Get Mystery Box with random crypto!

በአይንህ አላየኸውም ማለት የለም ማለት አይደለም! ምናብ በሕይወታችን የምንፈልገውን ማንኛውንም ነ | AbrshDREAMS

በአይንህ አላየኸውም ማለት የለም ማለት አይደለም!

ምናብ በሕይወታችን የምንፈልገውን ማንኛውንም ነገር በሀሳብ፣ በምስልና በስሜት የምናመነጭበት፣ የምንቀርጽበትና የምንፈጥርበት ልዩ የአዕምሮ መሣሪያ ነው። ይህ መሣሪያ በሕይወትህ ላይ ለውጥ እንድታመጣ፣ በትክክል ስትጠቀምበት ደግሞ ተዓምር እንድትፈጥር ያስችልሀል።

አንድ ሰው ምናቡን በትክክል ሲጠቀም፣ ኪሳራን አሸንፎ በቀላሉ ትርፍ ማግኘት ይጀምራል። ምናባችንን በትክክል ስንጠቀምበት፣ ችግር ውስጥ ሆነን በአምስቱ የስሜት ህዋሶቻችን ያልታየን “መፍትሄ” በምናባዊ መንገድ ማየት እንችላለን። ለችግራችን የሚሆነውን መፍትሄ በዐይናችን አላየነውም ወይም በጆሯችን አልሰማነውም ማለት፣ ችግራችን ትክክለኛ መፍትሄ የለውም ማለት አይደለም።

በዐይንህ አላየህም ማለት፣ ምንም ነገር የለም ማለት ወይም ውስጣዊ በሆነው ምናብ የአዕምሮ መሣሪያህ አታይም ማለት አይደለም። ገንዘብ ስለማግኘትም ስናወራ፣ ልትረዳው የሚገባህ ዋናው ቁም ነገር የምትፈልገውን ስራ ለመጀመር የሚያስፈልግህን ገንዝብ በዐይንህ አላየኸውም ማለት፣ ገንዘቡ የለም ማለት አለመሆኑን ነው። ማንኛውንም ነገር በትክክለኛው መንገድ ስትፈልግ፣ የሚያስፈልግህን ነገር ሁሉ ማየት ከዚያም ማግኘት ትጀምራለህ። የሚያስፈልጉህ ነገሮች በአምስቱ የስሜት ህዋሶችህ ባይታዩህም፣ ማየት ግን ትችላለህ፤ በምኔ ብትል፣ በምናብህ። የሚያስፈልግህን ነገር በምናብህ ካየኸው፣ በአዕምሮህ ታስበዋለህ። በአዕምሮህ ስታስበው ደግሞ በልብህ ታምነዋለህ። ከዚያም በአምስቱ የስሜት ህዋሶችህ ሊጨበጥ ወደሚችል ነገር ትቀይረዋለህ። ይህንን ሀሳብ በትክክል ካልተረዳኸው ግን፣ የማይሆን ነገር ብቻ መስሎ ሊታይህ ይችላል።

ዛሬን እንኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM