Get Mystery Box with random crypto!

የጸጋ ወንጌል

የቴሌግራም ቻናል አርማ abutjesys — የጸጋ ወንጌል
የቴሌግራም ቻናል አርማ abutjesys — የጸጋ ወንጌል
የሰርጥ አድራሻ: @abutjesys
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 376

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-29 16:31:55 ይህ የምዕራፍ 5 እና 6 ከማጀቢያ ጋር ነው ነገ በትርጓሜው መጽሐፍ አከፋፈል መሰረት ከምዕራፍ 7_10 ድረስ የሚቀጥል ይሆናል።
40 viewskoreb, 13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 16:20:53 ምዕራፍ 5 እና 6 ተጠናቋል። ነገ ከማጀቢያ ጋር ይላካል።
83 viewskoreb, 13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 16:20:30 Sharing File...
65 viewskoreb, 13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 18:54:03 Sharing File...
77 viewskoreb, 15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 13:24:47 * የመንፈስ ቅዱስ አካልነት! *

> የተለያዩ የስህተት አስተማሪዎች ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገሩ፣ “መንፈስ ቅዱስ የሆነ ኃይል ወይም ተጽህኖ እንጂ አካል ያለው አይደለም” ይላሉ፡፡

> መጽሐፉ ግን መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው መለኮት እንጂ የሆነ ኃይል ወይም ተጽህኖ እንዳልሆነ በሚከተሉት ጥቅሶች ያስረዳናል፡፡ አካል ስንል በዋናነት ስሜት፣ ፈቃድና እውቀት ያለውን ማንነት እያመለከትን ነው።

#ጥቂት ስለ መንፈስ ቅዱስ አካልነት የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

1ኛ. 2ሳሙ.23፡2-3፣ ማቴ.10፡20 መንፈስ ቅዱስ ሲናገር ያሳያል፡፡

2ኛ. ማቴ.28፡19 መንፈስ ቅዱስ አካል ካላቸው አብና ወልድ ጋር በአንድነት ቀርቦዋል፡፡

3ኛ. ኢሳ.63፡14፣ ሉቃ.4፡1 መንፈስ ቅዱስ ይመራል፡፡

4ኛ. ሉቃ.12፡12 መንፈስ ቅዱስ ያስተምራችኃል ተብሎዋል፡፡

5ኛ. ዮሐ.16፡8 መንፈስ ቅዱስ ይወቅሳል ተብሎዋል፤ አካል እንጂ አይል አይወቅስም፡፡

6ኛ. ዮሐ.16፡13 ላይ መንፈስ ቅዱስ ይመራል፣ ይናገራል፣ ይሰማል ተብለናል፡፡

7ኛ. ዮሐ.14፡16 ላይ “ሌላ” የሚለው የተለየ ግን እንደ እኔው የሆነ አካል ማለት ነው፡፡

8ኛ. ዮሐ.14፡16፣ 16፡7 መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስን ቦታ ተክቶ እንደሚያጽናናቸው ተነግሮናል፤ አይል የኢየሱስ ቦታ ሊተካም ሆነ ሊያጽናና አይችልም፡፡

9ኛ. ዮሐ.16፡16-17 መንፈስ ቅዱስ እርሱ ተብሎዋል፡፡

10ኛ. ዮሐ.14፡16 ከእናንተ ጋር ይኖራል የሚለው መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዳለው ማሳያ ነው፡፡

11ኛ. ዮሐ.15፡26 መንፈስ ቅዱስ ምስክር ተብሎዋል፤ አካል እንጂ አይል ምስክር ሊሆን አይችልም፡፡ ቁ.27 ላይ አካል የሆኑት ደቀመዛሙርቱ ምስክር በተባሉበት መጠን መንፈስ ቅዱስም እንደዚያ መባሉን ማስተዋ ይገባል፡፡

12ኛ. የሐዋ.5፡1-5 ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን ለመዋሸት ወይም ለማታለል ሞከራችሁ ብሎዋል፡፡

13ኛ. የሐዋ.10፡19-20 መንፈስ ቅዱስ ሲናገር እና ሲልካቸው እናያለን፡፡

14ኛ. የሐዋ.13፡2 ሰዎችን ለስራ ለዩልኝ ሲል እናያለን፡፡

15ኛ. የሐዋ.15፡28 መንፈስ ቅዱስ ሲፈቅድ ይታያል፡፡

16ኛ. የሐዋ.16፡6-7 መንፈስ ቅዱስ ይከለክላል፡፡

17ኛ. ሕዝ.37፡14፣ ሮሜ.8፡11 መንፈስ ቅዱስ ሕይወትን ይሰጣል፡፡

18ኛ. ሮሜ.8፡14 መንፈስ ቅዱስ ይመራል፡፡

19ኛ. ሮሜ.8፡26 መንፈስ ቅዱስ ይጸልያል ወይም ይማልዳል እንዲሁም የአብን የእኛንም አሳብ ያውቃል ተብሎዋል፡፡

20ኛ. ሮሜ.8፡27 መንፈስ ቅዱስ አሳብ እንዳለው ይነገራል፡፡ አካል እንጂ አይል አሳብ የለውም፡፡

21ኛ. ሮሜ.15፡30 መንፈስ ቅዱስ እንደሚወድ ይናገራል፡፡ መውደድ የአካል ጠባይ ነው፡፡

22ኛ. 1ቆሮ.2፡10-11መንፈስ ቅዱስ እውቀት አለው፡፡

23ኛ. 1ቆሮ.12፡11 መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ አለው፡፡
77 viewsJesus-my-Saviour, 10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 12:25:35 #የመዳን ቀን ፣ #የቁጣው ቀን!

“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
  — 2ኛ ቆሮ 6፥2
#።።
ራእይ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥
¹⁶ ተራራዎችንና ዓለቶችንም፦ በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤
¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸው።

☞ እያንዳንዱ ሰው ኃጢአተኛና በደለኛ በመሆኑ ለሰው ኃጢአትና በደል ምላሽ የሆነውን የቅዱሱ እግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ ማለትም #የዘላለም #የሞት_ፍርድ ይገቧል ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር  ሰለ ሰው ኃጢአትና በደል የጽድቁ ቁጣ #በቅዱሱ ልጁ #በኢየሱስ ክርስቶስ #በመስቀል ላይ  በማፍሰስ ይህን ፍቅር #አምነው ለሚቀበሉ ሁሉ #የዘላለም_መዳን አደረገ! የሚደንቅ ጸጋ።

— ኢየሱስ ክርስቶስ ሰለ ኃጢአታችን ሞቷል(1ዼጥ3፥18)
— ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሁሉ ይድን ዘንድ በመስቀል ስለ ሁሉ ነፍሱን #ቤዛ አድርጎ ሰጥቷል(2ጢሚ2፥5–6 ፣ ሮሜ 3፥23–24)
— ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኛው(ሰው ሁሉ) የሚገባውን ፍርድ በመቀበል #በመስቀል ላይ #ተፈጸመ በማለት #የኃጢአተኛውን #መዳንና #ከሞት #በመነሣት ደግሞ #የኃጢአተኛውን በእግዚአብሔር ዘንድ #መጽደቅ ወይም መሉ በሙሉ #ተቀባይነት ማግኘቱን አረጋግጧል(ዮሓ19፥28–30 ፣ ሮሜ4፥25)።

# ሰው ሰለ ኃጢአቱና ሰለ በደሉ ከሚገባው #የዘላለም የእግዚአብሔር የጽድቅ #ቁጣ #ይድን ያልተጠናቀቀ የቀረ ሥራ የለም #ሁሉም #በቅዱሱ #በእግዚአብሔር ልጅ #በኢየሱስ_ክርስቶስ #ሞትና #ትንሣኤ ተፈጽመዋል! የሰው ድርሻ ሰለ ኃጢአቱ #በሞተውና እርሱን ሰለማጽደቅ ከሞት #በተነሣው #በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ #በእውነት #ማመን ብቻ ነው።

“#በእርሱ #የሚያምን #ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
  — ዮሐንስ 3፥16


☞ ታድያ ሰው #በእውነተኛው #አዳኝና #ጌታ #በእውነት አምኖ የሚድንበት ቀን መቼ ይሆን? የእግዚአብሔር ቃል #የመዳን ቀን #አሁን ነው ይላል! ወገኖች #በጌታ #በኢየሱስ_ክርስቶስ #በእውነት #ካለመናችሁ #አሁኑኑ በእርሱ አምናችሁ #ከዘላለም ቁጣ ትድኑ ዘንድ #በእግዚአብሔር ፍቅር ጥሪአችንን እናቀርባለን።

☞ በብዙ የዋህነትና ትዕግስት በምድር ላይ በተመላለሰው ፣ የዓለምን ኃጢአት ያስወግድ ዘንድ በመስቀል #በሞተው #በእግዚአብሔር_በግ #ኢየሱስ  ዛሬ አሁን #የጸጋው_በር ሳይዘጋ #በእውነት #ያላመኑና #የማያምኑ ሰዎች #የቁጣ_ቀን ይጠብቃቸዋል! ያኔ በጉ በቁጣ ይገለጣል(ራእ6፥ 15–17)።

“በልጁ( በኢየሱስ) የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን #የእግዚአብሔር #ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
  — ዮሐንስ 3፥36
69 viewsYemane H/mariam, edited  09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 18:48:24 Sharing File...
73 viewskoreb, 15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 21:42:00 Sharing File...
27 viewskoreb, 18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 08:50:47 *እግዚአብሔርን የሚቀድመው ማነው?*
ፍጥረት በሙሉ በጊዜ ውስጥ ነው፤ ጊዜ ራሱ ደግሞ በእግዚአብሔር ውስጥ ነው!

> እግዚአብሔር አሳቡ፣ ሰው በምድር ባሉት ፍጥረታት ሁሉ ላይ ባለስልጣን ሆኖ ምድርን እየጠበቃት እና እያበጃት፣ በጋብቻም ሕይወት እየተባዛ በተባረከች ምድር ከእርሱ ጋር ኅብረት እያደረገ እንዲኖር ነበር።

#ይህን ያየው ሰይጣን ምን አደረገ?

> እግዚአብሔር ያሰበው ከመፈፀሙ በፊት ሊቀድመው ሞከረ፤ አዳምና ሚስቱ የገነት ኑሮን መኖር በጀመሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ (ምክንያቱም ልጅ እንኳ ገና አልወለዱም) የሰማይን ምክር ሊያፈራርሰው ፈለገ፤ ሰይጣን የእግዚአብሔርን አሳብ ቀድሞ በመገኘት ከፊት ያለውን እቅድ ጨለማ ሊያደርገው ሞከረ።

#ውጤት ምን ሆነ?

> ከላይ ሲታይ ሰይጣን ተሳካለት፤ እግዚአብሔርም ለሰው ያሰበው በአብዛኛው ሳይሆን ቀረ። ሰይጣን አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር አለያይቶ፣ የሰማዩን እቅድ የቀደመ መሰለ።

#እና እግዚአብሔር ተቀደመን?

> በፍፁም! ሰይጣን ያልገባው አንድ ነገር ነበር፤ አዳምና ሔዋን ገና ኃጢአት ከመስራታቸው በፊት በእግዚአብሔር ፊት ሲኖሩ ሳለ፣ ኃጢአት ሰርተው ከእርሱ እንደሚርቁ የሚያውቀው እግዚአብሔር፣ አዳምና ሔዋን ኃጢአት የሚሰሩበትን ቀን ቀድሞ ሄዶ አልፎ ገና ባልመጣ ቀን ላይ ቀድሞ ሄዶ እየጠበቃቸው ነበር።

> ሰዓት ቀዶሞ የሄደው ያው እግዚአብሔር፣ ወደፊት ብቻ ሳይሆን ወደ ኋላ ማለት አዳምና ሚስቱ ከመፈጠራቸው በፊትም አለና ሰይጣን የማያውቀውን ሌላ እቅድ አስቦ ጨርሷል(ኤፌ፡1÷4)።

> ምን እያልኩ ነው፦ እግዚአብሔር አልፋና ዖሜጋ ነው፤ ዛሬ ቅዳሜ ነው፤ እግዚአብሔር አልፋ ነውና ከቅዳሜ በፊት አለ፤ እግዚአብሔር ዖሜጋ ነውና ከቅዳሜ በኋላ አለ።

ፍጥረት በሙሉ በጊዜ ውስጥ ነው፤ ጊዜ ራሱ ደግሞ በእግዚአብሔር ውስጥ ነው!

#እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ዓለም ሳይፈጠር ያቀደውን ተመልከቱ

1: ሊበላሽ የሚችለው የተፈጥሮ ሕይወት ቀርቶ የዘላለም ሕይወት ባለቤት ማድረግ

2ኛ፡ በምድር ገነት ቀርቶ፣ በሰማዩ ገነት ማኖር

3ኛ፡ የምድር ላይ ብቻ ብቻቸውን ባለስልጣን ከሚሆኑ ከክርስቶስ ጋር በሰማይና በምድር ማንገስ

4ኛ፡ ሰይጣን፣ ኃጢአት፣ ሞት ለመግባት እድሉ ካላቸው ምድር ይልቅ ሶስቱም ድርሽ የማይሉበት የአብ ቤት ማኖር

> ሰይጣን ነገር አበላሻለሁ ብሎ፣ ክብር አስጨመረልን! ዘፍ፡3÷15 ላይ እግዚአብሔር የሴቲቱት ዘር ክርስቶስን እንገሚልክ ሰይጣን ሲሰማ፣ "ምነው መጀመሪያም ባልነካካው!" እንዳለ አስባለሁ።

#እናም መልእክቱ ይህ ነው! እግዚአብሔርን ማንም አይቀድመውም!!!

“አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”
— ራእይ 22፥13
52 viewsJesus-my-Saviour, 05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 21:17:27 «ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ፡፡ እግዚአብሔርን የምትፈሩ አመስግኑት የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ ፍሩት፡፡ ... በታላቅ ጉባኤ ምስጋናዬ ከአንተ ዘንድ ነው፤ እርሱን በሚፈሩት ፊት ስለቴን እሰጣለሁ፡፡ ችግረኞች ይበላሉ ይጠግቡማል፤ እግዚአብሔርንም የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸውም ለዘላለም ሕያው ይሆናል፡፡ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስቡ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሱ፤ የአሕዛብ ነገዶች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ፡፡ መንግሥት ለእግዚአብሔር ነውና እርሱም አሕዛብን ይገዛል፡፡... ዘሬ ይገዛለታል፤ የምትመጣው ትውልድ ለእግዚአብሔር ትነግረዋለች ጽድቁንም ለሚወለደው ሕዝብ እግዚአብሔር ያደረገውን ጽድቁን ይነግራሉ» (ቁ.22-31)፡፡
ታላቅ በሆነ ግልጽነት እነዚህ ሁለት ጥቅሶች የክርስቶስን ሞት ሁለቱን ገጽታዎች ያሳያሉ፡፡ እርሱ እንደ አንድ ሰማዕት ስለጽድቅ በሰው እጅ ሞተ፡፡ ለዚህም የሰው ልጅ ስለፈጸመው ግድያ ለእግዚአብሐር መልስ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ነገር ግን በሌላ ገጹ እርሱ እንደ አንድ ሰለባ በእግዚአብሔር እጅ ለኃጢአተ ሞተ፡፡ ይህም በስሙ ለሚያምኑት ሁሉ ለበረከቶች ሁሉ መሠረት ነው፡፡ የክርስቶስ የሰማዕትነት መከራ ቁጣንና ፍርድን በአምላክ የለሸ ዓለም ላይ ያወርዳል፤ ሥርየትን ለማስገኘት የተቀበለው መከራው ግን ለቤተክርስቲያን ለእስራኤልና ለመላው ፍጥረት ሁሉ ሕይወትና የመዳን የዘላለም ምንጭ እንዲከፈት አደረገ፡፡ የኢየሱስ ሞት የዓለምን የጥፋት ቁንጮ ሲያመለከት ለቤተክርስቲያን ግን ተቀባይነትዋን ያረጋግጣል፡፡ ዓለም በመስቀል ደም ስትጐድፍ ቤተክርስቲያን ግን በዚሁ ደም ነጻች፡፡
56 viewsTsegaye Tezazu, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ