2023-03-07 08:49:37
እይታ 4
ይህን ክፍል ቀጥዬ ስጽፍ ሁላችንም በትጋት እንደሆንን ተስፋ አደርጋለው። ምክንያቱም የምንተኛበት ጊዜ ላይ አይደለንም።
የብሉይ ኪዲን መዝሙረኛ እንኳን ይህን በመረዳት እንዲህ አለ “ጠላቴ
አሸነፍሁት እንዳይል የሚያሥጨንቁኝ እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው ልሞትም
እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ” (መዝ 131፤9)
በኤፌሶን 6፥ 11 የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።
12 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። የተጠቀሱት ጠላቶች ሊያሸንፉህ የሚችሉትና በአንተም መናወጥ
ደስ የሚላቸው የውስጥህ ዓይኖች ያንቀላፉ እለት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ያ እንዳይሆን
እንደ መዝሙረኛው ዘወትር ዓይኖቼን አብራ ጠላቴ እንዳያሸንፈኝ የቃልህን ፍቺ
አብራልኝ ከህግህም ታምራት እንዳይ (መዝ 119፤18) ብለን ልንጸልይ ያስፈልጋል::
ዓይኖችህ በቃል ውስጥ ያዩትን የእውነት ልክ ያህል ነው ነፃነትህ! የነፃነትህ ልክ
ያወቅከውን ወይንም የተረዳኸውን የእውነት ቃል ብዛት ያህል ነው! በውስጥህ እንዳለው
የቃል ክምችት መጠን ያህል የውጭውም ነፃነትህ የዚያኑ ያህል ነው! (ዮሐ 8፥ 31 ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ። እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ 32 እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። ጌታ የተመሰገነ ይሁን!
የውስጥ ዓይኖች የሚበሩት እኛ ስንጸልይ የጌታም መንፈስ ቃሉን ሲያበራልን
ነውና ስለዚህ ከእግዚአብሔር የሆነ የማስተማር ፡ ቃሉንም የመግለጥ
በቤተክርስቲያን ያለውን አገልግሎት ለማገልገል በውስጣችን ቃሉ ሊኖር ይገባሌ፡፡ ያስተምሯቸው ዘንድ መልካሙን መንፈስ ስጣቸው
የተባለው ለዚህ ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር ቃል በሆነ ትምህርት የውስጥ ዓይን ይከፈታል።
ርስቱንም ማየት ያኔ ይቻላል፡፡
በሐዋሪያት ስራ መጽሐፍ ላይ በጥቂቱ ዓይኑ ተከፍቶለት በዚያ በተረዳው ጥቂት
ብርሃን ሲተጋ የነበረው የአጵውሎስ ህይወት ልቤን ይነካዋል፡፡
ያ ሰው ጥቂት ብርሃን ነበረው፡፡ በዚያ ብርሃን ሲተጋ ጌታ ጥማቱን አየና
የውስጡ ዓይኖችን ሙሉ በሙሉ ከፈተለት፡፡ ጌታ የአጵውሎስን የመረዳት ባለጸግነት የጨመረለት እንደዚሁም እሱ ያላየውን ነገር ግን በጌታ ትንሳኤ የተረጋገጠውን ርስቱን ያሳየው በትምህርት በመትጋቱ አማካኝነት ነበር፡፡
የአጵውሎስ ዓይኖች ከፊት ይልቅ በበለጠ ይበሩለት ዘንድ በዚህ የትምህርት
ቅባት የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ወደ ሕይወቱ ላከለት፡፡ አጵውሎስም ትሁት ሰው ነበርና
ዝቅ ብል ተማረ፡፡
አኛስ ዛሬ ምን ላይ እንሆን? . . . ይቀጥላል
ጸጋና ሰላም ይብዛልን!!!!
29 viewsErmi, 05:49