Get Mystery Box with random crypto!

የቤተ ክርስቲያኑን ታሪክ የማያውቅ ሰው፣ ቢያንስ ሦስት ዋና ዋና ነገሮችን ያጣል። አንደኛ፦ . | ፩ ሃይማኖት

የቤተ ክርስቲያኑን ታሪክ የማያውቅ ሰው፣ ቢያንስ ሦስት ዋና ዋና ነገሮችን ያጣል።

አንደኛ፦
. የቤተ ክርስቲያን ጉዞ ውጣ ውረድ የበዛበት እና ሻካራ መሆኑን ካለፉት አበው ሕይወት እና ተጋድሎ ካለመማሩ የተነሣ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እና ውጭ ፈተና ሲያይ "እንዴት እንዲ ይኾናል? ፤ እንዴት እንዲያ ይደረጋል? ካህናት ወይም ጳጳሳት እንዲህ ያደርጋሉ እንዴ?፤..." እያለ፣ በርሱ ዘመን ብቻ እንደዚህ እንደሆነ እየመሰለው ይደናገጣል፤ መያዣው እና መጨበጫው ይጠፋዋል።

. በዚህም የሚያምኑት እግዚአብሔርን ሳይሆን ሰውን የነበረ ይመስል፣ ሰው እና እግዚአብሔርን መለየት አቅቷቸው፣ ከእውነተኛ ሃይማኖት የሚጠፉ አሳዛኝ ወገኖች ይኖሩ ይሆናል።

ኹለተኛ፦
. ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ካሉት አካላት ጋር፣ የሚኖረውን ግንኙነት እና አጠቃላይ ሁኔታ፣ እንዴት መምራት እና ምን ማድረግ እንዳለበት በቂ የታሪክ ተሞክሮ የሌለው ይሆንና፣ ሁሉንም ነገር ከራስ ሙከራ እና ምናልባትም ከራስ ስህተት መማር ብቻ ይሆንበታል።

. ዛሬ በተለያየ ስም እና መልክ በዓለም ላይ ካሉ የክርስትና አካላት ጋር እና ከሌሎችም ጋር ሊኖር የሚገባው ግንኙነት፣ ካለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ከነበረው ሰፊ እና ውስብስብ ታሪክ፣ ትምህርት የወሰደ እና ያን ግምት ውስጥ ያስገባ ካልሆነ፣ ስህተት መድገም እና መደጋገም ይሆናል።

ሦስተኛም፦
. የቅዱሳን አባቶቻችን ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ እና ከተጋድሎአቸው የሚገኘው ሕያው ትምህርት የሌለው ይሆናል፤

. ከሐዋርያት ጀምሮ የነበሩ ቅዱሳን አባቶችን አስተምህሮ እና ዜና ሕይወት ማወቅ በአ ስተሳሰባችን እና በድርጊታችን ሁሉ፣ በትውፊታዊው የቤተክርስቲያን መስመር ላይ እንድንጓዝ ያደርገናል።

ይህን ካለወቅን ግን፣
ምናልባት ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ፣ ስሜታችን እንዳመለከተን የማድረግ ግዴታ ላይ እንወድቅ ይሆናል።


[ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ፣ ሕይወቱ እና ትምህርቱ ፤ በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ፤ ገጽ፦ ፮/6 ፤ ፳፻፲፬/2014 ዓ.ም. ፪ኛ ዕትም]
@And_Haymanot