Get Mystery Box with random crypto!

#Ethiopia ተስፋ_ጽናት_ደስታ!! 'ለመኖር ሁለት ፐርሰንት ዕድል ብቻ እንዳለኝ በሀኪሞች ተነ | AbrshDREAMS

#Ethiopia ተስፋ_ጽናት_ደስታ!!

"ለመኖር ሁለት ፐርሰንት ዕድል ብቻ እንዳለኝ በሀኪሞች ተነግሮኛል:: ነገር ግን ሁለት ፐርሰንት ማለት ዜሮ ማለት አይደለም:: ሁለት ፐርሰንት ማለት የሆነ ነገር እንደሆነ ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ!!"

"ደስተኛ ልትሆን ለመወሰን ሕይወት ከዚህ በፊት ከነበረው ከባድነት ቀላል እስኪሆን መጠበቅ የለብህም!!"
____

ወደ American Got Talent የሚመጡ ተወዳዳሪዎች መድረኩን ከመርገጣቸው በፊት እጅግ ከሚጨነቁባቸው ነገሮች ዋናው "ሳይመን ምን ይለን ይሆን!?" የሚል ይሆንና ትንሽ ዘና ካሉ "ሳይመን 'yes’ ይሰጠን ይሆን!? የሚል ይሆናል:: ከሳይመን ካውል አፍ 'yes’ ከመቀበል አልፎ ከአይኖቹ እንባ እንዲወጣ ማድረግ ግን እጅግ ከባድ ነው:: ከሁሉ በላይ ከባዱ ግን የሳይመን እጆች ውዱን Golden Buzzer  እንዲጭኑ ማድረግ ነው::

አንዲት ሰውነቷ ገርጥቶ ልትቀነጠስ የደረሰች ኮሳሳ ተወዳዳሪ ወደ መድረክ መጣች:: የዕለቱ ተረኛ ጠያቂ ሀዋርድ ነበር:: "እንዴት ነሽ!?" አላት:: በጣም ደስተኛ ነኝ:: እዚህ በመሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል" አለች:: ሁሉም ተወዳዳሪ የሚለው ስለሆነ አይደንቅም:: አራቱም ዳኞች ከተለመደው ያልተለየ ደስታቸውን ገለፁ::

ሀዋርድ ቀጠለና "ምንድነው የሚታቀርቢልን!?" አላት:: እሷም "It is Ok” የሚል የራሴን ስራ ነው" አለች:: ሁላቸውን ባንድ አፍ "አዎ! ሁሉ ደህና ነው" አሉ:: ግን ይህም አይገርምም:: ሀዋርድ ቀጠለና "ግን ሁሉ ደህና ነው ስለምንድነው?" ሲላት ከካንሰር ጋር ስትታገል የኖረችውን የሕይወት ውጣውረድ ነገረቻቸው:: የሁሉም ፊት ጨለማ:: የእሷ ፊት ግን የደስታ ጨረር ከመርጨት አላቆመም:: ኮምጨጭ አለችና "አረ ሁሉ ደህና ነው:: እኔ ሰላም ነኝ" አለቻቸው::

የዚያኔም ባለስል አስተያየቱ ሳይመን "አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? አሁን እንዴት ነሽ!?" አላት:: እሷም "የመጨረሻውን ምርመራ ሳደርግ በሳንባዬ: ጣፊያዬና ጉበቴ ላይ ካንሰር እንዳለ ተነግሮኛል" ስትል ሳይመን በድንጋጤ አስፈሪ ጭጋግ ውስጥ ሆኖ "ዋው" ሲል ሀዋርድ ቀጠለና "ስለዚህ ደህና አይደለሽም ማለት ነዋ" አላት:: "በርግጥ በሁሉም መልኩ አይደለም" ስትል ሀዋርድ ተገርሞ "ማንም ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሽ እስከማያውቅ ድረስ ለሌሎች የደስታ ጨረር የሚረጭ አስገራሚ ፈገግታ አለሽ" ብሎ አሞካሻት!!

Nightbird የሕይወት ታሪኳን አሳማኝ በሆነ መልኩ በዜማ ካቀረበች በኅላ የደኞች ውሳኔ የሚሰጥበት  ሰአት ደረሰ:: ሁሉም ሳግ እየተናነቃቸው በስሜት የተሞሉ አዎንታዊ አስተያየቶችን ሰጡ:: ተራው ሲደርስ ተጠባቂው ሳይመን ሌሎች ዳኞች በሰጡት አስተያየት ሙሉ በሙሉ እንደሚስማማ ገልፆ ተጨማሪ ስሜቱን እንዴት መግለጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ሲያመነታ ሳለ መኻል ላይ አቋርጣ በከፍተኛ ፈገግታ በመሞላት "ደስተኛ ልትሆን ለመወሰን ሕይወት ከዚህ በፊት ከነበረው ከባድነት ቀላል እስኪሆን መጠበቅ የለብህም" የሚል እጅግ አስገራሚ አስተያየት ሰነዘረች::

ያ ንግግር ብዙዎችን ያስገረመ ቢሆንም ሳይመንን ለደቂቃዎች አፍዝዞ እንባ ከሁለቱን ዓይኖቹ ፈሰሱ:: ከፊቱ ያለውን የመጠጥ ዕቃ አነሳና ተጎንጭቶ ሳግና እንባውን አወራረደ:: በመቀጠልም  አስተያየቱን ሰነዘረ:- "በዚህ ዓመት ታላላቅ ችሎታ ያለቸውን ሰዎች  አይቻለሁ:: ሆኖም ላንቺ 'yes’ አልሰጥም" ሲል ከዳኞች እስከ ታደሚ በቅሬታ አጉተመተሙ:: ሳይመን አልጨረሰም ነበር:: "የሚሰጥሽ ከ'yes’ የተሻለ ነገር ነው" አለና እጆቹ ወደ Golden Buzzer ሄደ:: አደራሹ በከፍተኛ ደስታ ሲያስተጋባ Nightbird የወርቁ ብናኝ ላይ በደስታ እንባ ተደፋች!!
—-------
Jane Marczewiski (በቅጽል ስሟ Nightbird) በ2017 ባደረገችው ምርመራ ደረጃ ሶስት የጡት ካንሰር በሽተኛ መሆኗ ታውቆ ከዚያ በኅላ በምድር የሚኖራት ዕድሜ ስድስት ወራት ብቻ እንደሆነ ተነገሯት ከሕይወት ጋር ትግሏን ቀጠለች:: ትንሽ ቆይቶ በ2018 ከካንሰር ነፃ መሆኗ ቢነገራትም መልካም ዜናው ብዙም አልቆየም:: እንደገና በሽታው እንዳለባት ተነግሯት ትግሏን ቀጠለች:: የሕይወት ትግሏን ከጎኗ ሆኖ ማገዝ የሚጠበቅበት የአምስት ዓመት የትዳር አጋሯ ጥሏት ኮበለለ::

ይቺ ምስኪን: ብቸኛ ፅኑ ሴት ናት ሰኔ 10 2020 American Got Talent መድረክ ላይ ቆማ ሳለ ሀዋርድ "እዚህ ከማንጋር መጣሽ?" ሲላት (አባባሉ "የድል ደስታሽን ከማን ጋር ሊታጣጥሚ ነው?" የሚል ድምፀት አለው) "ብቻዬን ነኝ" ብላ የመለሰችው እና ከሳይመን Golden Buzzer በኅላ ከአዳራሹ ብቻዋን እየዘለለች የወጣችው!!

በዚህ የኮቪድ ውጥንቅጥ ወቅት ለብዙዎች የደስታ ምስክር እንደሆነች በማመን "you are the voice we all need to hear this year” የሚል አስተያየት ከሳይምን የተሰጣት ይቺ ብርቱ ሴት ከBBC ጋር በነበራት ቃለ መጠይቅ "ወደ ኅላ የሚያስቀርብኝ መልካም ነገሮች የሉትምና እግዚአብሔር የሆነ ጊዜ ላይ ቅጽበታዊ ፈውስ እንደሚያመጣ አምናለሁ" ስትል ተናግራለች::

May 3 በለጠፈችው ብሎጏ:- "እግዚአብሔር መጀመሪያ ለእኛ ራሱን ባስተዋወቀበት ወቅት (ዘፍጥረት) ያሳየንን ነገር ረስተን ይሆናል:: አቧራ ላይ እየዳሀ ነበር የቀረበን:: እንዴት መተንፈስ እንዳለብን በማናውቅበት ጊዜ ሳንባችንን በአየር ሞልቶ መተንፈስን አስተማረን" ብላለች!!

በሌላ ጽሑፏ ሕመሟን በተመለከት "እግዚአብሔር አብዛኛውን ጊዜ ወሳጅ ሳይሆን ሰጪ ነው:: ከመውሰድ ይልቅ ይጨምራል" ትላለች:: “ጨለማዬን አልወሰደውም ግን ብርሃን ጨመረልኝ:: ብቸኝነቴን አልፈወሰውም ግን እርሱ ይበልጥ ቀረበኝ" ትላለች:: በሕመሟ ተስፋዋ ይጨምራል እንጂ ተስፋ ቢስ አይደለችም:: በመሆኑም  "በህመሜ ተስፋ የማደርገው የእግዚአብሔርን ቅርበት በዚያ ስላወቅሁ ነው" ትላለች::

"እግዚአብሔር ትሁት ሆኖ ወደ እኛ የቀረበበት ከመስቀል የተሻለ ስፍራ የለም:: በኃጢአትና በሽታ ወደ ተመታው ዓለም  እግዚአብሔር ሰው ሆኖ መጣ::  ይህም እግዚአብሔር በሙሉ ፈቃድና ትህትና የኃጢአታችን ምትክ ሆኖ ሊቤዥን ወደ መስቀል ሄደ" ትለናለች!!

በመከራና ስቃይ ውስጥ ስናልፍ ልኖረን የተገባው እምነት: ተስፋና ፅናት ይኼ ነው:: የመስቀሉ ስቁዩ ኢየሱስ ስቃይና ህመማችን ይገባዋል:: የምንጠብቀው ፍፁም ቤዛችንም እሱ ነው:: አንድ ቀን ፈጽሞ የማይታመምና የማይሰቃይ አካል እስክንለብስ አሁን ከብዶን ብንቃትትም ተስፋ ቆርጠን ግን ወደኅላ አናፈገፍግም!!

መልካምና የሚያንፁ አስተማሪ ጽሁፎችን  ለተከታታይ ቀናቶች ሼር አደርጋችኋለሁ። እናተም በደስታ ለሌሎች ማካፈላችሁን አትርሱ።
ቻናሉንም ሼር ማድረጋችሁን አትዘንጉ።
----
አንድ ሰው ቢያንስ ለ #5 ሰዎች ሼር ያድርጉ።

==========||==============


____

ዛሬን ኑር!
የእናንተው ቤተሰብ AbrshDREAMS
Folow Us
YOUTUBE
INSTAGRAM
FACEBOOK
TELEGRAM