Get Mystery Box with random crypto!

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት? የመጨረሻ ክፍል #ማስረጃ ‹‹ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም | ፩ ሃይማኖት

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

የመጨረሻ ክፍል

#ማስረጃ
‹‹ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ›› ዘፍጥረት 4፥17 የሚለው ቃል በግብር
እንደቀረባት(እንደተገናኛት) የታወቀ ነው
ምክንያቱም አወቃት ብቻ ብሎ አላቆመም ‹‹ ጸነሰችም ›› ይላልና !!! ነገር ግን ዮሴፍ ድንግል ማርያምን እስክትወልድ ደረስ አላወቃትም ካለ
በኋላ ሌላ ምንም ዓይነት ተቀጽላ ቃል የለውም ፡፡ መናፍቃን በግድ እናጋባ እናዋልድ ካላሉ በቀር ጸነሰችም ወለደችም አላለም አዚያው ላያ ያበቃል አራት ነጥብ ፡፡ ‹‹‹ ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ውጪ ልጅ የላትም ! ›››

ተጨማሪ ማስረጃዎች እነሆ ፡- ሲጀመር መጽሐፍ ቅደስ በአንድም ቦታ ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ውጪ ልጅ አላት አይልም ብሎም አያውቅም !!! መጽሐፍ ቅዱስ እውነቱን እውነት ሐሰቱንም ሐሰት የሚል መጽሐፍ ስለሆነ ያልሆነውን ሆነ አይልም የሆነውንም አይደብቅም !!! ወንጌልን ለዓለም የሰበኩ ቅዱሳን ሐዋርያትም ድንግል ማርያምን ማዕከል አድርገው አስተምረዋልና ከክርስቶስ በኋላ ልጅ ወልዳ ቢሆን ኖሮ ለምን ደበቁን ? ለምሳሌ ጌታችን ሲሰቀል በመስቀል ሥር ሆና ስማልቀሷ ፣ለዮሐንስ ስለመሰጠቷና መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ እርሷ በመሃከላቸው እንደነበረች ሲጽፉ ለምን ከጌታ ሌላ ልጅ መውለዷን አልነገሩንም? ለምንስ ደበቁን? አሁንም በዚህ አቋም ለጸናችሁ መናፍቃን እውን መለኮት ባደረበት ማኅጸን ሰው ያድርበት ይሆን? አዎ ከሆነ ያንተ ኢየሱስ ፍጡር እና ተራ ሰው እንጂ አምላክ አይደለም !!!
የኛ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባደረበት ማኅጸን ግን ማንም….. !!! ማንም…. !!! ማንም…. !!! አያድርበትም ፡፡ በድጋሚ ልምጣባችሁ እውን ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ውጪ ሌላ ልጅ ያስፈልጋት ይሆን ከዚያ በኋላ ብትወልድም ሰው አምላክ አይሆን? አበው እንኳ ‹‹ ሃምሳ ቢወለድ …… ከተባረከ ይበቃል አንዱ ›› ብለው የለ ታዲያ ድንግል ማርያም ከአንዱ ከብሩክ ልጇ ከክርስቶስ ሌላ ምን ሽታ ትወልድ ይሆን ?


መጽሐፍ ቅዱስ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን እንዴት እንዳስቀመጠ ተመልከት ፡-
1) “እቴ ሙሽራዬ የተቆለፈች ገነት የተዘጋ ምንጭ የታተመች ፈሳሽ ናት”መኃ.ዘሰ 4÷12 (ዳዊት የመንፈስ አባቷ ነውና ልጄ ይላት ነበር ሰሎሞን ደግሞ የዳዊት ልጅ ነውና እህቴ ያላታል የመንፈስ ወንድሟ ነውና)
2) “የምስራቁም በር ለዘለዓለም ተዘግቶ ይኖራል ሰውም አይገባበትም እግዚአብሔር አንዴ ገብቶበታልና” ት.ሕዝ 44÷1-2 (ምሥራቅ የተሰኘች ድንግል ማርያም ናት በርሷ ሰማይነት ክርስቶስ ፀሐይ ሆኖ ወጥቷልና) ይህን ቃል ለቤተ መቅደስ ነው ብለህ የምትከራከር ካለህ ‹‹ ለዘለዓለም የተዘጋ ቤ/መ በዚህ ምድር ላይ የለምና እራስህን አታታል!!!
3) “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል” ሉቃ 1÷34(ይህ የእመቤታችን አስደናቂ ንግግር ለወደፊትም እራሷን አቅባ እንደምትኖር የሚያረጋግጥ ቃል ነው ፡፡ አንድም ኃላፊ ግስ ነው የወደፊት ዓላማዋንም ያረጋግጣል) ‹‹‹ እርሱ ብቻ ልጇ እንደሆነ የክርስቶስ ምስክርነት›››
1ኛ) አይሁድ በምቀኝነት ክርስቶስን ሲሰቅሉት ከእግረ መስቀሉ ሥር የተገኘው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ድንግል ማርያም ብቻ ነበሩ ፡፡ እመቤታችን ሌሎች ልጆች ቢኖሯት ኖሮ ‹‹ እነሆ ልጅሽ ›› ብሎ ዮሐንስን ጠብቃት ባላለውም ነበር ፡፡ በዚህ ላይ ዮሐንስም እኮ እናት ነበረችው ፡፡ ነገር ግን ድንግል ማርያም አንድያ ልጇ በመሆኑ ጌታችን ለዮሐንስ አደራ ሰጥቶአታል ፡፡
2ኛ) የኢየሩሳሌም ሴቶች ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ሲያልፍ ተመልክተው አዝነው ሲያለቅሱ ‹‹ ለራሳችሁ እና ለልጆቻችሁ አልቅሱ ›› ተብለዋል እመቤታችንም መስቀል ሥር ሆና ታለቅስ ነበር ታዲያ ለምን ‹‹ ሄደሽ ለልጆችሽ አልቅሺ አላላትም ? ? ?
‹‹‹ ትልቅ እርምት የሚሻው የመናፍቃን ስህተት ›››‹‹ ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም›› ማቴ13÷56 የሚለውን ቃል ለማን እንደተነገረ እንኳ ሳያስተውሉ ጭራሽ ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ሌላ ልጅ እንዳላት አድርገው ይህን አሳፋሪ ቃል ሲጠቀሙበት አይቼ እኔም አፈርኩበት !!! የዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ዓላማ አይሁድ ክርስቶስን ወንድሞች አሉት ፤
ዮሴፍ ከሟች ሚስቱ የወለዳቸውን ሁሉ ከድንግል ማርያም ነው ብለው በማሰባቸው ወይም በመናገራቸው ተሰናከሉ(ተሳሳቱ) ማለት ነው ፡፡

ታዲያ እነርሱ ክርስቶስ የዮሴፍ ልጅ ነው ፤ ድንግል ማርያምም ሌሎች ልጆች አሏት ብለው በማሰባቸው ተሳሳቱ ከተባለ ለምን አንተ ደግመህ ትሰናከላለህ??? ይህን ስህተታቸውን ሲያስረግጥ ትንሽ ወረድ ብሎ ‹‹ በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም ›› ይላል ፡፡

‹‹‹ ስለ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ ማጠቃለያ ››› እመቤታችን እንደማንኛውም ሴት አይደለችም !!! ክርስቶስን የጸነሰችው ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ሲያበሥራት ነው ፡፡ ‹‹‹ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል ››› በማለት እንደተናገረችው እንደሌሎች ሴቶች በዘር በሩካቤ አይደለምና ነው፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥም ‹‹ አንቺ ከሴቶች
ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ›› ሉቃ 13÷9 በማለት እንደተናገረችው፡፡ ቅዱስ ዳዊትም ‹‹ ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ኦ ሀገረ እግዚአብሔር ›› (የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ ባንቺ የተደረገው ምንኛ ድንቅ ነው) አንዳለ በእመቤታችን የተደረገው ልዩ ነው ፡፡ ለዚህ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ አንክሮ(ምሥጋና) ይገባል ፡፡
          
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
         
     @And_Haymanot
     @And_Haymanot_bot

በሚቀጥለው ደግሞ ተአምረ ማርያም መቅድም ላይ ተአምሯን የሰማ ስጋወደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል የሚለውን እንመለከታለን::