2023-01-31 09:40:04
የአዳም ልጆች
ዘፍ11:1 ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች። 2 ፤ ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ። 3 ፤ እርስ በርሳቸውም። ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፋት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው። 4 ፤ እንዲህም። ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ።
5 ፤ እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። 6 ፤ እግዚአብሔርም አለ። እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።
እዚህ ክፍል ውስጥ እናንተ ብዙ ለራሳቹ የሚሆን ትምህርት ታገኙበት ይሆናል። ግን እኔ ኣንድ ነገር ላጋራቹ ወደድኩ። እዚህ ክፍል ውስጥ
የአዳም ልጆች የሚል እንመለከታለን። እግዚኣብሄር ለምን የኖህ ልጆች አላለም? ለምን የሴም የካም የያፌት ልጆች አላለም?
1ጢሞ2፥13 አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች።
14 የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤
መጸሃፍት እንደሚያሳዩን አዳም ጋር መስማማት ነው እንጂ መታለል አይታይም። እዚህ ጋር እነዚህ ሰዎች ሲስማሙ ነው የምናገኛቸው ሲስማሙ ነው። ስምምነታቸው ልክ አንደ አዳም የራሳቸውን ጥቅምና ፍላጎትን የጠበቀ ነው እንጂ የእግዚኣብሄርን ፍላጎትም ሆነ መሻት የሌለበት መሆኑን እንመለከታለን። ስለዚህ ይህ አይደል ያባቱ ልጅ። የአባታቸው ልጆች ስለሆኑ ስለ ስማቸው እና ስለ ክብራቸው የሚያስቡ እንጂ ስለ እግዚኣብሄር የሚያስቡ አይመስሉም።
የሆነው ሆኖ
እኛስ ምን ላይ ነን ?
በምን አይነትስ ሃሳብና ስምምነት ውስጥ እንገኝ ይሆን? እግዚኣብሄር ሲጎበኘን ለፍርድ የሚጋብዝ ነው ወይስ ለበረከት በደስታ እጁን የሚዘረጋበት? ያለንበትን እኛው ስለምናውቅ ፍርዱን ለራሳችን ልተው። እራሳችንን አይተን ለመወሰን ግን ጊዜ አንፍጅ ምክንያቱም የጌታ አይኖች ሁሌም ወደኛ ናቸው። እራሳችንን አውቀን መበተን ሳይሆን ንስሃ ገብተብ እራሳችንን እናስተካክል። እና የሁለተናው አዳም ልጆች ነን።
ምዕራፍ 8፥1 እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። 2 በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና። 3 - 4 ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በባንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ። 5 እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። 6 ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
7 ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤ 8 በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም። 9 እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም። 10 ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።
11 ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።
ስለዚህ እኛ እንደዚህ ቃል ከሆነ ለሃጥያት ነገሮች የሞትን ነን ማለት ነው። በማወቅም ሆነ ባለማወክቅ ለእግዚኣብሄር በማይመች መንገድ ተስማምተን ከሆን አሁን ቆም ብለን የምናስብበት ጊዜ ላይ ነን። ጌታ ማስተዋሉን ይስጠን!
ዮሃ8፥31 ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ። እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ 32 እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። 33 እነርሱም መልሰው። የአብርሃም ዘር ነን ለአንድም ስንኳ ከቶ ባሪያዎች አልሆንም፤ አንተ። አርነት ትወጣላችሁ እንዴት ትላለህ? አሉት። 34 ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው። 35 ባርያም ለዘላለም በቤት አይኖርም፤ ልጁ ለዘላለም ይኖራል።
እና ወገኖች ባለንበት ቦታ በስራም ሆነ በትምህርት እንደ እግዚኣብሄር ቃል መመላለሳችንን እናስተውል!!!!
ጸጋና ሰላም ይብዛልን!!!!
40 viewsErmi, 06:40