2023-03-21 17:21:47
እይታ 5
ሰላም ለናንተ ይሁን! እንደምን አላችሁ?
ክፍል 5 ስጀምር ክፍል 4 ካስተዋወቅኳችሁ ልጀምር። ይህ ሰው እይታውን ከማስፋት የማይቦዝን ሰው ነው።
ሐዋ 18፤24-25)24 በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ ነገር አዋቂ የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን ወረደ፤ እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ ነበረ።
25 እርሱ የጌታን መንገድ የተማረ ነበረ፥ የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ በመንፈስ ሲቃጠል ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበር።
26 እርሱም በምኵራብ ገልጦ ይናገር ጀመር። ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ፥ ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት።
27 እርሱም ወደ አካይያ ማለፍ በፈቀደ ጊዜ፥ ወንድሞቹ አጸናኑት፥ ይቀበሉትም ዘንድ ወደ ደቀ መዛሙርት ጻፉለት፤ በደረሰም ጊዜ አምነው የነበሩትን በጸጋ እጅግ ይጠቅማቸው ነበር፤
28 ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ከመጻሕፍት እየገለጠ ለአይሁድ በሁሉ ፊት በጽኑ ያስረዳቸው ነበርና።
ይህ በመጽሐፍ እውቀት የበረታ የጌታን መንገድ የተማረ ስለ ጌታም የሚናገር
ሰው ነበር፡፡ አጵልስ ነገር ግን በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ የተረጋገጡት እርሱ ግን
ያላያቸው ሌሎች መንፈሳዊ እውነቶች ነበሩ፡፡ ስለዚህ ይሄ ሰው የበለጠ ዓይኑ
ሊከፈትለት ይገባ ነበርና ጌታ ሰው ላከለት፡
“ጵርስቅላና አቂላም በሰሙ ጊዜ ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ
በትክክል ገለጡለት” ምንም አስተማስሪ ቢሆን እራሱን በትክክለኛ ስፍራ ያስቀመጠ ሰው ነበር።
ይህን ሰው ስንመለከት እራሳችንን እንዴት እየተመለከትን ይሆን? ? ?
ገለጡለት የሚለውን ቃል አጽንኦት እንስጠውና ፡- ይህ ማለት አጵውሎስ
ያልተገለጹለት እውነት ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሁላችንም እንዲሁ ነን ገና ያልደረስንበት ብዙ ነገር እንዳለ አምናለው። ስለዚህ እነዚህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች
የአጵውሎስን መረዳት ቃሉን ፍቺ በመግለጥ መረዳቱን ጨመሩለት፡፡ የውስጥ
ዓይኖቹንም ከፈቱለት፡፡ የአጵውሎስም ዓይኖች ፈጽሞ ጤናማ ሆነው በሩ፡፡
ይሄ ሰው የመረዳቱን ሙላትና መገለጥን ያገኘው ከነዚህ ሰዎች ነበር፡፡ ከዚያ
በኋላ አጵዎሎስ ቤተክርስቲያንን እጅግ የሚጠቅም ሰው ሆነ፡፡ የጌታ ቃል በይበልጥ ጊዜ ሰጥተን በማስተዋል ስንመለከት እውነቱንም በቅንነት የሚያገለገሉትን በማስተዋል ስንሰማቸውና ስንቀበል ለኛ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ሆነ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም ሰራተኛ መሆን እንችላለን።
“እርሱም ወደ አካይያ ማለፍ በፈቀደ ጊዜ ወንድሞቹ አጽናኑት ይቀበሉትም ዘንድ
ወደ ደቀመዛሙራት ጻፉለት፡፡ በደረሰም ጊዜ አምነው የነበሩትን በጸጋ እጅግ ይጠቅማቸው
ነበር፡፡ እይታውን ሰፋ በማድረጉ እና መጨመር እንዲሁም እውነትን በመከተሉ ለውነትም ልቡን በመክፈቱ ላመኑት አንኳን ጠቃሚ ሰው ሆነ።
እናውካለን በሚሉት መካከል እንኳን የጌታን እውነት ከመጻህፍት አንጻር ለመናገር መኮም ተችሎታል።
የኛ ጊዜ ከባድ ነው! በቀላሉ የምናልፍበት ዘመን ላይ አይደለንም። ስለዚህ እይታችንን እናስፍ። ጌታ ይረዳናል! . . . ይቀጥላል
ጸጋና ሰላም ይብዛልን!!!
90 viewsErmi, 14:21