2023-01-23 10:34:19
*ከእግዚአብሔር ጋር እንሠራለን*
"1፤ ሰንባላጥም ቅጥሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፥ ተበሳጨም፥ በአይሁድም አላገጠ። በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት። እነዚህ ደካሞች አይሁድ የሚሠሩት ምንድር ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን? ብሎ ተናገረ።"
(ነህምያ 4:1)
ጠላት ቅጥሩ እንዳይሠራ በተለያ መንገድ ሕዝቡን ሊያዳክም ሲሞክር በነህምያ መጽሐፍ እናነባለን። በዚህ ምዕራፍ ደግሞ ሰንባላጥና ጦቢያ ቅጥሩ ቢሠራም ከንቱ እንደሆነ ይናገሩና ያፌዙ ጀመር።
"3፤ አሞናዊውም ጦብያ በአጠገቡ ቆሞ። በድንጋይ በሚሠሩት ቅጥራቸው ላይ ቀበሮ ቢመጣበት ያፈርሰዋል አለ። "
(ነህምያ 4:3፤)
ሆንም ግን ሕዝቡ የእነርሱን ከንቱ ስላቅ ሰምቶ ከሥራቸው ከመስተጓጎል ይልቅ ከፊት ይልቅ ለሥራው ልባቸው ጨከነ!
"6፤የሕዝቡም ልብ ለሥራው ጨከነ። "
(ነህምያ 4:6፤)
ወዳጆች ዛሬም ቢሆን እንደ ሰንባላጥና እንደጦቢያ ያሉ ሰዎች በዙሪያችን ተኮልኩለው ቅጥሩ እንዳይሠራና ተኩላ እንደፈለገ እንዲፈነጭበት ለማድረግ ሥራችን ከንቱ እንደሆነ ሊናገሩ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን ከእነርሱ ጋር ከንቱ ንትርክ ፈጥረን ጊዜኣችንን ከማባከን ይልቅ ልባችን ለሥራው ይጨክን! ምክንያቱም እኛ
"ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:9፤)
210 viewskoreb, 07:34