Get Mystery Box with random crypto!

​​ሃያል ነህ አንተ ሃያል ነህ አንተ ሃያል ደጉ መልአክ ገብርኤል /2/ ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት አ | ፩ ሃይማኖት

​​ሃያል ነህ አንተ

ሃያል ነህ አንተ ሃያል
ደጉ መልአክ ገብርኤል /2/
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት
አንተ ተራዳን በእውነት /2/
በዱራ ሜዳ ላይ........ገብርኤል
ጣዎት ተዘጋጅቶ.......ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ.......ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወጥቶ.......ገብርኤል
ሲድራቅና ሚሳቅ አብናጎም ፀኑ
ጣዎቱን እረግጠው በእግዚአብሔር አመኑ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ተቆጣ ንጉሡ.......ገብርኤል
በሶስቱ ሕፃናት .......ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ.......ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት.......ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ደረሰ መልአኩ
ከሞት አዳናቸው እሳት ሳይነኩ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
እቶኑ ስር ሆነው........ገብርኤል
ዝማሬ ተሞሉ........ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው.......ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ.......ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር
አዩ መኳንንቱ የእግዚአብሔር ክብር
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ናቡከደነጾር........ገብርኤል
እጁን በአፋ ጫነ.......ገብርኤል
ሠለስቱ ደቂቅን........ገብርኤል
ከእሳት ስላዳነ.......ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከው መልአኩን
ሊያመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን.
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንኳን አደረሳችሁ