Get Mystery Box with random crypto!

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት? ክፍል ሶስት @And_Haymanot ተወዳጆች በዚህ ር | ፩ ሃይማኖት

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

ክፍል ሶስት

@And_Haymanot

ተወዳጆች በዚህ ርዕስ ተከታታይ ምላሽ በመዳሰስ ላይ ነን በመሆኑም ሌሎችን ልንገፋበት ወይም ልንተች ያቀረብነው ሳይሆን የጠፋችሁ እህት ወንድሞቼ በማስተዋል እንድትጓዙ ብሎም እንድትነቁም ጭምር ነው፡፡
የማርያም ልጅ ይርዳን

@And_Haymanot

‹‹‹ የ-እስከ-ትርጉም ›››

ሥጋውያኑ ‹‹ እስከን ›› ተገን አድርገው ‹‹ እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ›› የሚለውን ቃል ፍጻሜ ላለው ነገር በማስገባት ደግመው ደጋግመው ተሰናክለውበታል፡፡ ትርጉሙ(ፍቺው) ግን ይህ አይደለም ፡፡

ለምሳሌ ፡-
1ኛ) የሣኦል ልጅ ሜልኮል ‹‹እስከሞተችበት ›› ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም 2ኛ ሳሙ6፥23 ፡፡ ይህም ማለት እስከመጨረሻው ልጅ አልወለደችም ማለት እንጂ ከሞተች በኋላ ወለደች ለማለት አለመሆኑ የታወቀ ነው ፡፡
2ኛ) ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰማ ‹‹ እስከሞቱ›› ድረስ ይህ በደል በእውነት አየሰረይላቸውም ኢሳ 22፥14 ታዲያ የዚህ ትርጉም ከሞቱ በኋላ ይሰረይላቸዋል ማለት ነውን? እስከዘለዓለም አይሰረይላቸውም ለማለት እንጂ፡፡
3ኛ) ከአዳም ጀምሮ ‹‹ እስከሙሴ ›› ድረስ ሞት ነገሠ ሮሜ 5፥14 ታድያ ከሙሴ በኋላ ሞት ቀረ ማለት ነውን?
4ኛ) እግዚአብሐየር ጌታዬን ጠላቶችህ ለእግርህ መረገጫ ‹‹ እስካደርግልህ ›› ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው መዝ101፥1 ታዲያ ጌታችን ጠላቶቹን (አይሁደን) በሥልጣኑ ከረታ በኋላ በአብ ቀኝ መቀመጡ ቀረ ማለት ነው?
5ኛ) እነሆም እኔ ‹‹ እስከ ዓለም ፍጻሜ ›› ድረስ ከእናተ ጋር ነኝ ማቴ28፥20 ከዓለም ፍጻሜ በኋላ ከእናንተ ጋር አይደለሀም ማለት ነውን ?
6ኛ) ቁራውንም ሰደደው እርሱም ወጣ ውሃውም ከምድር ‹‹ እስከሚደርቅ ›› ድረስ ወዲያና ወዲህ ይል ነበር ዘፍ 8፥7 ሲል ውሃው ከደረቀ በኋላ ወዲያና ወዲህ ማለቱን ተወ ማለት ነውን? እንግዲህ ከላይ በተዘረዘረው የእስከ ትርጉም መሠረት በማቴ1፥25 የተጠቀሰው ፍጻሜ የሌለው ‹‹ እስከ ›› መሆኑን ያስረዳል ስለዚህ ዮሴፍ እመቤታችንን እስከ ፍጻሜው ድረስ በግብር አላወቃትም ነበር ማለትነው፡፡ ከዚህ ውጭ በራሱ ፍቃድ የሚረተጉም ሁሉ የረተገመ ይሁን!!!

‹‹‹ የወንድሞች ትርጉም ›››

አዲስ ኪዳን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጌታችንን ‹‹ ወንድሞቹ ›› እንደሆኑ ከሐዋርያት ወገን የሚጠቅሳቸው አሉ ፡፡ ይህን በመያዝ ብዙ ጥራዝ ነጠቅ አንባቢያን (መናፍቃን) ጌታ ወንድሞች እንዳሉት እና ድንግል ማርያም ከጌታ ውጭ ልጅ እንዳላት በማውራት አነስተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀታቸውን ለማንጸባረቅ ይሞክራሉ ፡፡ ነገር ግን ማንም የራሱን ግላዊ ሃሳብ ከማንጸባረቁ በፊት የመጽሐፍ ቅዱስን የአጻጻፍ ዘይቤ መረዳት ያስፈልገዋል እንላለን ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ
1ኛ) በምን ቋንቋ እንደተጻፈ ፣
2ኛ) በማን ባሕልና ዘይቤ እንደተጻፈ ፣
3ኛ) በየትኛው ዘመን እንደተጻፈ አስቀድሞ ማወቅ ለማነበብና ለመረዳት ያስችላል ምክንያቱም ሃይማኖት መሠረታዊ ጉዳይ ነውና !!! መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ከ40 በላይ ቅዱሳን ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ ዕብራውያን ናቸው፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስን አንብቦ ለመረዳት የዕብራውያንን ባሕል በከፊልም ቢሆን መረዳት ያስፈልጋል ፡፡ ስለዚህም

በዕብራውያን ባሕል ፡-

1ኛ) አብሮ አደግና ዘመዶችን በሥጋ እንኳ ከአንድ እናትና አባት ባይወለዱም ‹‹ ወንድም ›› ይባላሉ ዘፍ 13፥11
2ኛ) በሃይማኖት የሚመሳሰሉም ‹‹ወንድሞች ›› ይባላሉ ገላ4፥1 ‹‹ ወንድሞቼ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ››
3ኛ) በሕብረት በአንድ (ማህበር) የሚቀመጡ ‹‹ ወንድሞች ›› ይባላሉ ‹‹ ወንድሞች በሕብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው እነሆም ያማረ ነው›› መዝ 133፥1፡፡
በተጨማሪም ሐዋርያት እርስ በርስ ‹‹ ወንድሞች ›› ይባባሉ ነበር ፡፡ ከዚህ በመነሳት ለጌታ ‹‹ ወንድሞቹ ›› ተደርገው የተጠቀሱት ሦስቱ ሐዋርያት በሥጋ የተወለዱ አይደሉም፡፡ ድንግል ማርያምም ከጌታ ውጭ ምንም ዓይነት
ልጅ የላትም !!! ልጅ ብቻም ሳይሆን ልጅ
የመውለድ ሃሳብም የላትም አልነበራትምም !!! በተጨማሪም ወንድሞቹ ተብለው የተጠቀሱት ‹‹ያዕቆብ ›› እና ‹‹ ይሁዳ ›› መልዕክቶቻቸውን ሲጽፉ ‹‹ የጌታ ባሪያ›› እያሉ ጻፉ እንጂ ‹‹ የጌታ ወንድሞች ›› ነን ብለው አልጻፉም
ማስረጃ ፡- የያዕቆብ መልእክት 1፥1 ‹‹የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ››
የይሁዳመልእክት 1፥1 ‹‹ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ ›› ስለዚህ እነዚህ ሐዋርያት ዮሴፍ ከሟች ሚስቶቹ የወለዳቸውና አብረውት ያደጉ እንጂ ከድንግል ማርያም የተወለዱ አይደሉም ፡፡ ‹‹‹እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም የሚለው ትርጉም ›››
ይህን ቃል በመጥቀስ ድንግል ማርያም ክርስቶስን ከወለደች በኋላ ዮሴፍ በግብር አውቋታል የሚሉ መናፍቃን አሉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከወለደች በኋላ ልጅ ወልዳለች የሚል ቃል አልተጻፈም እንጂ !!! ይህን ቃል መነሻ አድርጎ ለመጀመርያ ጌዜ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን የጠየቀው በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ንጉሥ አርቃድዮስ ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምሥት ነገሮችን ግልጽ አድርጎለታል ፡፡ አርቃድዮስም መልሱን በሚገባ አምኗል ተረድቷል ፡፡ ዛሬም ጥያቄውን በድርቅና ሳይሆን ልክ እንደ አርቃድዮስ በየዋህነት ለጠየቀ ሁሉ መልስ የማያስፈልገው ጥያቄ ነው ፡፡ ሆኖም
ለዚህ ስህተታቸው መልስ መስጠቱ ተገቢ ነውና

አነሆ ፡- ‹‹ የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ ዮሴፍ ድንግል ማርያምን አላወቃትም ›› ማለት ፡- ዮሴፍ ድንግል ማርያም ጌታን እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ማን እንደሆነች አላወቃትም(ማንነቷን) አልተረዳም ነበር ለማለት ነው ፡፡ ኋላ ግን ጌታን በወለደች ጊዜ በቤተልሔም እረኞች(ኖሎት) እና መላእክት በአንድነት ሲዘምሩ ፣ የሩቅ ምሥራቅ ነገሥታት(ሰብዓ ሰገል) እጅ መንሻ ይዘው መጥተው ሲሰግዱለት ፣ እንዲሁም ቤተልሔም ላይ የብርሃን ድንኳን ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ሲመለከት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኗን አወቀ (ተረዳ) እስከዚያች ቀን ድረስ ግን ማለትም ጌታን እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ዮሴፍ ድንግል ማርያም የአምላክ
እናት መሆኗን አላወቀም ፣ አልተረዳም ነበር ለማለት ነው ፡፡

አወቀ ማለት በግብር ተገናኘ ማለት አይደለም !!! እንዲህ ከታሰበ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ ፡-‹‹ ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤ ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም››ሉቃ 24፥30-31 ይህም ማለት ጌታችን መሆኑን አወቁ (ተረዱ) ከማለት ውጪ ሌላ ምን ዓይነት ትርጉም ሊኖረው ይችላል ??? (ማዕዱን ቆርሶ እስከሚሰጣቸው ድረስ ግን ጌታን አላወቁትም ነበር)ስለዚህ ማወቅ ማለት መረዳት እንጂ የግድ በግብር መገናኘት ዓይደለም !!
ይቆየን.....
ወስብሀት ለእግዚአብሔር

፩ ሃይማኖት ተዋህዶ

✞_✞_✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot