Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ጠያቂ እንዴት ወደ ድንግል ማርያም ልመና ይቀርባል ብሎአል:: በምድራዊ ኑሮ እርስ በእርሳች | ፩ ሃይማኖት

አንድ ጠያቂ እንዴት ወደ ድንግል ማርያም ልመና ይቀርባል ብሎአል:: በምድራዊ ኑሮ እርስ በእርሳችን በተለያየ ምክንያት እንዲህ አድርግልኝ ብለን ወንድሞቻችንን እኅቶቻችንን እንለምናለን:: ሀብት ሥልጣንና እውቀታቸው ከፍ ያለ ሰዎችን ደግሞ የበለጠ እንለምናለን:: ትብብራቸውን ምክራቸውን እንጠይቃለን:: በመንፈሳዊው ዓለም ደግሞ ወንድሜ በጸሎት አስበኝ አስቢኝ እንላለን:: ለእግዚአብሔር ቅርብ የሆኑት የበለጠ ልመና ይቀርብላቸዋል::

ዝናም እንዳይዘንም ብትፈልግ ለእኔ ዓይነቱ ደካማ ሰው "እስቲ ዝናም እንዳይዘንም ጸልይልኝ" ትለዋለህ:: ይጸልይልሃል:: ጸሎቴ አልሰምር ካለ አብሬህ እጠለላለሁ::

በእኔ ፋንታ ነቢዩ ኤልያስ ቢጸልይልህ ግን "የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች:: ኤልያስ እንደኛው ሰው ነበረ ዝናም እንዳይዘንም አጥብቆ ጸለየ በምድር ላይ አንድ ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም ሁለተኛም ጸለየ ሰማዩ ዝናብ ሰጠ" ያዕ. 5:16

አዎ ብዙ ልመና በመጽሐፍ ቅዱስ ለፍጡራን ቀርቦአል::

“አብርሃም አባት ሆይ ማረኝ" 16:24
"አሮንም እንዲህ አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ ቍጣህ አይቃጠል፤ ይህ ሕዝብ ክፋትን እንዲወድድ አንተ ታውቃለህ" ዘጸ. 32:22

ኦሪት ዘኍልቍ 12
11፤ አሮንም ሙሴን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ስንፍና አድርገናልና፥ በድለንማልና እባክህ፥ ኃጢአት አታድርግብን።

2ኛ ነገሥት 2
9፤ ከተሻገሩም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፦ ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን፡ አለው፤ ኤልሳዕም፦ መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ፡ አለ።

"እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፡ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን" ሐዋ.16:15
የምንለምነው ከፈጣሪ በተሠጣቸው ጸጋ እንዲፈውሱን እንዲጎበኙን እንዲጸልዩልን እንዲያማልዱን ነው::
ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
እንኳን አደረሳችሁ