2023-02-05 16:32:08
እይታ
ዘፍ 13፥14 “ ሎጥ ከተለየው በኋላም እግዚአብሔር አብራምን አለው። ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ፤ 15 ፤ የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና። 16 ፤ ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ የምድርን አሸዋን ይቈጥር ዘንድ የሚችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈጠራል። 17 ፤ ተነሣ በምድር በርዝመትዋም በስፋትዋም ሂድ እርስዋን ለአንተ እሰጣለሁና። 18 ፤ አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው በመምሬ የአድባር ዛፍ ተቀመጠ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ።
ስንቶቻችን ነን መለየት አቅቶን ተደባልከን ያለን አብርሃም የእግዚኣብሄርን ምሪት ለማግኘት መለየት ነበረበት።
በእግዚአብሄር መለኮታዊ ጥሪ ከሀገሩና ከዘመዱ ተለይቶ የወጣው አብርሃም
የሚወርሰው የምድር ስፋት የሚለካው “ባየው” ልክ ነበር፡፡ አብርሃም ትወርሳለህ
የተባለው አንድ ጂኦግራፊካዊ ምድር ብቻ ነበር፡፡
በአዲስ ኪዳን የሰማያዊ ጥሪ ተካፋዮች ለሆነው ለእኛ ግን አሁን የሚሰጠን
ጂኦግራፊካዊ ምድር ወይም አንድ የመሬት ርስት ሳይሆን ነገር ግን የሚሰጠን ወይንም
ሌንወርሰው ያለ ርስት ጌታ በመስቀለ አማካኝነት ያስገኘልንን በዚህም ቁሳዊ አለም
ሊገለጡ የሚችሉት መንፈሳዊ ርስቶችን ነው፡፡
የእነዚን መንፈሳዊ ርስቶች የሚገኙበትና የሚወርሱበት ብቸኛ መንገድ የልቦናችን
ዓይኖች ሲበሩና በእምነት ዓይን ሲታዩ ነው፡፡
በክርስቶስ የመስቀለ ስራ (በሞቱና በትንሳኤው) የተገኙት እነዚህ መንፈሳዊ
በረከቶች በልቦናው ዓይኑ ያየ ይወርሳቸዋሌ፡፡
በመፅሐፍ ቅዱስ የመውረስ ህግ አለ፡፡ ያም “አምነህ ብታይ” የሚል ህግ ነው፡፡
ኤልሳ ሁለት እጥፍ በአንተ ላይ ያለውን መንፈስ በማለት ሲጠይቅ? ያገኝ ዘንድ በትጋት የኤሌያስን እንቅስቃሴ ማየት ነበረበት፡፡
ኤሌያስ አለው “ብታይ” ይሆንልሀል አለው፡፡ (2 ነገስት 2፤10)
ለአብርሃም የምታያትን ምድር ሁለ ለአንተ እሰጣለሁ ተባለ፡፡ በሌላ አባባል
አብርሃም ሊወርሰው የሚችለው ባየው ልክ ወይንም የአብርሃም የርስት ስፋት ያየውን
ያህል ነው፡፡
እኛ የዘላለም ሕይወት ያገኘነውና የዳነው ክርስቶስ በከፈለው ዋጋ ቢሆንም ስለ ደህንነት በቃል
አማካኝነት በውስጣችን ስለበራልንና ውስጣዊ ዓይናችን ይህንን እውነት ወይም ቃል
ስለተመለከተ ነው፡፡
ስለ ደህንነት በውስጥ ዓይናች ያን መረዳት ባናይ ዛሬ ባልዳንን ነበር፡፡
ልክ እንደዚሁ በቃል አማካኝነት የሕሊናችን ወይም የልቦናችን ዓይኖች ሲበሩ ብዙ እስከ ዛሬ ያላስተዋልናቸው
መንፈሳዊ ርስቶችን ከቃሉ እናገኛለን። ከእኛ የሚጠበከው በመጸሃፍ ቅዱስ ርዝመትና ስፋት እይታችንን አስተካክለን መራመድ ብቻ ነው።
ይቀጥላል . . .
ጸጋና ሰላም ይብዛልን!!!!
90 viewsErmi, 13:32