Get Mystery Box with random crypto!

፩ ሃይማኖት

የቴሌግራም ቻናል አርማ and_haymanot — ፩ ሃይማኖት
የቴሌግራም ቻናል አርማ and_haymanot — ፩ ሃይማኖት
የሰርጥ አድራሻ: @and_haymanot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.62K
የሰርጥ መግለጫ

ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-04-08 12:46:16
ለመስቀሉ እሮጣለው
@And_Haymanot
5.4K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 18:09:38
ሁላችሁም አንብቧት ተወዳጆች

@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
6.2K views15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 12:33:36 ለፍጹም ትህትና ማርያም ምሳሌ ናት
5.8K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 12:36:42 እኛ እያንዳንዱ የተቆለፈ በር ሺህ መክፈቻ ቁልፎች አሉት ብለን እንናገራለን ። እግዚአብሔር ግን ሁሉንም የተዘጉ ደጃፎች ወይም መዝጊያዎች መክፈት ይችላል ። ሁሉም ጨለማ በብርሃን ይተካል እያንዳንዱ ጥያቄም መፍትሄ ወይም መፍትሔዎች ይኖሩታል ። እግዚአብሔር እያንዳንዱን መከራ መቆጣጠር ይቻለዋል ከመራራው ጣፋጭን ከበላተኛውም የሚበላ ማውጣት የሚቻለው እግዚአብሔር ለችግሮቻችን በሙሉ መፍትሔ አለው ።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
7.5K views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 07:29:21
በረከታቸው አትለየን
"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ። በረከታቸው አትለየን።" (ማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ
ግንኙነት)
@And_Haymanot
8.1K views04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 07:53:55 የቤተ ክርስቲያኑን ታሪክ የማያውቅ ሰው፣ ቢያንስ ሦስት ዋና ዋና ነገሮችን ያጣል።

አንደኛ፦
. የቤተ ክርስቲያን ጉዞ ውጣ ውረድ የበዛበት እና ሻካራ መሆኑን ካለፉት አበው ሕይወት እና ተጋድሎ ካለመማሩ የተነሣ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እና ውጭ ፈተና ሲያይ "እንዴት እንዲ ይኾናል? ፤ እንዴት እንዲያ ይደረጋል? ካህናት ወይም ጳጳሳት እንዲህ ያደርጋሉ እንዴ?፤..." እያለ፣ በርሱ ዘመን ብቻ እንደዚህ እንደሆነ እየመሰለው ይደናገጣል፤ መያዣው እና መጨበጫው ይጠፋዋል።

. በዚህም የሚያምኑት እግዚአብሔርን ሳይሆን ሰውን የነበረ ይመስል፣ ሰው እና እግዚአብሔርን መለየት አቅቷቸው፣ ከእውነተኛ ሃይማኖት የሚጠፉ አሳዛኝ ወገኖች ይኖሩ ይሆናል።

ኹለተኛ፦
. ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ካሉት አካላት ጋር፣ የሚኖረውን ግንኙነት እና አጠቃላይ ሁኔታ፣ እንዴት መምራት እና ምን ማድረግ እንዳለበት በቂ የታሪክ ተሞክሮ የሌለው ይሆንና፣ ሁሉንም ነገር ከራስ ሙከራ እና ምናልባትም ከራስ ስህተት መማር ብቻ ይሆንበታል።

. ዛሬ በተለያየ ስም እና መልክ በዓለም ላይ ካሉ የክርስትና አካላት ጋር እና ከሌሎችም ጋር ሊኖር የሚገባው ግንኙነት፣ ካለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ከነበረው ሰፊ እና ውስብስብ ታሪክ፣ ትምህርት የወሰደ እና ያን ግምት ውስጥ ያስገባ ካልሆነ፣ ስህተት መድገም እና መደጋገም ይሆናል።

ሦስተኛም፦
. የቅዱሳን አባቶቻችን ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ እና ከተጋድሎአቸው የሚገኘው ሕያው ትምህርት የሌለው ይሆናል፤

. ከሐዋርያት ጀምሮ የነበሩ ቅዱሳን አባቶችን አስተምህሮ እና ዜና ሕይወት ማወቅ በአ ስተሳሰባችን እና በድርጊታችን ሁሉ፣ በትውፊታዊው የቤተክርስቲያን መስመር ላይ እንድንጓዝ ያደርገናል።

ይህን ካለወቅን ግን፣
ምናልባት ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ፣ ስሜታችን እንዳመለከተን የማድረግ ግዴታ ላይ እንወድቅ ይሆናል።


[ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ፣ ሕይወቱ እና ትምህርቱ ፤ በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ፤ ገጽ፦ ፮/6 ፤ ፳፻፲፬/2014 ዓ.ም. ፪ኛ ዕትም]
@And_Haymanot
7.0K views04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 12:45:19 በፈተና ጊዜ፥ ደካማው ሰው "እንደዚህ የደረሰብኝ'ኮ" እያለ የሚያመካኝበት ሌላ ሰውን ይፈልጋል፤ ብርቱው ሰው ግን በፈተናው ይጸና ዘንድ እግዚአብሔርን ይፈልጋል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@And_Haymanot
7.3K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 21:18:31 የምስራች

በሆሳዕና ከተማ ጥምቀት ይከበራል
እንኳን ደስ አላችሁ ተወዳጆች
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
9.1K views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 17:22:40 + መስቀል አደባባይና ቤተ ክርስቲያን +
ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
Share

3. ግንቦት ልደታ


በመስቀል አደባባይ ሊከናወን የሚገባውና ከይዘቱ አንጻር ተገቢ የሆነው ሌላው የአደባባይ በዓል የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሆነው የግንቦት ልደታ በዓል ነው፡፡ ግንቦት ልደታ በቤተ ክርስቲያንዋ ከቤት ውጪ በምሽት በድምቀት
ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ነው፡፡ ይህንን በዓል በውጪ እንዲከበር ያደረገው ድንግል ማርያም የተወለደችው በቤት ውስጥ ሳይሆን በተራራ ላይ የነበረ መሆኑን ለማስታወስ ነው፡፡ ይህንን በማስመልከት ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናን
ከቤታቸው ውጪ ሆነው በዓሉን ያከብራሉ፡፡
ከዓመታት በፊት በግንቦት ልደታ በዓል ታሪክ ዙሪያ አነስተኛ ጥናታዊ ጽሑፍ በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ትእዛዝ በሠራሁና ባቀረብሁበት ወቅት ለመገንዘብ እንደቻልሁት ግንቦት ልደታ በኢትዮጵያውያን
ዘንድ እንደየ ብሔር ብሔረሰቡ የተለያየ ቅርፅ ያለው ቢሆንም ትልቅ ቦታ ሊሠጠው የሚችልና ለቱሪስት መስሕብ ለመሆን የሚችል እምቅ እሴት የያዘ ሀገራዊ ቅርስ ነው፡፡ ይህ እጅግ ድንቅ የሆነ በዓል በመስቀል አደባባይ የመከበሩን ተገቢነት ድንግል ማርያምን ከመስቀል ጋር በሚያስተሳስሩ ጸሎቶችዋና ዜማዎችዋ የምትታወቀው የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚደግፈው ነው፡፡ በብዙ ሀገራት በብሔራዊ በዓል ደረጃ የሚከበረው ይህ በዓል በቤተ ክርስቲያን ደረጃም ቢሆን በሚመጥነው ክብር ቢከበር በቤተ ክርስቲያኒቱ ተልእኮና በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚፈጥረው በጎ ተጽዕኖ ቀላል አይደለም፡፡

4. የጥምቀተ ባሕር ሜዳዎች

ቤተ ክርስቲያናችን ጥምቀተ ባሕር ላይ ሰፋፊ ሥራዎችን ለመሥራት ዕቅድ እንደያዘችና ሥራ እንደ ጀመረች ብፁዕ አቡነ ያሬድ ይፋ ያደረጉት የጃን ሜዳ ፕሮጀክትና ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በመግለጫቸው የዳሰሱአቸው ርእሰ ጉዳዮች ምስክሮች ናቸው:: ቤተ ክርስቲያናችን እነዚህን ቅዳሴ የሚደረግባቸው ክቡራት ሥፍራዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ፓርኮች ሆነው መገንባት: የሕፃናት ማጫወቻዎችና ስፖርት ማዘውተሪያዎች : ከሱስ ማገገሚያ ማእከላት ሊሆኑም ይችላሉ::
በተጨማሪም በዓላት በደረሱ ቁጥር ልዩ ልዩ ባዛሮችና መንፈሳዊ ዐውደ ርእዮች ከጉባኤያት ጋር ቢካሔዱባቸው በዓልን በስካርና ጭፈራ ከማክበር ብዙኃንን ማዳን ይቻላል:: የግንቦት ልደታ በዓልም ከመስቀል አደባባይ በተጨማሪ
በጥምቀተ ባሕር የሚካሔድ መሆን ሲችል ደብረ ታቦርና የእመቤታችን ትንሣኤ (አሸንዳም) እንዲሁ ጥምቀተ ባሕር ላይ መከበር ይችላል:: እጃችን ላይ ያሉ በጎ ዕድሎችን በአግባቡ ከተጠቀምን እጃችን ላይ የሌሉትንም እንጨምራለን:: "ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት
ትመጣለች" ዮሐ. 9:4 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 4 2014 ዓ.ም.
"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም
ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share
ያድርጉ :-
የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/
UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
@And_Haymanot
9.9K views14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ