Get Mystery Box with random crypto!

መሀይም ስለሆንን ነው የፈለግነውን ውጤት የማናገኘው! የምትፈልገውን ውጤት የምታገኝበትን ምስጢር | AbrshDREAMS

መሀይም ስለሆንን ነው የፈለግነውን ውጤት የማናገኘው!

የምትፈልገውን ውጤት የምታገኝበትን ምስጢር ካላወቅክ፣ የፈለግከውን ውጤት ማግኘት ይከብድሀል። አስቀድመን ስለመሀይምነት ትርጉም ስንነጋገር እንዳነሳነው፣ መሀይምነት ማለት፣ ነገሮችን የማከናወኛ ምስጢርን አለማወቅ ነው። በዚህም በርካታ ሰዎች መሀይም ናቸው። ቀለም ለቆጠርነው እንኳ፣ እንዴት አድርገን ትልቅ ሕልም በማስቀመጥ፣ ሕይወታችንን መቀየር እንዳለብን፣ ትምህርት ቤቶቻችን አላስተማሩንም። ሕልሙን የሚያሳካበትን ምስጢር ያላወቀ ሰው፣ ስለ ትልቅ ሕልሙና ሕልሙን ማሳካት ስለሚችልበት መንገድ ሲያስብ ይጠራጠራል፤ ይፈራል፤ ይጨነቃል፤ ደግሞም ተስፋ ይቆርጣል። ሕልሙን የሚያሳካበትን ምስጢር ተምሮ መሀይምነቱን ሲያሸንፍ ግን፣ የማንንም ሰው መብት ሳይነካ፣ ትልቁን ሕልሙን በማሳካት የሚፈልገውን ሕይወት መኖር ይጀምራል።

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM