Get Mystery Box with random crypto!

ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፩ @And_Haymanot ጥያቄ ፩ ገድለ ተክለ ሃይማኖ | ፩ ሃይማኖት

ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፩

@And_Haymanot
ጥያቄ ፩
ገድለ ተክለ ሃይማኖትላይ ‘ሰይጣንን አጠመቁት’ ይላል እያሉ የተሐድሶ መናፍቃን ይተቻሉ፡፡ እውን ግን ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በቁሙ ሰይጣንን አጥምቀዋልን?

መልስ፡- በቀድሞ መጻሕፍት ሥጋ ለበስ የሆኑ አጋንንት ታሪክ የታወቀ ነው፡፡ እነዚህ ሥጋ ለበስ አጋንንት የአጋንንትን ሥራ የሚሠሩ ቢሆኑም
የሚዳሰስ ሥጋ ግን አላቸው፡፡ ለምሳሌ ድርሳነ ሚካኤል ዘጥር ላይ እንደ ተገለጠው እነዚህ በሽታዎችን ሁሉ የሚያመጡ ሥጋ ለበስ አጋንንት
እንደ ሰው ሁሉ ይታመማሉ፤ ይራባሉ፤ ይሞታሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በበረሐ ውስጥ አንዳንድ ጊዜም በውኃ ውስጥ ይኖራሉ፡፡

+ በገድለ ተክለ ሃይማኖትና በልደተ አበው ላይ እንዲህ ይላል “አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእነዚህ አውራጃዎች ሲመላለስ አንድ ቀን በውኃ ዳር ዐረፍ አለ፡፡ ጋኔንም ከውኃው ወጣና ደቀ መዛሙሩን ያዘው፡፡ አሳመመውም፡፡ እርሱም ጋኔን መሆኑን ዐወቀ፡፡ በረድኡ ላይም በመስቀል ምልክት አማተበበት፡፡ ጋኔኑም ፈጥኖ ወጣ ሸሸ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በእጁ ያዘው፡፡ ሥራዩንም አወጣበት፡፡ ያን ጊዜም ለሁሉ ታየ፡፡ እርሱም “ማነው ስምህ?” አለው፡፡ ጋኔኑም “ባሕር አልቀም” አለው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም “ከኔ ጋር ትኖራለህን?” አለው፡፡ እርሱም ገዘረውና ወደ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ጥምቀት አገባው፡፡ ስሙንም ክርስቶስ ኀረዮ(ክርስቶስ መረጠው ማለት ነው) አለው፡፡ ረድእም አደረገው፡፡ ወደ በኣቱም አስገባው፡፡ እርሷም አስቦ ናት፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚወድና ወንድሞቹንም ሁሉ የሚያስደስት ሆነ፡፡” (ገድለ ተክለ ሃይማኖት፤ነሐሴ 1989 ዓ.ም፤ ምዕራፍ ፶፩፤ ገጽ. 177-178፤ Getachew Haile, Geneaology, P.11&12)

+ በጥንታውያን ሰዎች ዘንድ በአጋንንት አሠራር ተጠምደው የሚኖሩ ጣዖት አምላኪ ሰዎችን ባደሩባቸው አጋንንት ስም መጥራት የተለመደ ነው፡፡ ሰው በውስጡ ባለው ነገር ይጠራልና፡፡ ልክ ጌታ ጴጥሮስን “አንተ ሰይጣን ከኋላየ ሒድ” (ማቴ.16፡23) እንዳለው ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ታሪኮች በብዙ ጥንታውያን መጻሕፍት አሉ፡፡ ሥጋ ለበስ አጋንንት የሚሏቸው እነርሱን ነው፡፡ የተለያዩ የምትሐት ነገሮችን ይሠራሉ፡፡ በባሕር ይኖራሉ፣ በእሳት ውስጥም ገብተው በደኅና ይወጣሉ፡፡ ዋሊስ ባጅ ባሰተመው የደብረ ሊባኖስ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ላይ ጸሐፊው ከሌሎቹ የአካባቢው ቅጅዎች ለየት ብሎ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያጠመቁት ክፉ መንፈስ ያለበትን ሰው እንጂ መንፈስ የሆነውን ሰይጣን አለመሆኑን በቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎች ያብራራል፡፡ (E.A.W. Budge, The Life and Miracles of Takla Hay-manot, (London,1906), P. 80).
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot