2023-02-20 12:54:56
#ዳዊት በፍልስጥኤማውያን ምድር!
(1 ሳሙ 27 )
------------
1 ዳዊትም በልቡ፦ አንድ ቀን በሳኦል እጅ እጠፋለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሽ በቀር የሚሻለኝ የለም፤ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፥ እንዲሁም ከእጁ እድናለሁ አለ።
2 ዳዊትም ከእርሱም ጋር የነበሩት ስድስቱ መቶ ሰዎች ተነሥተው ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አንኩስ አለፉ።
☞ አካሄዱን ሁሉ በማስተዋል ያደርግ የነበረውና እግዚአብሔር እንደልቤ ያለው ዳዊት ከሳኦል እጅ ለመዳን የእግዚአብሔርና የእግዚአብሔር ህዝብ ጠላት ወደ ሆነው ወደ ፍልስጤም መሸሹ ዳዊት ሙሉ በሙሉ ዓይንኑን ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ማንሳቱና በራሱ መንገድ መሄዱን የሚገልጥ ነው።
☞ ታማኙ እግዚአብሔር ግን ዳዊት በምድረበዳ እንኳን ሳይቀር ለሳኦል እጅ አሳልፎ አልሰጠውም ነበር!
" ዳዊትም በምድረ በዳ በአምባ ውስጥ ይኖር ነበር፥ ከዚፍ ምድረ በዳም ባለው በተራራማው አገር ተቀመጠ፤ ሳኦልም ሁልጊዜ ይፈልገው ነበር፥ እግዚአብሔር ግን በእጁ አሳልፎ አልሰጠውም።"
(1 ሳሙ 23: 14)
☞ ዳዊት በራሱ መንገድ በሄደ ጊዜ ወደ ፍልስጤኤም ምድር መሸሽ ብቻ ሳይሆን ለፍልስጤኤም ንጉሥ ራሱን #ባሪያ እስክያደረግ ድረስና ከፍልስጤኤም ጋር በመተባበር ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር ለመዋጋት እስኪደፍር ድረስ #ውድቀቱ ተገለጠ(1 ሳሙ 28 ፥1–2)።
☞ እግዚአብሔር ግን ባሪያውን ዳዊት እንደገና በምሕረቱ ተገናኘው የዳዊት ልብ #በእግዚአበሔር #በረታ!(1ሳሙ 30፥ 6) እግዚአብሔርም በጠላቶቹ ላይ ድልን ሰጠው ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለዳዊት በመንገዱ ሁሉ ድልን ሰጠው ፣በእስራኤል ሁሉ ላይ ይነግሥ ዘንድና በእስራኤል ላይ ፍርድንና ጽድቅ ያደርግ ዘንድ እ/ር ምህረቱንና ጸጋውን አበዛለት!
(2 ሳሙ 8 )
------------
14 በኤዶምያስ ሁሉ ጭፍሮች አኖረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ እግዚአብሔርም ዳዊት በሚሄድበት ሁሉ ድልን ሰጠው።
15 ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ዳዊትም ለሕዝቡ ሁሉ ፍርድንና ጽድቅን አደረገላቸው።
☞ #በክርስቶስ ኢየሱስ ያላችሁ ቅዱሳን ሁሉ ሁሌም ቢሆን የገዛ መንገዶቻችን በኃፍረትና በውድቀት የተሞሉ ናቸው ከዚያም ባሻገር ትናንትና ስንወዳቸው በነበሩ ወንድሞችና እህቶች ላይ ጠላት ሆነን እንነሳለን! እግዚአብሔር ግን የእንደገና አምላክ ነው ፥ በእውነት ከተመለሥን ከውድቀታችን ሊያነሣን #የታመነ ነው።
☞ ሁሉ ጊዜ የእግዚአብሔር ሙላት የሆነውን ጌታ ኢየሱስ እንድንመለከት እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልን! አሜን።
63 viewsYemane H/mariam, 09:54