Get Mystery Box with random crypto!

​​እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት? ክፍል ሁለት @And_Haymanot እመቤታችን ሌ | ፩ ሃይማኖት

​​እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

ክፍል ሁለት

@And_Haymanot

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት(ወልዳለች) በማለት ኑፋቄያቸውን ለሚዘሩ የተሃድሶዎ መናፍቃን በተከታታይ በዚህ ርእሥ የቤተክርስቲያናችንን ምላሽ ማቅረባችንን ቀጥለናል

@Konobyos

‹‹‹ የእጮኛ ትርጉም ›››

እጮኛ የሚለው ቃል ጠባቂ ማለት ነው፡፡ ሌላ ከሰው ልብ የፈለቀ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡ ለምሳሌ ‹‹እናንተን ለዘለዓለም ለእኔ እንድትሆኑ አጭቻችኋለሁ ›› ሆሴ 2፥21 ማለት ለጋብቻ ነውን? ያሳዝናል አጣመው ለተረጎሙት፡፡ አሁንም ሐዋርያው ከጌታችን ጋር ስላዋሐዳቸው ‹‹ ለእርሱ አጭቻችኋለሁ›› 2ኛ ቆሮ 11፥3 ማለቱን እናስተውል፡፡
እንደገናም ምእመናንን የከበረች ማደርያው ስላደረጋቸው ‹‹ለሰማያዊው ክብር አጭቻችኋለሁ ›› ኤፌ 5፥26 ታዲያ እንዲህ ሲል ላጋባችሁ ነው ማለት ይሆን(ሎቱ ስብሐት) ፡፡
እመቤታችን ንግሥተ ሰማይ ወምድር ነችና በ15 ዓመቷ መለኮት ተዋሐዳት ፡፡ ሲዋሐዳትም ለዮሴፍ ታጨች ሉቃ1፥26፡፡ እንግዲህ እጮኛ ማለት ትርጉሙን ያላወቁ ይወቁ እንላለን ፡፡ ነገር ግን ሰው በራሱ ፍቃድ አይተርጉም !!! ሌላው እጅግ የሚደንቀው ነገር ደግሞ ድንግል ማርያም ክርስቶስን ከመውለዷ በፊት እንጂ ከወለደች በኋላ ዮሴፍ ‹‹ እጮኛ›› ተብሎ በአንድም ስፍራ አለመጠቀሱ ነው
ማስረጃ ‹‹ ሕጻንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ ›› ማቴ 2፥3 እንዲሁም በግብጽ 3 ዓመት ከ3ወር በስደት ከቆዩ በኋላ ይህንኑ ቃል ለዮሴፍ በህልም ተነግሮት ‹‹ ሕጻኑን የሚፈልጉት ሞተዋልና ሕጻንና እናቱን ይዘህ ወደ ናዝሬት ተመለስ ›› አለው እንጂ እጮኛህን (ሚስትህን) ይዘህ
ተመለስ አላለውም ማቴ 2፥20፡፡

‹‹‹ የበኩር ትርጉም ›››

የበኩር ልጇን ወለደች የሚለው ቃል ብዙዎችን አሳስቷል ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በተለምዶ የበኩር ልጅ የሚባሉ የግድ ተከታይ ያላቸው መሆን አለባቸው የሚል አስተሳሰብ በመናፍቃን ክፉ ልቦና ስለሰረጸነው፡፡ ነገር ግን በተለምዶ የሚባል ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ጋር አይሰራምና እንዲህ ይታረማል
፡- ‹‹ እግዚአብሔር ሙሴን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳትም ማኅጸንን የሚከፍት በኩር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ አለው ›› ዘጸ 13፥1-2 ይህ ቃል እንደሚገልጸው በኩር የሚባሉት ለመጀመርያ ጊዜ ከእናታቸው ማኅጸን የሚወጡ መሆናቸውን እንጂ ግዴታ ተከታይ ሊኖራቸው እንደማይገባ ያረጋግጣል ፡፡ አንድም ብቻ ቢሆን የእናቱም ማኅጸን ለመጀመርያ ጊዜ ከፍቶ ከወጣ ተከታይም ባይኖረው በኩር ነው ፡፡ ይሄ የበኩር ትርጉም ካልገባን ወደ ሌላ ፤ ይልቁን ወደ ማንወጣው አዘቅት መዘፈቃችን አይቀሬ ነው ፡፡
ለምሳሌ ቆላስየስ 1፥7 ላይ ስለ ክርስቶስ ሲናገር ‹‹ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው ›› ይላል እዚህ ጋር በኩር የሚለው ቃል ተወዳዳሪ ላላቸው ነገሮች የሚጠቀስ ሆኖ ከቀረበ ጌታን ፍጡር አድርጎ ከፍጡራን ጋር አነጻጽሮ እርሱ ከፍጥረታት በፊት ቀደም ብሎ የተፈጠረ ፍጡር ነው እንደማለት ይሆናልና(ሎቱ ስብሐት)፡፡
እንደገናም በኩር የሚለውን ቃል በሥጋዊ ደማዊ ሃሳብ ከተረጎምነው ዕብ 1፥6 ላይ ‹‹በኩርን ወደ ዓለም ሲያገባ ›› የሚል ቃል አለ እዚህ ላይ የክርስቶስ በኩር ተብሎ መጠራት አብ ቀዳሚ ተከታይ የሌለውን የባሕርይ ልጁን ወደ መሬት ሂድ ፣ ውረድ ተወለድ ፣ ሙት ተሰቀል ብሎ እንደላከው ለመግለጽ ነው ፡፡ ታድያ አብ በኩርን ወደ ዓለም ሲልክ በኩር የሚለው ቃል ተጠቅሷልና አብም ከክርስቶስ ሌላ ልጅ አለው ማለት ነውን? እናንት ግብዞች መናፍቃን የመጽሐፍን ቃል በግርድፍ መረዳት ምን ያህል እንደሚያስት ይረዱ ድንግል ማርያምን የነኩ እየመሰላቸው ባለቤቱን መንቀፋቸው ያሳፍራል !!!
እርሷስ ክብር ይግባትና በተቃዋሚዎች አፍ አትረክስም እርሱ ባለቤቱ አንዴ አክብሯታልና ፡፡ ‹‹ የበኩር ልጇን ወለደች›› መባሉ መጀመርያና መጨረሻ የሌለውን አምላከ አዶናይ ፣ ልዑለ ባሕርይን ወለደች ማለቱ ነው፡፡

ይቀጥላል
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
Join
@Konobyos
Join
@And_Haymanot
Join
@And_Haymanot

ለሌሎች ሼር በማድረግ ኑፋቄያቸውን አብረን እንዋጋ

የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡