ባላለችውም ነበር ፡፡ ሊያበሥራት የተላከው ለዮሴፍ ከታጨች በኋላ ነውና ፡፡ በዚህም ንግግሯ ለዮሴፍ የታጨችው ሊጠብቃት እንጂ ሊያገባት እንዳልሆነ አረጋግጣለች፡፡ ዛሬ የተነሱ መናፍቀን ምሥጢር ይጎድላቸዋልና ዮሴፍን እንደወጣት ሰው ቆጥረው ድንግል ማርያምን ሊያገባ እንደታጨ በደካማ ጎናቸው ያስባሉ እውነቱ ግን ይሄ ነው ፡፡
ይቆየን ....
ወስብሀት ለእግዚአብሔር

፩ ሃይማኖት ተዋህዶ

✞_✞_✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot