Get Mystery Box with random crypto!

ጽዮን በመፅሐፍ ቅዱስ ማን ናት?? @And_Haymanot የተሐድሶ መናፍቃን ከሚያነሱት መከራከሪ | ፩ ሃይማኖት

ጽዮን በመፅሐፍ ቅዱስ ማን ናት??

@And_Haymanot

የተሐድሶ መናፍቃን ከሚያነሱት መከራከሪያ አንዱ በትንቢተ ኢሳያስ 60 ፤14 የተፃፈው ቃል ነው “”””የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ የእግዚአብሔርም
ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።””””ይሄ ቃል
የተነገረው ለድንግል ማርያም አይደለም።እንደዛ ከሆነ አሉ፤እንደዛማ ከሆነ እናንተ ኦርቶዶክሶች ድንግል ማርያምን እየተሳደባችሁ አይደላችሁም ፤ምክንያቱም ፤ሌላ ስለ ጽዮንእንዲህ ተብሎ ተጽፏል እኮ በማለት እንዚህን ጥቅሶች ይጠቅሱልናል……

፩ኛ) ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 3 ከቁጥር 16 .ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ የጽዮን ቈነጃጅት
ኰርተዋልና፥ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፥ ፈንጠርም እያሉ፥ በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉና 17.ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት አናት በቡሀነት ይመታል፥
እግዚአብሔርም ኀፍረተ
ሥጋቸውን ይገልጣል።

፪ኛ)ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 52፤2
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያሽን አራግፊ ተነሺ፥ ተቀመጪ ምርኮኛይቱ
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።እነዚህንና የመሳሰሉትን በመጥቀስ
እናንተ ኦርቶዶክሶች ….ጽዮን የሚለውን ስያሜ ፤ዝም ብላችሁ ለማርያም ከሰጣችሁ፤እነዚህን ጥቅሶችስ አላነባባችሁም ማለት ነው ይሉናል።

፨በመጀመሪያ “””ጽዮን/ZION ”””” የሚለው ቃል የዕብራይስጥ
ሲሆን ትርጉዋሜውም፤”””አንባ፤መሸሸጊያ፤መጠጊያ””””፤ማለት ነው፡፡
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 11፤5፦ ዳዊት ግን አምባይቱን ጽዮንን ያዘ እርሷም የዳዊት ከተማ ናት።መረጃ---፩
ትንቢተ ኢሳይያስ 14፡32 ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መመለስ ይገባል? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደ መሠረተ፥ የሕዝቡም ችግረኞች
በእርስዋ ውስጥ እንደሚጠጉ ነው።
መረጃ --፪ ~ሲቀጥል በመጽሀፍ ቅዱስ ጽዮን የሚለው ቃል ለ አራት፡(4)ነገሮች ነው የተነገረው……..

1ኛ ለዳዊት ከተማ እና በውስጧ ያሉትን ተራራዎቹዋንም ጭምር
2ኛ ለሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም.
3ኛለህዝበ/ቤተ እስራኤል.
4ኛ ለእናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ነው……

~~~ማስረጃ፦፦፦
1ኛ ለዳዊት ከተማ ና ተራራዎቹዋ ከ 76 ጊዜ በላይ..ጽዮን በሚለው ስያሜ በመጽሀፍ ቅዱስ ተጠርተዋል.
፩ኛ. መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 5:2፦ ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ
አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች የአባቶቻቸውን ቤቶች መሳፍንት፥ ንጉሡ ሰሎሞን ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም
ሰበሰባቸው።…
፪ኛ .መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 11፤5 ዳዊት ግን አምባይቱን ጽዮንን ያዘ እርሷም የዳዊት ከተማ ናት
፫ኛ .መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 19፤31 ከኢየሩሳሌም ቅሬታ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይወጣሉና የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።……..እና ለመሳሰሉት….ተጨማሪውን አንብቡ

~~~ማስረጃ ፦፦፦2ተኛው ለሰማያዊቷ ኢሩሳሌም (ለ 7ተኛዋ ሰማይ) 14 ጊዜ ጽዮን በሚለው ስያሜ በመጽሀፍ ቅዱስ ተጠርታለች፡፡
፩ኛ .ወደ ዕብራውያን 12፤22 ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት
መላእክት፥
፪ኛ.የዮሐንስ ራእይ 14፤1 አየሁም፥ እነሆም፥ በጉ በጽዮን ተራራ
ቆሞ ነበር፥ ከእርሱም ጋር
ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ። መዝሙረዳዊት 50፤2 ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር
ግልጥ ሆኖ ይመጣል።………እና
ለመሳሰሉት….ተጨማሪውን አንብቡ

~~~ማስረጃ 3ተኛው ለህዝበ/ለቤተ እስራኤል(ለእስራኤል ልጆች)፤ጽዮናውያን/ ZIONIST ተብለው ይጠራሉ፤ ከ 46 ጊዜ በላይ በመጽሀፍ ቅዱስ ጽዮን በሚለው ስያሜ
ተጠርተዋል.
፩ኛ. ትንቢተ ኢሳይያስ 52፤2 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያሽን አራግፊ፡ተነሺ፥ ተቀመጪ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።፤8 እነሆ፥ ጕበኞችሽ ጮኸዋል እግዚአብሔር
ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ በአንድነትም ይዘምራሉ።
፪ኛ.ትንቢተ ኢሳይያስ 3፤16 -17 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ የጽዮን ቈነጃጅት ኰርተዋልና፥ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፥ ፈንጠርም እያሉ፥
በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉና
ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት አናት በቡሀነት ይመታል፥ እግዚአብሔርም ኀፍረተ ሥጋቸውን ይገልጣል።
፫ኛ.ትንቢተ ኢሳይያስ 4፤3-4 ጌታም የጽዮንን ቈነጃጅት እድፍ ባጠበ ጊዜ፥ የኢየሩሳሌምንም ደም በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስ ከመካከልዋ ባነጻ
ጊዜ፥ በጽዮን የቀረ በኢየሩሳሌምም የተረፈ፥ በኢየሩሳሌም ለሕይወት የተጻፈ ሁሉ፥ ቅዱስ ይባላል።
፬ኛ. ትንቢተ ሚክያስ 4፤10-13
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ በዚያም
ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።
11፥ አሁንም። ርኩስ ትሁን፥ ዓይናችንም በጽዮን ላይ ይይ የሚሉ
ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።
13፤ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ
አደርጋለሁና ተነሺ ሂጂ ብዙ
አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ።………………እና ለመሳሰሉት….ተጨማሪውን አንብቡ……..

~~~ማስረጃ ……4ተኛው ጽዮን የሚለው ስያሜ በመጽሃፍ ቅዱስ የተሰጠው ስሟ ከማር ከወተት ይልቅ ጥዑም የሆነ ፤ክብሯ፤ከፈጣሪ በታች ነገር ግን ከፍጡራን ሁሉ በላይ የሆነ፤
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ፤ጽዮን በሚለው ስያሜ ተጠርታለች ፤ መረጃ ከማቅረቤ በፊት ለምን ቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን በሚለው ስያሜ ነብያቱ ትንቢት ተናገሩላት ካልን ፤ካላይ
ለመግለረጽ እንደሞከርኩት “””ጽዮን”””” የሚለው ቃል ፤ቃሉ፤የዕብራይስጥ ሲሆን
ትርጉዋሜውም፤”””አንባ፤መሸሸጊያ””””፤ማለት ነው፡፡ ስለሆነም እናታችን ለህዝብ ልጆች ሁሉ በዘመኑ ፍፃሜ(በሀዲስ
ኪዳን) ከልጅዋ ምህረትን ፈልገው ሲመጡ አንባ፡ ጥላ፤ መሸሸጊያ ፤መጠጊያ፤እንደምትሆን፤አ ስቀድመው ነቢያት መንፈስ ቅዱስ ስለገለጸላቸው፤እናታችንን፤ ጽዮን በሚለው ስያሜ ጠርተዋታል፡፡

~~ማስረጃ~~፩ኛ.መዝሙረ ዳዊት 53፡6 መድኃኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን በሰጠ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት
ያደርጋል። ይሄ ትንቢት ሲሆን ተርጉሞ የነገረን ግን ቅዱስ ጳውሎስ ነው
እንዲህ በማለት ሮሜ 11፡26 መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል።ስለዚህ መዳኒት የተባለው ንጉስ ክርስቶስ
ሲሆን ጽዮን ተብላ የተጠራችሁ ደግሞ እናታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ናት፡፡
፪ኛ.መዝሙረ ዳዊት 87፡2 ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።ይሄ ትንቢት ደግሞ ቀራንዮ ላይ ተፈጽሟል ፡፡
የዮሐንስ ወንጌል 19፤27 ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።ቅዱስ ዮሐንስ አለምን ወክሎ አስቀድሞ ነብዩ ዳዊት፤
በትንቢቱ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል ብሎ የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ድንግል ማርያምን የአለም ተወካይ(የሰው ልጆች ተወካይ) ሆኖ ለአለሙ እናት እንድትሆን እናት አድርጎ ተቀበለ ።
ይቀጥላል...