Get Mystery Box with random crypto!

ተአምረ ማርያም ላይ መናፍቃን ጥያቄዎች አንዱ ☞ ጥያቄ. ነፍሳትን በበላው በበላኤ ሰብ ታሪክ ላይ | ፩ ሃይማኖት

ተአምረ ማርያም ላይ መናፍቃን ጥያቄዎች አንዱ

☞ ጥያቄ. ነፍሳትን በበላው በበላኤ ሰብ ታሪክ ላይ።
☞ መልስ፦ የብላዔ ሰብዕ 78 ነፍስ አጥፍቶ መማሩ በማቴ10:42
"በደቀ መዝሙር ስም ቀዝቃዛ ዉሃ ቢጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም" በሚለው አምላካዊ ቃል መሰረት ነው::
ተአምረ ማርያም እንደሚነግረን ስምዖን የተባለው ይህ ሰው ብዙ ነፍስ ካጠፋ በሗላ ንስሓ ገባ ተጸጸተ ልክ በቀኝ እንደተሰቀለው ወንበዴ::
በወንጌሉ መሰረት ለድሀ ከደቀመዛሙርት ሁሉ ከፍጥረት
ሁሉ በከበረችው በእመቤታችን ስም ቀዝቃዛ ዉሀ ለድሀ አጠጣ:: እመቤታችም በወንጌሉ መሰረት ማርለኝ አለችው ማረላት:: በቀኝ የተሰቀለ ከብላዔ ሰብዕ (ከዚህ ሰብ በላ) የበለጠ ይሥራ አይሥራ እኛ አናዉቅም::
ቃል ኪዳን ሲሰጥ ክርስቶስ ገደብ አላስቀመጠም (ይህንን ያህል
የገደለ አልምርም የሚል የለ)::
በደቀ መዝሙር ስም ያጠጣ አለ እንጂ:: ስለዚህ የወንበዴውን መዳንም እየተጠራጠሩ በወንጌል አምናለሁ ማለት አይቻልም:: በወንጌል ተጽፎ ነው እንጂ በቀኝ የተሰቀለው ታሪክ በተአምረ
ማርያም ቢጻፍ ኖሮ አይቀበሉትም ነበር::
በመጨረሻም መናፍቃን ከተለያዩ ገድላት፣ድርሳናት፣ተአምራት በመጥቀስ ምዕመንን ለማሰናከል ይኳትናሉና።
በተቻለ መጠን አይታለሉላቸው። ምንም እንኳን ገድሉ ተአምሩ ለማመን ከባድ ቢሆንም ክርስቲያኖች ነንና ከዚህም በላይ እንደሚደረግ እንወቅ!
ጌታ ያለውም ይህንኑ ነው።በእኔ የሚያምን ከዚህ በላይ ያደርጋል
ተብሎ ተፅፋልና!!!..... ሌሎች ጥያቄዎችን እንመለስበታለን  ይቆየን
@And_Haymanot
@And_Haymanot