Get Mystery Box with random crypto!

AbrshDREAMS

የቴሌግራም ቻናል አርማ amazingviewss — AbrshDREAMS A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amazingviewss — AbrshDREAMS
የሰርጥ አድራሻ: @amazingviewss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.81K
የሰርጥ መግለጫ

Abrsh DREAMS - A Director, storyteller, cinematographer & Producer. and the other side Personal Development and spiritual coach. My vision is to make wisdom go viral in an accessible, relevant & practical way.

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-06 06:00:23
ሁሉም ነገር ይቻላል! የማይቻል ነገር የለም! ለአንተ ምን ይቻላል?

ዛሬን ኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
1.5K viewsAbrsh DREAMS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 06:01:17 አልመህ ተኩስ

አንድ ንጉስ ከአጃቢዎቹ ጋር በአንድ ጫካ ውስጥ ሲዘዋወር አንድ ዛፍ ላይ ያየው ነገር ትኩረቱን ሳበው፡፡ በዚህ ትልቅ ዛፍ ላይ የተለያዩ ክብ ቅርጽ ያላቸው ኢላማዎች ተስለዋል፡፡ የገረመው ነገር፣ እያንዳንዳቸው ኢላማዎች መካከል ምንም ሳይስቱ ኢላማቸውን በትክክል የመቱ ቀስቶች ተሰክተው ይገኛሉ፡፡ ንጉሱ በጣም ተገረመና፣ “እነዚህን ኢላማዎች ሁሉ በትክክል አነጣጥሮ የመታውን ሰው ለሰራዊቴ አለቃነት እፈልገዋለሁና ፈልጋችሁ አግኙልኝ” አለ፡፡

ልክ ይህንን ተናግሮ እንደጨረሰ አንድ ወጣት ልጅ ብዙ ቀስቶችን ተሸክሞ እየገሰገሰ ንጉሱ ጋር ደረሰ፡፡ ንጉሱ፣ እነዚህን ሁሉ ኢላማዎች በትክክል የመታው ሰው እሱ መሆኑን ጠይቆ የአዎንታ መልስ ካገኘ በኋላ እንዴት እንደዚህ አነጣጣሪ ሊሆን እንደቻለ ጠየቀው፡፡ የልጁ መልስ አጭርና ግልጽ ነበር፣ “በመጀመሪያ ቀስቴን ወጥሬ በዛፉ ላይ እሰካዋለሁ፡፡ ከዚያም ወደ ዛፉ በመሄድ በተሰካው ቀስት ዙሪያ የክብ ምልክትን አስቀምጥበታለሁ” በማለት እንደዚያ አነጣጣሪ ያስመሰለውን እውነት ፍርጥ አደረገና ነገረው፡፡

ይህ መሰረታዊና ቀላል አፈ-ታሪክ የብዙ ሰዎችን የሕይወት ዘይቤ ያንጸባርቃል፡፡ ይህ ወጣት በመጀመሪያ ዓላማን አድርጎ አልነበረም ያንን ዓላማ ለመምታት ጥረት ያደረገው፡፡ በቅድሚያ ወዳሻው ቀስቱን ከለጠጠና ከሰነዘረ በኋላ ቀስቱ ያረፈበትን ስፍራ ነው እንደዓላማ በመቁጠርና ልክ ዓላማውን እንደመታ ለማስመሰል በዙሪያው ክብን ያበጀለት፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲሁ ናቸው፡፡

በመጀመሪያ ዒላማንና ግብን አቅደው በዚያ ባቀዱት መሰረት ሊተኩሲ ሲገባቸው ከተኩሱ በኋላ ቀስቱ ያረፈበትን ነው እንደግብ የሚቆጥሩት፡፡ በሌላ አባባል፣ ያገኘነውን፣ የመሰለንንና የቀለለንን ነገር ካደረግን በኋላ በዚያ ባደረግነው ተግባር ዙሪያ ዓላማን ለመፍጠር መሞከር የሞኝነት ሁሉ ሞኝነት ነው፡፡ ዓላማ ከሌለን የምንሄድበትን አናውቅም፡፡ ግብም ከሌለን ተኩሰን የመታነው ነገር ሁሉ እንደ ግብ ስለሚቆጠር ይህንና ያንን ስናደርግ ጊዜያችን ይባክናል፡፡ ለዚህ ነው በዓላማና በግብ የምንመራ ሰዎች መሆን ያለብን፡፡

አንድ በር ተከፍቶ ስላገኘህ ብቻ ከገባህ በኋላ የገባህበትን ዓላማ ለማግኘት አትሯሯጥ፤ በመጀመሪያ በዚያ በር የመግባትህ ጉዳይ ከሕይወትህ ዓላማ ጋር መስማማቱን አረጋግጥ፡፡

አንድ ሃገር የመሄድ እድል ስለተገኘ ብቻ ከሄድክ በኋላ ዓላማ ለመፍጠር አትሂድ፤ በመጀመሪያ ወደዚያ ሃገር የመሄድህ ጉዳይ ከሕይወትህ ዓላማህ ጋር አለመጣረሱን አረጋግጥ፡፡

አንድ ሰው ትኩረትና የመፈቀር ስሜት ስለሰጠህ ብቻ ሁለንታንህ በመስጠት ግንኙነት ውስጥ ከገባህ በኋላ ዓላማ ለመፍጠር አትታገል፤ ጓደኛንም ሆነ ፍቅረኛን ከዓላማህ አንጻር ምረጥ፡፡

ስራህንም እንደዚያው! ትምህርትህንም እንዲዚያው! የሕይወትህን ዋና ዋና ክፍሎችም እንደዚያ!

ከዓላማ ተነሳ እንጂ ተነስተህ ከተጓስክ በኋላ ዓላማህን ለማግኘት አትባክን፡፡ ዓልመህ ተኩስ እንጂ የተኮስከው ነገር የመታውን ነገር ሁሉ ዓላማህ እንደሆነ በማሰብ ራስህን በማታለል ዘመንህን አታባክን፡፡


መልካምና የሚያንፁ አስተማሪ ጽሁፎችን  ለተከታታይ ቀናቶች ሼር አደርጋችኋለሁ። እናተም በደስታ ለሌሎች ማካፈላችሁን አትርሱ።
ቻናሉንም ሼር ማድረጋችሁን አትዘንጉ።
----
አንድ ሰው ቢያንስ ለ #5 ሰዎች ሼር ያድርጉ።

==========||==============


____

ዛሬን ኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
1.6K viewsAbrsh DREAMS, 03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 19:13:46

1.6K viewsAbrsh DREAMS, 16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 06:00:54 አሉታዊ አስተሳሰብ

ለምንድን ነው ግን የሰው ልጅ ስለማይፈልገው ውጤት በማሰብ፣ የማይፈልገውን የባሰ ውጤት የሚያገኘው? ለምንድን ነው አሁን ያለውን ችግር በማማረር፣ የባሰ ችግር የሚጠራው? መልሱ ቀላል ነው፤ ማሰብ የአዕምሮ መሣሪያውን በትክክል ስለማይጠቀምበት ነው።
ማሰብ የአዕምሮ መሣሪያውን በትክክል የማይጠቀም ሰው፣ ስለ ችግሩ በማሰብ እና በማማረር የባሰ ችግር ያገኛል፤ የባሰ ውጤትም ያጭዳል። ይህ ማለት ግን እያገኘ ስላለው የማይፈልገው ውጤት ወይም ችግር መፍትሄ የለውም ማለት አይደለም። ማሰብ የአዕምሮ መሣሪያውን በትክክል በመጠቀም፣ አሁን ካለበት አሉታዊ ሁኔታ እና ችግር በመውጣት፣ ወደሚፈልገው አዎንታዊና የመፍትሄ ዓለም መግባት ይችላል።

ዛሬን ኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
2.2K viewsAbrsh DREAMS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 06:00:47 ከውስጥ ወደ ውጭ መኖር

የሰው ልጅ አምስት የስሜት ህዋሳቱን በመጠቀም፣ ከውጪ ያለውን ማንኛውም ነገር ወደ ውስጡ ሲያስገባ ከውጪ ወደ ውስጥ ይኖራል። ፈጣሪ አምስቱን የስሜት ህዋሳት የሰጠን፣ የውጪውን ዓለም በመመልከት አስፈላጊ የሆነ መረጃ እንድንሰበስብና እንድንማር ነው። የሰው ልጅ የተሸወደው ግን፣ እነዚህን አምስቱን የስሜት ህዋሳት በመጠቀም ከውጪ ወደ ውስጥ መኖር በመጀመሩ ነው። ከውጪ ወደ ውስጥ የሚኖር ሰው፣ በውጪ ደስ የሚያሰኝ ነገር ካየ፣ በውስጡ ደስ ይለዋል። ደስ የማያሰኘውን ነገር ከተመለከት ደግሞ፣ ይደብረዋል።

አንድ ሰው በትክክል ማሰብ ሲጀምር፣ ከውስጥ ወደ ውጪ ነው የሚኖረው። ይህ ማለት ደግሞ በውጪው ዓለም ምንም አይነት ነገር ቢፈጠር፣ የውስጡን ሰላምና መረጋጋት እንዲነካበት አይፈቅድም ማለት ነው። ማንኛውም የማያስብና የማሰብ ሂደትን የማይጠቀም ሰው ግን፣ በአምስቱ የስሜት ህዋሶቹ በመጠቀም፣ ከውጪ ወደ ውስጥ በመኖር፣ የውጪው ዓለም መጫወቻ ነው የሚሆነው።

ዛሬን ኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
2.2K viewsAbrsh DREAMS, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 06:01:32 ቅፅበታዊ ውሳኔ
ስጋዊ አካላችንን ቶሎ መቀየር ይከብዳል፤ በጊዜ ሂደት ግን መቀየሩ አይቀርም። ዋና ዋና የሰውነታችን ክፍሎች ከታመሙ ወይም ከአገልግሎት ውጪ ከሆኑ፣ ለመዳን፣ ሀኪም ቤት ገብተን ከባድ ምርመራ ማድረግና የጽኑ ሕክምና ክትትል ማድረግ ሊያስፈልገን ይችላል። ቀለል ያለ ጉዳት የደረሰባቸው የሰውነታችን ክፍሎችም ቢሆኑ፣ ለመስተካከል ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። ሕይወት የሌለውን ጸጉራችንን እንኳ ለማስተካከል ከሰላሳ ደቂቃ በላይ ሊያስፈልገን ይችላል።

አዕምሯችንን ለመቀየር ግን ቅጽበታዊ ውሳኔ ብቻ ነው የሚያስፈልገን።

ዛሬን ኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
2.3K viewsAbrsh DREAMS, edited  03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 06:01:52 ፍራቻ፣ እምነትና አመለካከት፡
በመጀመሪያ በውስጥህ ያሉትን አሉታዊ ፍራቻዎች ከአዕምሮህ እና ከልብህ ለማባረር ወስን። በመቀጠልም ድንቅና አዎንታዊ እምነት በልብህ ለመገንባት ወስን። በመጨረሻም ራስህን በድንቅ አመለካከት በመጠበቅ፣ ከውስጥ ወደ ውጪ ለመኖር ወስን።


ዛሬን ኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
TIKTOK
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
2.7K viewsAbrsh DREAMS, 03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 17:44:57

2.3K viewsAbrsh DREAMS, 14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 21:30:01 በየቀኑ መጽሐፍ ማንበብ

መጽሐፍ በአነበብክ ቁጥር ነው ጥበበኛ የምትሆነው። መጻሕፍቶች የተጠናከሩ የጥበብ ምንጮች ናቸው። ብዙ መጽሐፍት ባነበብክ ቁጥር የበለጠ ለጥበብ እራስህን ታጋልጣለህ።

እራስዎን ለማበልጸግ ማንበብ የሚችሏቸው አንዳንድ መጽሃፎች የትኞቹ ናቸው? ያነበብኳቸው እና ጠቃሚ ሆነው ያገኘኋቸው መጽሃፎች በጥቂቱ እነሆ:-

ትልቅ ሕልም አለኝ፣ Think and Grow Rich, Think like a Monk, 7 Habits, The Science of Getting reach, 10x, Reach dad Poor dad.

በየቀኑ መጽሐፍ በምታነብበት ጊዜ፣ አእምሮህን የበለጠ እና የሰፋ እውቀት ትመግበዋለህ።  ስለዚህ በየቀኑ በማንበብ ከትላንት በልጦ የተዋበ ነገን ታገኛለህ።

Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM

መልካም አዳር
2.6K viewsAbrsh DREAMS, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 21:17:00
ጠይቁ ይሰጣችኋል!

ትልቅ ሕልማቸውን ለማሳካት መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት የሚከፍሉ ሰዎች አንዳንዴ በሕይወት ጉዟቸው ላይ እያሉ፣ ትክክለኛው አቅጣጫ ይጠፋባቸዋል። ከዚያም ምን ማድረግ እንዳለባቸውና ወደ የትኛው አቅጣጫ መሄድ እንዳለባቸው ይጠይቁኛል። መልሱ ይሄው ነው በመጀመሪያ እነዚህ ሰዎች ትክክለኛ ሕልም እንዳላቸው እና መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት እየከፈሉ መሆናቸውን አረጋግጣለሁ። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ስትሆን በመጀመሪያ መረዳት ያለብህ ነገር ለሁሉም ጥያቄ መልስ፣ ለሁሉም ችግር መፍትሄ እንዳለው ነው። በሕይወትህ አንዳንድ ከባባድ ችግሮችና ጥያቄዎች ሲያጋጥሙህ፣ ትክክለኛ የሆነ መፍትሄና መልስ እንዳላቸው መቼም እንዳትረሳ። በሕይወትህ ላይ ወሳኝና ትክክለኛ ጥያቄ ስትጠይቅ ትክክለኛውን መልስ ታገኛለህ። ከጉግል (Google) ድረ ገጽ ብዙ ነገር መማር እንችላለን። ጉግል ለምትጠይቀው በርካታ ጥያቄዎች መልስ አለው። አሁን ጉግልን በመክፈት፣ በሕይወትህ ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን እንዴት አድርገህ እንደምታደርግ፣ እንደምታስተካክልና እንደምትሰራ ብትጠይቅ፣ ትክክለኛውን መልስ ታገኛለህ። በዚህ ሰው ሰራሽ ድረ ገጽ ስለ ተለያዩ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ከቻልን፣ ፈጣሪን የሰጠንን አዕምሮ በመጠቀም፣ ለሁሉም የሕይወት ጥያቄዎቻችን መልስ ማግኘት እንደምንችል ታዲያ ምን መጠራጠር ያስፈልጋል?! አምስቱን የስሜት ህዋሶችህንና ምክንያታዊ አዕምሮህን ብቻ በመጠቀም፣ ለጥያቄዎችህ መልስ ለችግሮችህም መፍትሄ ከፈለግክ፣ የምትፈልገውን መፍትሄ ላታገኝ ትችላለህ። በመንፈሳዊ አካልህ ማሰብ ስትጀምር ግን፣ አሁን ላለህ ማንኛውም ችግርም ሆነ ጥያቄ፣ ከበቂ በላይ የሆነ አጥጋቢ መልስና መፍትሄ በእርግጠኝነት ታገኛለህ።

Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM

መልካም አዳር
824 viewsAbrsh DREAMS, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ