Get Mystery Box with random crypto!

AbrshDREAMS

የቴሌግራም ቻናል አርማ amazingviewss — AbrshDREAMS A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amazingviewss — AbrshDREAMS
የሰርጥ አድራሻ: @amazingviewss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.81K
የሰርጥ መግለጫ

Abrsh DREAMS - A Director, storyteller, cinematographer & Producer. and the other side Personal Development and spiritual coach. My vision is to make wisdom go viral in an accessible, relevant & practical way.

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-15 06:02:01
ሰው ለምን ያረፍዳል?

አንድ ሁሌም ወደ ቢሮ አርፍዶ ስለሚገባና አለቃው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስለሰጠው ሰው ምሳሌ ልስጥህ። ይህ አርፋጅ ሰውዬ በተዳጋጋሚ ያረፍዳል ድጋሚ ማርፈድ ግን አይፈልግም፣ይህ ሰውዬም ‘‘ከነገ ጀምሮ በጥዋት እነሳለሁ፤ ከስራ ባልደረቦቼም ቀድሜ ስራ ቦታዬ ላይ እደርሳለሁ’’ ብሎ ይወስናል። በሚቀጥለው ቀን ግን፣ ልክ እንደ ትናንቱ አርፍዶ ይገባል። ከዚያም አለቃው ‘‘ለምንድን ነው ያረፈድከው?’’ ብሎ ሲጠይቀው፣ የተለያዩ ሰበቦቹን ይደረድራል። ሁሌም የሚያረፍድበት ምክንያት ግን ፓራዳይም መሆኑን እሱም ይሁን ምክር፣ ማስጠንቀቅያና ቅጣት የሚሰጠው አለቃው አያውቁም። ግለሰቦች፣ ድርጅቶችም ሆኑ አገር የማይቀየሩበት ምክንያት ፓራዳይም የሚሰራውን ስራ ጠንቅቆ ባለመረዳት ነው።

ብዙ ሰው የማይፈልገውን ነገር በማድረግ የሚፈልገውን ውጤት ባለማግኘቱ ይቆጨዋል። ነገር ግን በሚቀጥለው ቀን የማይፈልገውን ውጤት የሚያስገኘውን ነገር በድጋሚ ያደርጋል። ወደ ስኬትና ደስታ የሚወስደውን፣ ማድረግ የሚገባውን ነገር እያወቀ ስለማይተገብረው፣ የማይፈልገውን ውጤት እያጨደ፣ የማይፈልገውን ሕይወት ይኖራል፤ ቅሉ ‘‘ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል አይደል!’’ አንተም በዚህ አይነት ተመሳሳይ ሕይወት ውስጥ ካለህ፣ ‘‘ለምንድን ነው እያወቅክ የምታበላሸው?’’ ፓራዳይምህ መሆኑን ታውቃለህ?


ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
2.0K viewsAbrsh DREAMS, 03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 06:01:15
አዎንታዊ አስተሳሰብ

አዎንታዊ የማሰብ ሂደትን የሚጠቀም ሰው፣ የማሰብ ሂደቱ ከውጤት ሳይሆን፣ ከትልቅ ሕልሙ ወይም ከሚፈልገው ውጤት ነው የሚጀምረው። አሁን እያገኘ ያለው ውጤት የማይፈልገው ቢሆንም፣ በማሰብ የአዕምሮ መሣሪያው፣ ስለ ሕልሙ እና ሕልሙን ስለሚያሳካበት መንገድ ብቻ ነው የሚያስበው። በሕይወቱ ችግሮች እያሉ፣ በአዕምሮው ስለ ሕልሙ እና ሕልሙን ስለሚያሳካበት መንገድ ብቻ ያስባል።
አንተም ይህንን የማሰብ ሂደት በመጠቀም፣ ሕይወትህን መቀየር ስትጀምር፣ በሕይወትህ በማትፈልጋቸው ውጤቶች እና ችግሮች ተከበህ ልትሆን ትችላለህ። ነገር ግን ቀንህን በምስጋና በመጀመር፣ አሁኑኑ ስለ ትልቁ ሕልምህ ብቻ ማሰብ ጀምር። ትልቁ ሕልምህ ምን እንደሆነ ወስን።

በዚህ የማሰብ ደረጃ ችግሮቹን እንዴት እንደምትፈታቸው ወይም ትልቁ ሕልምህ እንዴት አድርገህ እንደምታሳካው ማወቅ አይጠበቅብህም።
በዚህ አዎንታዊ የማሰብ ደረጃ፣ የማሰብ የአዕምሮ መሣሪያህን በመጠቀም፣ ትልቁ ሕልምህ ምን እንደሆነ መወሰን እና ሕልምህን እንደምታሳካው ማመን ብቻ ነው የሚጠበቅብህ።

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
2.3K viewsAbrsh DREAMS, 03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 06:01:40
በአይንህ አላየኸውም ማለት የለም ማለት አይደለም!

ምናብ በሕይወታችን የምንፈልገውን ማንኛውንም ነገር በሀሳብ፣ በምስልና በስሜት የምናመነጭበት፣ የምንቀርጽበትና የምንፈጥርበት ልዩ የአዕምሮ መሣሪያ ነው። ይህ መሣሪያ በሕይወትህ ላይ ለውጥ እንድታመጣ፣ በትክክል ስትጠቀምበት ደግሞ ተዓምር እንድትፈጥር ያስችልሀል።

አንድ ሰው ምናቡን በትክክል ሲጠቀም፣ ኪሳራን አሸንፎ በቀላሉ ትርፍ ማግኘት ይጀምራል። ምናባችንን በትክክል ስንጠቀምበት፣ ችግር ውስጥ ሆነን በአምስቱ የስሜት ህዋሶቻችን ያልታየን “መፍትሄ” በምናባዊ መንገድ ማየት እንችላለን። ለችግራችን የሚሆነውን መፍትሄ በዐይናችን አላየነውም ወይም በጆሯችን አልሰማነውም ማለት፣ ችግራችን ትክክለኛ መፍትሄ የለውም ማለት አይደለም።

በዐይንህ አላየህም ማለት፣ ምንም ነገር የለም ማለት ወይም ውስጣዊ በሆነው ምናብ የአዕምሮ መሣሪያህ አታይም ማለት አይደለም። ገንዘብ ስለማግኘትም ስናወራ፣ ልትረዳው የሚገባህ ዋናው ቁም ነገር የምትፈልገውን ስራ ለመጀመር የሚያስፈልግህን ገንዝብ በዐይንህ አላየኸውም ማለት፣ ገንዘቡ የለም ማለት አለመሆኑን ነው። ማንኛውንም ነገር በትክክለኛው መንገድ ስትፈልግ፣ የሚያስፈልግህን ነገር ሁሉ ማየት ከዚያም ማግኘት ትጀምራለህ። የሚያስፈልጉህ ነገሮች በአምስቱ የስሜት ህዋሶችህ ባይታዩህም፣ ማየት ግን ትችላለህ፤ በምኔ ብትል፣ በምናብህ። የሚያስፈልግህን ነገር በምናብህ ካየኸው፣ በአዕምሮህ ታስበዋለህ። በአዕምሮህ ስታስበው ደግሞ በልብህ ታምነዋለህ። ከዚያም በአምስቱ የስሜት ህዋሶችህ ሊጨበጥ ወደሚችል ነገር ትቀይረዋለህ። ይህንን ሀሳብ በትክክል ካልተረዳኸው ግን፣ የማይሆን ነገር ብቻ መስሎ ሊታይህ ይችላል።

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
1.5K viewsAbrsh DREAMS, 03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 06:02:07
የማሸነፍ ምስጢር

አብዛኛውን ሰው ‘‘...አንድ ሴት ልጅ፣ ከአንድ ወንድ ልጅ እኩል ወይም ከወንድ ልጅ በላይ መሮጥ ትችላለች?” ብለህ ብትጠይቀው፣ ለሰከንድ ሳያስብ፣ ‘‘አትችልም’’ ብሎ ሊመልስ ይችላል። “አንድ ሴት፣ ከአንድ ወንድ እኩል ወይም በላይ መሮጥ አትችዪም” የሚል ፓራዳይም ከልጅነቷ ከተቀረጸላት፣ ይህንን የተደጋገመላትን ውሸት ነው የምታምነው። ነገር ግን በሕይወት አጋጣሚ እንደ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት ደፋር፣ አልማዝ አያናና ሌሎች ሴት አትሌቶቻችን ይመጡና ውሸቱን አጋልጠው እውነቱን ግልጽ ያደርጉታል። እነ ሳህለወርቅ ዘውዴ ይመጡና የአገር ንጉስ ይሆናሉ። ወላጆች፣ ሴት ልጆቻችሁ እንደ ፕሬዚደንታችን፣ አትሌቶቻችንና በተለያዩ ዘርፎች ላይ ትላልቅ ደረጃ ላይ እንደደረሱ ሴቶች ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ፣ እና ታሪክ እንዲሰሩ የምትፈልጉ ከሆነ፣ የሴት ልጆቻችሁን አዕምሮ እንዴት እየቀረጻችሁ እንደሆናችሁ ማስተዋል አለባችሁ።

አንዳንድ ሴቶች ‘‘አሁን ዳዊት እያለ ያለው እኮ እውነቱን ነው... ነገር ግን የኔ ቤተሰብ ‘ይቻላል’ እያሉ አላሳደጉኝም’’ ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ሕይወትሽን ለመቀየር፣ ራስሽን መቀየር ብቻ ነው ያለብሽ። አሁን አንዴ ሰከን ብለሽ ማሰብ ያስፈልግሻል። ‘‘በአዕምሮሽ እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ’’ ብለሽ ነው የምታምኚው? በአዕምሮሽ “ምን ማድረግ አትችይም” ብሎ የገባ የውሸት እምነት አለ? አዕምሮሽንና በአዕምሮሽ ያለውን ሀሳብና እምነት ስትቀይሪ፣ ሕይወትሽ ይቀየራል። ትልቁን ሕልምሽን ለማሳካት ራስሽን ካልከለከልሽ፣ ማንም አይከለክልሽም። ራስሽን ከረዳሽ ደግሞ የማንም እርዳታ አያስፈልግሽም።

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
628 viewsAbrsh DREAMS, 03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 06:00:21
መሀይም ስለሆንን ነው የፈለግነውን ውጤት የማናገኘው!

የምትፈልገውን ውጤት የምታገኝበትን ምስጢር ካላወቅክ፣ የፈለግከውን ውጤት ማግኘት ይከብድሀል። አስቀድመን ስለመሀይምነት ትርጉም ስንነጋገር እንዳነሳነው፣ መሀይምነት ማለት፣ ነገሮችን የማከናወኛ ምስጢርን አለማወቅ ነው። በዚህም በርካታ ሰዎች መሀይም ናቸው። ቀለም ለቆጠርነው እንኳ፣ እንዴት አድርገን ትልቅ ሕልም በማስቀመጥ፣ ሕይወታችንን መቀየር እንዳለብን፣ ትምህርት ቤቶቻችን አላስተማሩንም። ሕልሙን የሚያሳካበትን ምስጢር ያላወቀ ሰው፣ ስለ ትልቅ ሕልሙና ሕልሙን ማሳካት ስለሚችልበት መንገድ ሲያስብ ይጠራጠራል፤ ይፈራል፤ ይጨነቃል፤ ደግሞም ተስፋ ይቆርጣል። ሕልሙን የሚያሳካበትን ምስጢር ተምሮ መሀይምነቱን ሲያሸንፍ ግን፣ የማንንም ሰው መብት ሳይነካ፣ ትልቁን ሕልሙን በማሳካት የሚፈልገውን ሕይወት መኖር ይጀምራል።

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
932 viewsAbrsh DREAMS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 06:01:21 ፕሮፌሰሩ ስለ ማርኬቲንግ ለተማሪዎቹ ገለፃ ሲያደርግ እንዲህ አላቸው።
1. በጣም ቆንጆ የሆነች ሴት አይተህ ወደ እርሷ ሄደህ በጣም ሀብታም ነኝ አግቢኝ ካልካት = #Direct_Marketing ይባላል።
2. በአንድ ዝግጅት ታድመህ ጓደኛህ ቆንጆዋ ሴት ጋር ሄዶ አንተን እየጠቆመ ያ የምታይው ሰው ሀብታም ነው አግቢው ካለ = #Advertising ይባላል።
3. ሴቷ ወደ አንተ ቀርባ አንተ ሀብታም ነህ ፤ ልታገባኝ ትችላለህ ካለችህ = #Brand_Recognition ይባላል።
4. እኔ በጣም ሀብታም ነኝ ስለዚህ እንድታገቢኝ እፈልጋለሁ ብሎ በጥፊ ከመታችው = #Customer_Feedback ይባላል።
5. በጣም ሀብታም ሰው ነኝ አግቢኝ ስትላት ባሏን ካስተዋወቀችህ = #Demand_and_Supply_Gap ይባላል።
6. ሀብታም ነኝ አግቢኝ ብለህ ሳትጨርስ ሚስትህ ከተፍ ካለች = #Restriction_from_Entering_New_Market ይባላል።

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
1.2K viewsAbrsh DREAMS, 03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 06:01:21 አየር ልቀቅ!

በአንድ ትልቅ የመኪና ማምረቻ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሠራ መሐንዲስ፤ በዐይነቱ ልዩ የሆነ፣ በተወዳዳሪነቱም የላቀ- አዲስ የመኪና ሞዴል ይነድፋል። የድርጅቱ ባለቤትም በውጤቱ እጅጉን በመደነቅ ምስጋናን ይቸረዋል። ይሁንና መኪናውን ከማምረቻ ሥፍራ ወደ ማሳያ ክፍል ለመውሰድ በሚሞክሩበት ጊዜ፤ አዲሱ መኪና ከመግቢያው በር በ10 ሳ.ሜ እንደሚረዝም ይረዳሉ።

መሐንዲሱም፤ ቀድሞውኑ የመኪናውን ንድፍ ሲሠራ ይህንን ግንዛቤ ውስጥ ባለማስገባቱ ይተክዝና ያዝን ጀመር። የድርጅቱ ባለቤትም መኪናውን ከማምረቻ ሥፍራ እንዴት እንደሚያወጣው ግራ ይገባዋል። ይህን ጊዜ ቀለም ቀቢው ተነሥቶ፤ "መኪናውን ሊያወጡት እንደሚችሉና በመኪናው ላይኛው ክፍል ብቻ ትንሽ ጭረት እንደሚኖር እሱም ቢሆን ከወጣ በኋላ በቀለም ሊስተካከል እንደሚችል" በመናገር ተስፋን ይሰጣል።

ለጥቆ መሐንዲሱ፤ "የመግቢያውን በር ሰብረው መኪናውን ማውጣት እንደሚችሉና መልሰውም በሩን እንደሚጠግኑት" ይናገራል። ይሁንና የኩባንያው ባለቤት የተነሱት የመፍትሄ ሐሳቦች በመላ አልተዋጡለትም፤ መኪናው ላይ የሚደርሰው ጭረትም ሆነ የመግቢያውን በር መስበሩ መልካም መስሎ አልታየውም። ታዲያ ይህ ሁሉ ሲሆን ዳር ቆሞ ሲታዘብ የነበረው የኩባንያው ጥበቃ ሠራተኛ በዝግታ ወደ ባለቤቱ ይጠጋና የሚቻል ከሆነ በነገሩ ላይ ሐሳብ ለመስጠት እንደሚፈልግ ይናገራል።

ኃላፊውም የጥበቃ ሠራተኛው የነገራቸው ኤክስፐርቶች ሊሰጡ ያልቻሉትን በመሆኑ እጅጉን ተደነቁ። ጥበቃው የተናገረው፤ "መኪናው ከመግቢያው በር በትንሽ ሳ.ሜ ከፍታ ብቻ ነው የሚረዝመው፤ ስለዚህ በቀላሉ በጎማው ያለውን አየር ስትለቁ የመኪናው ቁመት ይወርዳል፤ በቀላሉም መውጣት ይችላል" የሚል ነበር። ሁሉም በአንድ እጅ አጨበጨቡ!

ይህንን ልብ በል!
አንድን ችግር ከባለሙያ/ኤክስፐርት እይታ ብቻ ተነስተህ ለመተንተን ወይም ለመፍታት አትሞክር። ሁልጊዜም ቢሆን "ተራ" ከሚባል ሰው ለወሳኝ ሁነት የሚሆን ጠቃሚ መልስ እንዳለ አትዘንጋ። ጥበብ በትህትና የምትሸመት ገንዘብ መሆኗን ልብ በል። አንድን ጥያቄ የሚያከብደውም የሚያቀለውም የነገሩ ውስብስብነት ሳይሆን ችግሩን የምትፈታበት መንገድ መሆኑን አስተውል። የህይወት ነገርም እንዲሁ ነው ቀለል አድርገህ አስብ በቀላሉም ኑር ምክንያቱም 'ተሞልተን' ነው እንጅ እኛ በተፈጥሮ መልካም ሰዎች ነን።

ይኸውልህ አንተ በጠጣኸው መርዝ ሌላው እንዲሞት መቼም አትጠብቅም ውስጥህን የሞላው 'አየር' ያንተን እጣ ፈንታ ይወስናል። ምናልባት ይህ አየር (ንዴት፣ ጸጸት፣ ግራ መጋባት፣ ቂም፣ ጥላቻና በቀል) ጉዞህን ገቶት፣ ነገህን አጨልሞት፣ እርምጃህን ገድቦት፣ ተስፋን አሳጥቶ ሩቅ አልመህ ሩቅ እንዳታድር አድርጎህ ይሆናል። የተሞላኸውን አየር ልቀቅ። ስትለቅ የሚለቅና የሚለቀቅ ነገር አለ። ያን ጊዜ አላልፍም ካልክበት ሁኔታ ልታልፍ፣ አልወጣም ካልክበት ማጥ ልትወጣ ትችላለህ። አየህ በስተመጨረሻ ሁሉም ነገር "ቁመትን/አስተሳሰብን ማስተካከል" ይሆናል፤ በውጤቱም የውስጥ ሰላምን፣ ጤናማ አስተሳሰብን፣ ስኬትንና ደስታን... ማጣጣም ትችላለህ!!

ሳሙኤል ገዳ እንደፃፈው

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
1.3K viewsAbrsh DREAMS, 03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 06:00:59 ሁሌም ራሳችን ላይ እንስራ!
ብዙ ሰው አዲስ ነገር በቀላሉ ለመቀበል ዝግጁ አይደለም፤ በነዳጅ መኪና የለመደ በኤሌክትሪክ መኪና ያብዳል፣ በኩራዝ ብርሃን የለመደ በኤሌክትሪክ ብርሃን ያብዳል፣ በፈረስ ጉዞ የለመደ ሰው በመኪና ለመሄድ ያብዳል፣ በአውሮፕላን የለመደ በመንኮራኩር ለመጓዝ ያብዳል፣ ሰው ከመሬት የሚወጣው ሲሞት ብቻ ይመስለዋል፤ ከምድር ወጥተህም ግን ወደ ጠፈር በሮኬትም ይመጠቃል! በርካታ አዲስ ነገሮች በአለማችን ላይ እንየተከሰቱ ነው ነገር ግን አንተ ራስህን ዝግጁ ካላደረክ አይንህ እያየ ያልፍሀል ከዚያም ያልፍብሃል ለዚያ ነው ራሳችን ላይ እንስራ የምለው!

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
1.4K viewsAbrsh DREAMS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 06:00:14 #Ethiopia ተስፋ_ጽናት_ደስታ!!

"ለመኖር ሁለት ፐርሰንት ዕድል ብቻ እንዳለኝ በሀኪሞች ተነግሮኛል:: ነገር ግን ሁለት ፐርሰንት ማለት ዜሮ ማለት አይደለም:: ሁለት ፐርሰንት ማለት የሆነ ነገር እንደሆነ ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ!!"

"ደስተኛ ልትሆን ለመወሰን ሕይወት ከዚህ በፊት ከነበረው ከባድነት ቀላል እስኪሆን መጠበቅ የለብህም!!"
____

ወደ American Got Talent የሚመጡ ተወዳዳሪዎች መድረኩን ከመርገጣቸው በፊት እጅግ ከሚጨነቁባቸው ነገሮች ዋናው "ሳይመን ምን ይለን ይሆን!?" የሚል ይሆንና ትንሽ ዘና ካሉ "ሳይመን 'yes’ ይሰጠን ይሆን!? የሚል ይሆናል:: ከሳይመን ካውል አፍ 'yes’ ከመቀበል አልፎ ከአይኖቹ እንባ እንዲወጣ ማድረግ ግን እጅግ ከባድ ነው:: ከሁሉ በላይ ከባዱ ግን የሳይመን እጆች ውዱን Golden Buzzer  እንዲጭኑ ማድረግ ነው::

አንዲት ሰውነቷ ገርጥቶ ልትቀነጠስ የደረሰች ኮሳሳ ተወዳዳሪ ወደ መድረክ መጣች:: የዕለቱ ተረኛ ጠያቂ ሀዋርድ ነበር:: "እንዴት ነሽ!?" አላት:: በጣም ደስተኛ ነኝ:: እዚህ በመሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል" አለች:: ሁሉም ተወዳዳሪ የሚለው ስለሆነ አይደንቅም:: አራቱም ዳኞች ከተለመደው ያልተለየ ደስታቸውን ገለፁ::

ሀዋርድ ቀጠለና "ምንድነው የሚታቀርቢልን!?" አላት:: እሷም "It is Ok” የሚል የራሴን ስራ ነው" አለች:: ሁላቸውን ባንድ አፍ "አዎ! ሁሉ ደህና ነው" አሉ:: ግን ይህም አይገርምም:: ሀዋርድ ቀጠለና "ግን ሁሉ ደህና ነው ስለምንድነው?" ሲላት ከካንሰር ጋር ስትታገል የኖረችውን የሕይወት ውጣውረድ ነገረቻቸው:: የሁሉም ፊት ጨለማ:: የእሷ ፊት ግን የደስታ ጨረር ከመርጨት አላቆመም:: ኮምጨጭ አለችና "አረ ሁሉ ደህና ነው:: እኔ ሰላም ነኝ" አለቻቸው::

የዚያኔም ባለስል አስተያየቱ ሳይመን "አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? አሁን እንዴት ነሽ!?" አላት:: እሷም "የመጨረሻውን ምርመራ ሳደርግ በሳንባዬ: ጣፊያዬና ጉበቴ ላይ ካንሰር እንዳለ ተነግሮኛል" ስትል ሳይመን በድንጋጤ አስፈሪ ጭጋግ ውስጥ ሆኖ "ዋው" ሲል ሀዋርድ ቀጠለና "ስለዚህ ደህና አይደለሽም ማለት ነዋ" አላት:: "በርግጥ በሁሉም መልኩ አይደለም" ስትል ሀዋርድ ተገርሞ "ማንም ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሽ እስከማያውቅ ድረስ ለሌሎች የደስታ ጨረር የሚረጭ አስገራሚ ፈገግታ አለሽ" ብሎ አሞካሻት!!

Nightbird የሕይወት ታሪኳን አሳማኝ በሆነ መልኩ በዜማ ካቀረበች በኅላ የደኞች ውሳኔ የሚሰጥበት  ሰአት ደረሰ:: ሁሉም ሳግ እየተናነቃቸው በስሜት የተሞሉ አዎንታዊ አስተያየቶችን ሰጡ:: ተራው ሲደርስ ተጠባቂው ሳይመን ሌሎች ዳኞች በሰጡት አስተያየት ሙሉ በሙሉ እንደሚስማማ ገልፆ ተጨማሪ ስሜቱን እንዴት መግለጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ሲያመነታ ሳለ መኻል ላይ አቋርጣ በከፍተኛ ፈገግታ በመሞላት "ደስተኛ ልትሆን ለመወሰን ሕይወት ከዚህ በፊት ከነበረው ከባድነት ቀላል እስኪሆን መጠበቅ የለብህም" የሚል እጅግ አስገራሚ አስተያየት ሰነዘረች::

ያ ንግግር ብዙዎችን ያስገረመ ቢሆንም ሳይመንን ለደቂቃዎች አፍዝዞ እንባ ከሁለቱን ዓይኖቹ ፈሰሱ:: ከፊቱ ያለውን የመጠጥ ዕቃ አነሳና ተጎንጭቶ ሳግና እንባውን አወራረደ:: በመቀጠልም  አስተያየቱን ሰነዘረ:- "በዚህ ዓመት ታላላቅ ችሎታ ያለቸውን ሰዎች  አይቻለሁ:: ሆኖም ላንቺ 'yes’ አልሰጥም" ሲል ከዳኞች እስከ ታደሚ በቅሬታ አጉተመተሙ:: ሳይመን አልጨረሰም ነበር:: "የሚሰጥሽ ከ'yes’ የተሻለ ነገር ነው" አለና እጆቹ ወደ Golden Buzzer ሄደ:: አደራሹ በከፍተኛ ደስታ ሲያስተጋባ Nightbird የወርቁ ብናኝ ላይ በደስታ እንባ ተደፋች!!
—-------
Jane Marczewiski (በቅጽል ስሟ Nightbird) በ2017 ባደረገችው ምርመራ ደረጃ ሶስት የጡት ካንሰር በሽተኛ መሆኗ ታውቆ ከዚያ በኅላ በምድር የሚኖራት ዕድሜ ስድስት ወራት ብቻ እንደሆነ ተነገሯት ከሕይወት ጋር ትግሏን ቀጠለች:: ትንሽ ቆይቶ በ2018 ከካንሰር ነፃ መሆኗ ቢነገራትም መልካም ዜናው ብዙም አልቆየም:: እንደገና በሽታው እንዳለባት ተነግሯት ትግሏን ቀጠለች:: የሕይወት ትግሏን ከጎኗ ሆኖ ማገዝ የሚጠበቅበት የአምስት ዓመት የትዳር አጋሯ ጥሏት ኮበለለ::

ይቺ ምስኪን: ብቸኛ ፅኑ ሴት ናት ሰኔ 10 2020 American Got Talent መድረክ ላይ ቆማ ሳለ ሀዋርድ "እዚህ ከማንጋር መጣሽ?" ሲላት (አባባሉ "የድል ደስታሽን ከማን ጋር ሊታጣጥሚ ነው?" የሚል ድምፀት አለው) "ብቻዬን ነኝ" ብላ የመለሰችው እና ከሳይመን Golden Buzzer በኅላ ከአዳራሹ ብቻዋን እየዘለለች የወጣችው!!

በዚህ የኮቪድ ውጥንቅጥ ወቅት ለብዙዎች የደስታ ምስክር እንደሆነች በማመን "you are the voice we all need to hear this year” የሚል አስተያየት ከሳይምን የተሰጣት ይቺ ብርቱ ሴት ከBBC ጋር በነበራት ቃለ መጠይቅ "ወደ ኅላ የሚያስቀርብኝ መልካም ነገሮች የሉትምና እግዚአብሔር የሆነ ጊዜ ላይ ቅጽበታዊ ፈውስ እንደሚያመጣ አምናለሁ" ስትል ተናግራለች::

May 3 በለጠፈችው ብሎጏ:- "እግዚአብሔር መጀመሪያ ለእኛ ራሱን ባስተዋወቀበት ወቅት (ዘፍጥረት) ያሳየንን ነገር ረስተን ይሆናል:: አቧራ ላይ እየዳሀ ነበር የቀረበን:: እንዴት መተንፈስ እንዳለብን በማናውቅበት ጊዜ ሳንባችንን በአየር ሞልቶ መተንፈስን አስተማረን" ብላለች!!

በሌላ ጽሑፏ ሕመሟን በተመለከት "እግዚአብሔር አብዛኛውን ጊዜ ወሳጅ ሳይሆን ሰጪ ነው:: ከመውሰድ ይልቅ ይጨምራል" ትላለች:: “ጨለማዬን አልወሰደውም ግን ብርሃን ጨመረልኝ:: ብቸኝነቴን አልፈወሰውም ግን እርሱ ይበልጥ ቀረበኝ" ትላለች:: በሕመሟ ተስፋዋ ይጨምራል እንጂ ተስፋ ቢስ አይደለችም:: በመሆኑም  "በህመሜ ተስፋ የማደርገው የእግዚአብሔርን ቅርበት በዚያ ስላወቅሁ ነው" ትላለች::

"እግዚአብሔር ትሁት ሆኖ ወደ እኛ የቀረበበት ከመስቀል የተሻለ ስፍራ የለም:: በኃጢአትና በሽታ ወደ ተመታው ዓለም  እግዚአብሔር ሰው ሆኖ መጣ::  ይህም እግዚአብሔር በሙሉ ፈቃድና ትህትና የኃጢአታችን ምትክ ሆኖ ሊቤዥን ወደ መስቀል ሄደ" ትለናለች!!

በመከራና ስቃይ ውስጥ ስናልፍ ልኖረን የተገባው እምነት: ተስፋና ፅናት ይኼ ነው:: የመስቀሉ ስቁዩ ኢየሱስ ስቃይና ህመማችን ይገባዋል:: የምንጠብቀው ፍፁም ቤዛችንም እሱ ነው:: አንድ ቀን ፈጽሞ የማይታመምና የማይሰቃይ አካል እስክንለብስ አሁን ከብዶን ብንቃትትም ተስፋ ቆርጠን ግን ወደኅላ አናፈገፍግም!!

መልካምና የሚያንፁ አስተማሪ ጽሁፎችን  ለተከታታይ ቀናቶች ሼር አደርጋችኋለሁ። እናተም በደስታ ለሌሎች ማካፈላችሁን አትርሱ።
ቻናሉንም ሼር ማድረጋችሁን አትዘንጉ።
----
አንድ ሰው ቢያንስ ለ #5 ሰዎች ሼር ያድርጉ።

==========||==============


____

ዛሬን ኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
1.6K viewsAbrsh DREAMS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 06:00:14
1.2K viewsAbrsh DREAMS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ