Get Mystery Box with random crypto!

AbrshDREAMS

የቴሌግራም ቻናል አርማ amazingviewss — AbrshDREAMS A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amazingviewss — AbrshDREAMS
የሰርጥ አድራሻ: @amazingviewss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.81K
የሰርጥ መግለጫ

Abrsh DREAMS - A Director, storyteller, cinematographer & Producer. and the other side Personal Development and spiritual coach. My vision is to make wisdom go viral in an accessible, relevant & practical way.

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-29 06:01:43 ተራ ነህ ወይንስ ድንቅ

የስኬት የመጀመሪያው ቁልፍ፣ አሁን ያለህበትን የዕድገት ደረጃ በትክክል መገንዝብ ነው። አቅምህን እየተጠቀምክ ያለህበት መንገድና እያገኘህ ያለኸው ውጤት በየትኛው ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት? በድንቅ ወይስ ተራ? በተለያዩ አጋጣሚዎች ያስተዋልኩት፣ በጣም ብዙ ሰው አሁን የሚያደርገው እንቅስቃሴ፣ በእንቅስቃሴው እያገኘ ያለው ውጤት እና ተዓምር መስራት የሚችል አቅሙን እየተጠቀመ ያለበት ደረጃ “ተራ” መሆኑን ነው። አብዛኛው ሰው ድንቅ አቅሙን ተራ በሆነ መንገድ በመጠቀም “ተራ ሰው” ይሆናል።

“ተራ ሰው ድንቅ የሆነ አቅሙን ተራ በሆነ መንገድ በመጠቀም፣ ተራ ውጤት ያገኛል!” ተራ ሰው፣ ተራ የሆነ ሀሳብ ያስባል፤ ተራ ስራ ይሰራል፤ በተራ ችግር ያማርራል፤ ተራ ገቢ ያገኛል፤ ተራ ዕድገት ያድጋል፤ በአጠቃላይ ተራ ሕይወት በመኖር ተራ ሞት ይሞታል። ከዚያም ተራ የቀብር ስነ-ስርዓት ይፈጸምለታል። ድንቅ የሆነ ሰው ግን ልክ እንደ ተራ ሰው በተለያዩ ችግሮች ቢፈተንም፣ ድንቅ ሀሳብ በማሰብ፣ ድንቅ ስራ በመስራት፣ ድንቅ መፍትሄ በመፈለግ፣ ድንቅ ገቢና ዕድገት በማግኘት፣ ድንቅ ሕይወት በመኖር፣ ድንቅ ሞት ይሞታል፤ ድንቅ የቀብር ስነ-ስርዓትም ይፈጸምለታል። አሁን ዋናው ቁም ነገር ተራ ወይም ድንቅ የቀብር ስነ-ስርዓት የሚፈፀምለት ሰው መሆን አይደለም። ዋናው ቁም ነገር፣ ተራ የሆነ የሕይወት ስርዓት እየመራህ አለመሆኑንና በድንቅ የሕይወት መስመር ላይ እየተጓዝክ መሆኑን ማረጋገጡ ነው።
1.8K viewsAbrsh DREAMS, 03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 08:01:11
A good environment for success should keep your senses stimulated and awake while you work on your goals, while not being too distracting. For example, one specific thing you could do is put plants or a fish tank in your office, gym, or workplace to surround yourself with nature more.

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
1.8K viewsAbrsh DREAMS, edited  05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 09:24:47
2.0K viewsAbrsh DREAMS, 06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 21:07:49 AbrshDREAMS pinned a photo
18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 21:06:57
ደስታ

እኔ የምፈልገውን መኪና፤ ቤት፤ ስገዛ ወይም ሕልሜን ሳሳካ እደሰታለሁ ብለህ እራስህን አትሸውድ፤ መኪና የገዛ ሕልሙን ያሳካ ሁሉ ደስተኛ አይደለም፤ ዋናው ነገር ደስተኝነት ሕልም ሲሳካ ወይም የምትፈልገውን ስታገኝ ሳይሆን፤ መጀመሪያ ምንም ሳይኖርህ ባለህ ነገር ለመደሰት ስትወስን ነው በራሥህ የውስጥ ሠላም የምትደሰት ከሆነ፤ የውጭው ረብሻና ጫጫታ ምንም አይመስልህም ዞር ብለህ ብታይ ሕይወት እጅግ በጣም ውብ ናት፤ አሁን ባለህ ስትደሰት ሌላው ቀስስስስስ እያለ ይመጣል ደስታ ደግሞ በነገሮች መገጣጠም የሚመጣ ሳይሆን ደስታህ የውስጥህ ምርጫ ውጤት ነው። ስለዚህ ደስተኛ ሁን!


ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
TELEGRAM
2.7K viewsAbrsh DREAMS, edited  18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:22:56
2.4K viewsAbrsh DREAMS, 18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 10:35:49
"ዛሬ የሞት አልጋችሁ ላይ ብትሆኑ ኖሮ፤ መጨረሻ ቀናችሁ ቢሆን ኖሮ ..  እስከአሁን የኖራችሁት ህይወት በቂ ይሆን ነበር ወይ???"

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
TELEGRAM
2.6K viewsAbrsh DREAMS, edited  07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 10:14:56
መታገስ

የዘራኸው ዘር ፍሬ አፍርቶ ከመብቀሉ በፊት መሬት ውስጥ ሥር በመልቀቅ እድገቱን ይጀምራል። አብዛኞቻችን ግን እድገቱን ለማየት ትዕግሥት ስለሌለን የዘራሁት ዘር አያፈራም ብለን ሌላ ለመትከል ድጋሚ እንሞክራለን ፤ በዚህ መሐል ያማረ ፍሬ እናጣና እርካታ እናጣበታለን :: ማንኛውም ዘር ከመብቀሉ በፊት የማይታይ የውስጥ ለውስጥ እድገት አለው፤ ከታገስክ ፍሬውን ማግኘትህ አይቀርም።ሕልምም እንደዚሁ ነው፤ ውጤቱን እስከምታገኝ ድረስ የውስጥ ለውስጥ ግንባታህን ቀጥል።ከታገስክ የዘራኸውን ዘር ማጨድህ ግድ ነው!


ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
2.4K viewsAbrsh DREAMS, edited  07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 06:34:03 መቼም እንዳትረሳው!

ትምህርት ቤት የተለያዩ እውቀቶችን ያስተምሩናል በመቀጠል ምን ያህል እንዳወቅን ለመረዳት ይፈትኑናል!

በሕይወት ግን መጀመርያ ትፈተናለህ ከዚያ በፈተናህ መረዳትን ታገኛለህ!

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
2.2K viewsAbrsh DREAMS, 03:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 06:01:49
ምን እየጠበክ ነው?

ቤተልሔም ጥላሁን ትባላለች። አነስተኛ ደመዎዝ እየተከፈላት ተቀጥራ ትሰራበት ከነበረው መስሪያ ቤት፣ “ለስራው ብቁ አይደለሽም” በመባል ትሰናበታለች። ሆኖም ቤተልሔም ትልቅ ሕልም ስለነበራት፣ ለአለቃዋ “ልጆችህንና የልጅ ልጆችህን የሚቀጥር ድርጅት እከፍታለው” በማለት ከድርጅቱ ትወጣለች። ከዚያም የተጣሉ የመኪና ጎማዎችን በመሰብሰብ፣ በተለምዶ “ጋዴ” ወይም “በረባሶ” በመባል የሚታወቀውን ጫማ በልዩ ሁኔታ መስራት ጀመረች። ከዚያ የበረባሶ ጫማ ስራ በመነሳት አሁን ላለችበት የስኬት ደረጃ በቅታለች።
በአሁን ሰዓት ቤተልሔም “ሶል ሬብልስ” የሚባል ትልቅ የጫማ ፋብሪካ በመክፈት፣ ወደ 30 የሚሆኑ አገራት ላይ ምርቶቿን በማከፋፈል፣ ጫማዎቿን ለዓለም አስተዋውቃለች። ከዚህም አልፎ በአፍሪካ ካሉ አምስት፣ እንዲሁም በዓለም ላይ ካሉ ሃያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል አንዷ ለመሆን በቅታለች። በተጨማሪም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2017 ዓ.ም. “የአፍሪካ የሴቶች መሪ” በሚል ዘርፍ ልዩ ሽልማት አግኝታለች። በአንድ ወቅት ግን፣ ቤተልሔም ልክ እንደ አብዛኛው ሰው ሁሉ በትንሽ ደመዎዝ እና ስራ በመርካት፣ የተለመደ ኑሮዋን እየገፋች ነበር። አንተስ ትልቁ ሕልምሕን ለመኖር ምን እየጠበክ ነው?


ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM
2.4K viewsAbrsh DREAMS, 03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ