Get Mystery Box with random crypto!

+ መስቀል አደባባይና ቤተ ክርስቲያን + ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ Share 3. | ፩ ሃይማኖት

+ መስቀል አደባባይና ቤተ ክርስቲያን +
ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
Share

3. ግንቦት ልደታ


በመስቀል አደባባይ ሊከናወን የሚገባውና ከይዘቱ አንጻር ተገቢ የሆነው ሌላው የአደባባይ በዓል የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሆነው የግንቦት ልደታ በዓል ነው፡፡ ግንቦት ልደታ በቤተ ክርስቲያንዋ ከቤት ውጪ በምሽት በድምቀት
ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ነው፡፡ ይህንን በዓል በውጪ እንዲከበር ያደረገው ድንግል ማርያም የተወለደችው በቤት ውስጥ ሳይሆን በተራራ ላይ የነበረ መሆኑን ለማስታወስ ነው፡፡ ይህንን በማስመልከት ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናን
ከቤታቸው ውጪ ሆነው በዓሉን ያከብራሉ፡፡
ከዓመታት በፊት በግንቦት ልደታ በዓል ታሪክ ዙሪያ አነስተኛ ጥናታዊ ጽሑፍ በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ትእዛዝ በሠራሁና ባቀረብሁበት ወቅት ለመገንዘብ እንደቻልሁት ግንቦት ልደታ በኢትዮጵያውያን
ዘንድ እንደየ ብሔር ብሔረሰቡ የተለያየ ቅርፅ ያለው ቢሆንም ትልቅ ቦታ ሊሠጠው የሚችልና ለቱሪስት መስሕብ ለመሆን የሚችል እምቅ እሴት የያዘ ሀገራዊ ቅርስ ነው፡፡ ይህ እጅግ ድንቅ የሆነ በዓል በመስቀል አደባባይ የመከበሩን ተገቢነት ድንግል ማርያምን ከመስቀል ጋር በሚያስተሳስሩ ጸሎቶችዋና ዜማዎችዋ የምትታወቀው የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚደግፈው ነው፡፡ በብዙ ሀገራት በብሔራዊ በዓል ደረጃ የሚከበረው ይህ በዓል በቤተ ክርስቲያን ደረጃም ቢሆን በሚመጥነው ክብር ቢከበር በቤተ ክርስቲያኒቱ ተልእኮና በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚፈጥረው በጎ ተጽዕኖ ቀላል አይደለም፡፡

4. የጥምቀተ ባሕር ሜዳዎች

ቤተ ክርስቲያናችን ጥምቀተ ባሕር ላይ ሰፋፊ ሥራዎችን ለመሥራት ዕቅድ እንደያዘችና ሥራ እንደ ጀመረች ብፁዕ አቡነ ያሬድ ይፋ ያደረጉት የጃን ሜዳ ፕሮጀክትና ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በመግለጫቸው የዳሰሱአቸው ርእሰ ጉዳዮች ምስክሮች ናቸው:: ቤተ ክርስቲያናችን እነዚህን ቅዳሴ የሚደረግባቸው ክቡራት ሥፍራዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ፓርኮች ሆነው መገንባት: የሕፃናት ማጫወቻዎችና ስፖርት ማዘውተሪያዎች : ከሱስ ማገገሚያ ማእከላት ሊሆኑም ይችላሉ::
በተጨማሪም በዓላት በደረሱ ቁጥር ልዩ ልዩ ባዛሮችና መንፈሳዊ ዐውደ ርእዮች ከጉባኤያት ጋር ቢካሔዱባቸው በዓልን በስካርና ጭፈራ ከማክበር ብዙኃንን ማዳን ይቻላል:: የግንቦት ልደታ በዓልም ከመስቀል አደባባይ በተጨማሪ
በጥምቀተ ባሕር የሚካሔድ መሆን ሲችል ደብረ ታቦርና የእመቤታችን ትንሣኤ (አሸንዳም) እንዲሁ ጥምቀተ ባሕር ላይ መከበር ይችላል:: እጃችን ላይ ያሉ በጎ ዕድሎችን በአግባቡ ከተጠቀምን እጃችን ላይ የሌሉትንም እንጨምራለን:: "ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት
ትመጣለች" ዮሐ. 9:4 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 4 2014 ዓ.ም.
"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም
ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share
ያድርጉ :-
የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/
UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
@And_Haymanot