Get Mystery Box with random crypto!

የ ፍቅር ጥግ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ye_dessie_lijoci — የ ፍቅር ጥግ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ye_dessie_lijoci — የ ፍቅር ጥግ
የሰርጥ አድራሻ: @ye_dessie_lijoci
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 467
የሰርጥ መግለጫ

‼️DESSIE‼️

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 13:35:16 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አክቲቪስቶች ግድያ ሲፈጸም አየሩን ይሞሉታል፤ ፖሊስ እርምጃ ሲወስድ ህጋዊ ነገር ሲከበር ግን የሉም፤
ሸኔ የኦሮሞ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ ሸኔ ለማንም የማይመለሱ አውሬዎች ናቸው፤
ለምንድን ነው አውሬ የሆኑት የሚለው ጥናት ይፈልጋል፤ የፖለቲካ አላማ ግን የላቸውም፤
የሸኔ ዓላማው አገር ማፍረስ ነው፤
ሁለት ልጆችህን አገር ሊታደጉ ዘምተዋል ተብለው አባት በሸኔ ተገድለዋል፤
የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ቤተሰቦች ተገድለዋል፤ በመቶ የሚቆጠሩ አመራሮች ተገድለዋል፤
ሸኔ የኦሮሞ ተወካይ አይደለም፤ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ በሸኔ ምክንያት ወለጋ ውስጥ ልማት ቆማል፤
ይሄንን ጠላት የሁላችንም ጠላት ነው ብለን ከተነሳን እናጠፋዋለን፤
ለሸኔ የሚራራ የሚያዝን የተለየ ስሜት የለንም፤ እንደ ሸኔ ያሉ ኃይሎች ዋና ፍላጎታቸው ፓርላማው ሚዲያው ዓለም ስለእነሱ እንዲያወራ ነው፤
ለእናንተ ባንናገርም በእያንዳንዱ ደቂቃ እየተዋጋናቸው ነው፤
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለመመስረት ነው ፍላጎታችን እየሰራን ያለነወም ለዚያ ነው፤
ጽንፈኞች በየትኛው ሰፈር ይደራጁ ሁለት መርዝ አላቸው፤ አንደኛው የእኔ ብቻ ጥሩ ነው የሚለው ነው፤ ሁለተኛው በጣም የበዛ የራስ ሀዘኔታ፤ የነገሮች ሁሉ ማዕከል ራስን ብቻ ማድረግ ነው፤
ጽንፈኝነት ዓለምን አልጠቀመም ኢትዮጵያን አይጠቅምም፤ መግረፍና ማፈን ከብልጽግና ጋር አብሮ አይሄድም፤ ለጠላት ተገማች አንሁን፤

የሽግግር መንግስት የሚለው ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ የነበረ ተረት ተረት ነው፤ እነሱ የሽግግር መንግስት ይበሉ እኛ አገር እናጽና፤
የሽግግር መንግስት የሚሉ ሰዎች ስርአት ማፍረስ እንጂ አገር ቀርቶ ተቋም እንዴት እንደሚመራ ልምዱም ዝግጅቱም የላቸውም፤
በኢትዮጵያ የተካሄደው ምርጫ ከእስከዛሬው ምርጫ በዴሞክራሲያዊነቱ በጣም የተሻለ ነው፤
ያለን ጊዜ አራት አመት ነው፤ ያንን ታሳቢ አድረገን ሳንተኛ እየሰራን ነው፤
የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት በሙሉ ድምጽ ምንጊዜም ቅድሚያ የሚሰጡት ለሰላም ነው፤
የኢትዮጵያን መንግስት የሚመራው ብልጽግና ነው፤ የማወያየት እንጂ ወስኖ የመምራት መብት የብልጽግና ነው፤
ከአሸባሪ ጋር ድርድር አይካሄድም የሚለውን በደንብ ብናየው ጥሩ ነው፤ ውጊያ ውስጥ እንኳን ሆኖ ድርድር ይካሄዳል፤
ማንኛውም ዜጋ መጠየቅ ያለበት የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈህ ሰጥተሃል ወይንስ አልሰጠህም ብሎ ነው፤
አገር አቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ትምህርት ሚኒስቴር በቂ ዝግጅት እያደረገ ነው፤
ለሥራ እድል ፈጠራ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ተቋሙን በሚኒስቴር ደረጃ አቋቁመናል፤ ከፍተኛ ልምድ ያለው ሚኒስትርም እንዲመራው ተደርጓል፤
በክረምት አዲስ ገጽ እንግለጥ፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናልብስ፤ ሰው እየሞተ ችግኝ መትል የለብንም የሚለን ጠላት ነው፤ አትስሙት፤
ችግኝና ፖለቲካን ስንዴና ፖለቲካን አንደ የሚያደርጉ ሰዎች ፖለቲካን የማያውቁ ሰርተው የማያውቁ ናቸው፤
ይህ ክረምቱ ብዙ የምንሰራበት ብዙ የምናተርፍበት መሆን አለበት፤
ለፈተናሸብረክ የምንል ሳይሆን ኢትዮጵያን የምናሻግር መሆን አለብን፤

የቀጣይ አመት በጀት የተጀመረውን እድገት የሚያስቀጥል ነው፤
የመንግስት ገቢ እስከ ግንቦት ድረስ 300 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደን 309 ቢሊዮን ብር ሰብሰበናል፤
አምና በ11 ወር የሰበሰብነው የዘንድሮው 50 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው፤
ይህንን እድገት ያመጣው በገቢ ሰብሳቢ መስሪያቤት ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ስለሰሩ ነው፤ ምስጋና ይገባቸዋል፤
በሁለተኛ ደረጃ ዋና ዋና የሚባሉት ነጋዴዎች ግብር ለመክፈል ያላቸው መሻሻል ነው፤
ግድታቸውን የሚወጡ ነጋዴዎች እየበዙ ነው፤ ምስጋና ይገባቸዋል፤
በ11 ወራት ውስጥ 500 ቢሊዮን ብር ወጪ አውጥተናል፤ ወጪያችንን ያበዛው የከፈልነወ እዳ ነው፤
ከገቢያችን ውስጥ 1 ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር እዳ ከፍለናል፤
ወጪ ንግድ ላይ ያመጣነው እመርታ በጣም ግዙፍ ነው፤
ኢትዮጰያ በ2002 ዓ ም ሁለት ቢሊዮን ዶላር የወጪ ምርት አድርጋ ነበር፤ በ10 አመት ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር ነው የጨመርነው፤
ዘንድሮ በሸቀጥና አገልገሎት 10 ቢሊዮን ዶላር በላይ አግኝተናል፤ ከወጪ ንግዱ የተገኘው ውጤት የለውጡን ስኬት የሚያሳየው ነው፤
ግብርና ከተገኘው ውጤት 20 በመቶ ድርሻ አለው፤
በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ዘንድሮ ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት መጥቷል፤
በፋይናንሻል ሴክተሩም በተወሰደ ማስተካከያ መሰረት ከፍተኛ ለውጥ መጥቷል።
76 views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:04:05 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ታብሌቶች ካልደረሱ ሌሎች አማራጮች እንደሚጠቀም መንግስት አስታወቀ!!

በሚቀጥለዉ አመት በኦንላይን ይሰጣል ለተባለዉ ሀገር አቀፍ ፈተና ይገባሉ የተባሉ 1 ሚሊዮን ታብሌት ኮምፒውተሮች በወቅቱ ካልደረሱ ሌሎች ምርጫዎችን መንግስት ይከተላል-ጠ/ሚ አብይ

በ2015 ዓ.ም የሚሰጠዉ ሀገር አቀፍ ፈተናን ዲጂታል በሆነ መንገድ በኦንላይን ምዘናዉን ለመስጠት ታቅዶ እንደነበር ይታወሳል። ለዚህም 1ሚሊዮን የሚሆኑ ታብሌት ኮምፒውተሮች ወደ ሀገር ይገባሉ ተብሎም ነበር።

ጠ/ሚ አብይ ይህን በተመለከተ በሰጡት ማብራርያ ያለዉን ስርቆት ለማስቀረት ሲባል ፈተናዉን ዲጂታላያዝ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም 1ሚሊዮን ታብሌት ኮምፕዩተሮቹን ከቻይና መንግስት ጋር በመሆን ለማስገባት እየተሰራ እንደነበር አስታዉሰዋል። ሆኖም በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያትም አምራች ድርጅቱ ስራዉን በተያዘለት ግዜ ማጠናቀቅ አለመቻሉን አስታዉቀዋል።

በ2015 ለመስጠት የታቀደዉ ፈተናዉ ፤ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ ታብሌት ኮምፒውተሮቹ በተያዘላቸዉ ግዜ ከደረሱ ፈተናዉ ይሰጣል ብለዋል። ሆኖም ታብሌቶቹ በግዜዉ ካልደረሱ መንግሰት ሌሎች ምርጫዎችን እንደሚጠቀም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።
76 views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:56:57 #እንዴት ነው #መጋበዝ ምንችለው?

1/ በመጀመሪያ " ሰው ለመጋበዝ" የሚለውን MENU ይጫኑ።

2/ በመቀጠል ለእርሶ የሚላክሎትን የራሶ መለያ ሊንክ ለሌሎች #ሼር ( #Forward ) በማድረግ ይጋብዙ።

3/ ሰዎች የእርስዎን ሊንክ ተጭነው ቡቱን ሲቀላቀሉ መልዕክት ይደርስዎታል።

4 በእርስዎ ግብዣ አማካኝነት የተቀላቀሉ ሰዎች ቁጥር 20 ሲደርስ የባንክ ሂሳብ ቁጥርና ስልክዎን ይላኩልን። ወዲያውኑ 1ሺ ብር እና 2 GB ጥቅል እንልክልዎታለን።

የቴሌብር አሸናፊ ተሸላሚዎችን ሊንኩን በመጫን በቴሌግራም ገፃችን ይመልከቱ።

ከሽልማቱ ለመሳተፍ ይህን የመጋበዣ ሊንክ ኮፒ አድርገው ለወዳጅዎ በመላክ ተሸላሚ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል
https://t.me/EthTelebirr_bot?start=r01438135450

Telebirr
586 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:22:53 Ewenet new tetkmubet
102 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:33:55
"ጭፍጨፋውን እየመሩት ያሉት የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ናቸው።" - አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባል ከተናገሩት የተወሰደ

አቶ ሀንጋሳ ትናንት ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ በዚህም፣

አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣ አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር ቤት በማስገባት ሰላም ይስፈን፣ ዶ/ር አብይ ከለማ የቀረበ ወዳጅ አልነበረህም በሱ ላይ የጨከንክ በሽመልስ ላይ መጨከን እንዴት አቃተህ ብሏል።

- እነ ሽመልስ ዙሪያውን ከበው ሊበሉህ ነው፣ ሊጨርሱህ ነው የመጨረሻው ሰዓት ላይ ደርሰሃል አይንህን ግለጥ! አማራን ኦሮሚያ ውስጥ መጨፍጨፍ የሚጎዳው ከአማራ ይልቅ ኦሮሞን ነው፣ መቼ ነው ዶ/ር አብይ ከአትክልት ስራ ወጥተህ ጠንከር ያለ ስራ የምትሰራው፤ መቼ ነው የከበበህ መከራ የሚታይህ፣ መቼ ነው ሊበላህ የተነሳው ጅብ የሚታይህ ብሏል።

- ዛሬ አማራን እየገደለ የሚመጣው ሀይል መቆሚያው አንተ ቤት (አራት ኪሎ) ነው ፣ ሽመልስ እና ፍቃዱ ታደሰን ወደ እስር ቤት ካላስገባህ ከዚህ ጥቃት ጀርባ አንተ አለህ ማለት ነው፣ ለአብዲ ኢሌ ክፍት የሆነ እስር ቤት ለሽመልስ እና ፍቃዱ ዝግ የሆነው ኦሮሞ ስለሆኑ ነው ወይስ አዛዡ አንተ ስለሆንክ ነው ብሏል።
124 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:31:49 በቄለም ወለጋ የጅምላ ግድያው ከመፈፀሙ አስቀድሞ ለስብሰባ ትፈለጋለችሁ በሚል ተጠርተን ነበር ሲሉ የዓይን እማኞች ተናገሩ፡፡

አሻም ያነጋገረቻቸው ከጅምላ ግድያው ያመለጡ የኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ፣ ለምለም ቀበሌ፣ መንደር 20 እና 21 ነዋሪዎች ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ”ጭፍጨፋው ከመፈፀሙ አስቀድሞ ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ” በሚል በማስገደድ ጭምር ከየቤታቸው እንደተወሰዱ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ባነጣጠረው የጅምላ ግድያ 72 ሰዎች ሰርዓተ-ቀብራቸው መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩት የቀብር ስነ ሰርዓታቸው ሲፈፀም ጭምር መመልከታቸውን ለአሻም ነግረዋታል፡፡ ”አሁንም ድረስ የት እንዳሉ፣ ይሞቱ/ይኑሩ የማይታወቁ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንዳሉም” ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡
117 views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:23:48 እኔን ሚወክል ሰው ካላ እጁን ያውጣ
154 views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 17:41:49 ወቅታዊ መግለጫ

በአገሪቱ ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የሚወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ!!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም በዛሬው ዕለት ለውጭ መገናኛ ብዙኃን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ አሸሪው ሸኔ በንጹሓን ዜጎች ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ አውግዘዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል አሸባሪው ሸኔ በሚንቀሳሰቀስባቸው አካባቢዎች ላይ አስፈላጊው ህግ የማስከበር እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የገለጹት ቢልለኔ፥ ቡድኑ እርምጃውን መቋቋም ሲያቅተው በንጽሃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ግድያ መፈጸሙን አስረድተዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ተግባር በኦሮሞ እና አማራ ህዝቦች መካከል የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ አለመረጋጋት ለመፍጠር አቅዶ የፈጸመው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ በቡድኑ የሽብር ድርጊት ዝርዝር ሁኔታ ላይ ምራመራ እያካሄደ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ቡድኑ በፈጠረው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎችም አስፈላጊው እርዳታ እየተሰራጨ መሆኑን ጠቁመው፥ በአሸባሪው ሸኔ ላይ በፌደራል መንግስት እና በክልሉ መንግስት የሚወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መወሰኑን የገለጹት ብልለኔ ስዩም፥ ለዚህም በሰላም ውይይት ላይ የሚሳተፍ ኮሚቴ መቋቋሙን አስታውሰዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት የሰሜን እዝ እስከተወጋበት ጊዜ ድረስ የነበሩ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር አስታውሰው፥ ከጥቃቱ በኋላም መንግስት ህውሐት ግጭቱን እንዲያቆም እና በግጭቱ ምክንያት ደም መፋሰስ እንዳይከሰት ለማድረግ ብዙ ጥረቶች አድርጎ ብዙ ዋጋ መክፈሉንም አብራርተዋል፡፡

በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከህወሓት ጋር የሚደረገው የሰላም ውይይት ህግ መንግስቱን ባከበረ እና የአገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ እንደሚካሄድ መስፈርቶች መቀመጣቸውንም አብራርተዋል፡፡በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በተሽከርካሪ እና በአየር ትራንፖርት የሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልፀዋል።የአረንጓዴ አሻራን በሚመለከትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አራተኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ማስጀመራቸውን አንስተዋል፡፡

በመርሐ ግቡሩም በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማሳተፍ በአራት ዓመት ውስጥ 20 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል የታቀደውን እቅድ ለማሳካት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በመርሐ ግብሩ ለ183 ሺህ በላይ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜዊ የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ያሉት ብልለኔ÷ ይህም 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ማስገኘቱን አመላክተዋል፡፡
250 views14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 17:41:18
198 views14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 17:37:34 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ እንደሚሰጥ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሆሳዕና ፣ በወራቤና በወልቂጤ ከተሞች የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኚታቸዉ ወቅት ከተማሪዎችና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

እንደሚኒስትሩ ገለጻ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኤሌክትሮኒክስ /online/ መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲ እንዲሰጥ የተወሰነው የፈተና ሰርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ በመሆኑ ተማሪዎች ትምህርት በስራና በታታሪነት የሚገኝ መሆኑን አውቀው በርትተው መማር ፣ማጥናትና ማወቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትን ጥራትን ለማሻሻል በአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፎች ሌሎችንም የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ሶስቱንም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጎበኙ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ ችግኝም ተክለዋል፡፡

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
https://t.me/ye_dessie_lijoci
175 views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ