Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች የኢትዮጵያ ፖለቲ | የ ፍቅር ጥግ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አክቲቪስቶች ግድያ ሲፈጸም አየሩን ይሞሉታል፤ ፖሊስ እርምጃ ሲወስድ ህጋዊ ነገር ሲከበር ግን የሉም፤
ሸኔ የኦሮሞ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ ሸኔ ለማንም የማይመለሱ አውሬዎች ናቸው፤
ለምንድን ነው አውሬ የሆኑት የሚለው ጥናት ይፈልጋል፤ የፖለቲካ አላማ ግን የላቸውም፤
የሸኔ ዓላማው አገር ማፍረስ ነው፤
ሁለት ልጆችህን አገር ሊታደጉ ዘምተዋል ተብለው አባት በሸኔ ተገድለዋል፤
የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ቤተሰቦች ተገድለዋል፤ በመቶ የሚቆጠሩ አመራሮች ተገድለዋል፤
ሸኔ የኦሮሞ ተወካይ አይደለም፤ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ በሸኔ ምክንያት ወለጋ ውስጥ ልማት ቆማል፤
ይሄንን ጠላት የሁላችንም ጠላት ነው ብለን ከተነሳን እናጠፋዋለን፤
ለሸኔ የሚራራ የሚያዝን የተለየ ስሜት የለንም፤ እንደ ሸኔ ያሉ ኃይሎች ዋና ፍላጎታቸው ፓርላማው ሚዲያው ዓለም ስለእነሱ እንዲያወራ ነው፤
ለእናንተ ባንናገርም በእያንዳንዱ ደቂቃ እየተዋጋናቸው ነው፤
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለመመስረት ነው ፍላጎታችን እየሰራን ያለነወም ለዚያ ነው፤
ጽንፈኞች በየትኛው ሰፈር ይደራጁ ሁለት መርዝ አላቸው፤ አንደኛው የእኔ ብቻ ጥሩ ነው የሚለው ነው፤ ሁለተኛው በጣም የበዛ የራስ ሀዘኔታ፤ የነገሮች ሁሉ ማዕከል ራስን ብቻ ማድረግ ነው፤
ጽንፈኝነት ዓለምን አልጠቀመም ኢትዮጵያን አይጠቅምም፤ መግረፍና ማፈን ከብልጽግና ጋር አብሮ አይሄድም፤ ለጠላት ተገማች አንሁን፤

የሽግግር መንግስት የሚለው ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ የነበረ ተረት ተረት ነው፤ እነሱ የሽግግር መንግስት ይበሉ እኛ አገር እናጽና፤
የሽግግር መንግስት የሚሉ ሰዎች ስርአት ማፍረስ እንጂ አገር ቀርቶ ተቋም እንዴት እንደሚመራ ልምዱም ዝግጅቱም የላቸውም፤
በኢትዮጵያ የተካሄደው ምርጫ ከእስከዛሬው ምርጫ በዴሞክራሲያዊነቱ በጣም የተሻለ ነው፤
ያለን ጊዜ አራት አመት ነው፤ ያንን ታሳቢ አድረገን ሳንተኛ እየሰራን ነው፤
የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት በሙሉ ድምጽ ምንጊዜም ቅድሚያ የሚሰጡት ለሰላም ነው፤
የኢትዮጵያን መንግስት የሚመራው ብልጽግና ነው፤ የማወያየት እንጂ ወስኖ የመምራት መብት የብልጽግና ነው፤
ከአሸባሪ ጋር ድርድር አይካሄድም የሚለውን በደንብ ብናየው ጥሩ ነው፤ ውጊያ ውስጥ እንኳን ሆኖ ድርድር ይካሄዳል፤
ማንኛውም ዜጋ መጠየቅ ያለበት የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈህ ሰጥተሃል ወይንስ አልሰጠህም ብሎ ነው፤
አገር አቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ትምህርት ሚኒስቴር በቂ ዝግጅት እያደረገ ነው፤
ለሥራ እድል ፈጠራ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ተቋሙን በሚኒስቴር ደረጃ አቋቁመናል፤ ከፍተኛ ልምድ ያለው ሚኒስትርም እንዲመራው ተደርጓል፤
በክረምት አዲስ ገጽ እንግለጥ፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናልብስ፤ ሰው እየሞተ ችግኝ መትል የለብንም የሚለን ጠላት ነው፤ አትስሙት፤
ችግኝና ፖለቲካን ስንዴና ፖለቲካን አንደ የሚያደርጉ ሰዎች ፖለቲካን የማያውቁ ሰርተው የማያውቁ ናቸው፤
ይህ ክረምቱ ብዙ የምንሰራበት ብዙ የምናተርፍበት መሆን አለበት፤
ለፈተናሸብረክ የምንል ሳይሆን ኢትዮጵያን የምናሻግር መሆን አለብን፤

የቀጣይ አመት በጀት የተጀመረውን እድገት የሚያስቀጥል ነው፤
የመንግስት ገቢ እስከ ግንቦት ድረስ 300 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደን 309 ቢሊዮን ብር ሰብሰበናል፤
አምና በ11 ወር የሰበሰብነው የዘንድሮው 50 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው፤
ይህንን እድገት ያመጣው በገቢ ሰብሳቢ መስሪያቤት ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ስለሰሩ ነው፤ ምስጋና ይገባቸዋል፤
በሁለተኛ ደረጃ ዋና ዋና የሚባሉት ነጋዴዎች ግብር ለመክፈል ያላቸው መሻሻል ነው፤
ግድታቸውን የሚወጡ ነጋዴዎች እየበዙ ነው፤ ምስጋና ይገባቸዋል፤
በ11 ወራት ውስጥ 500 ቢሊዮን ብር ወጪ አውጥተናል፤ ወጪያችንን ያበዛው የከፈልነወ እዳ ነው፤
ከገቢያችን ውስጥ 1 ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር እዳ ከፍለናል፤
ወጪ ንግድ ላይ ያመጣነው እመርታ በጣም ግዙፍ ነው፤
ኢትዮጰያ በ2002 ዓ ም ሁለት ቢሊዮን ዶላር የወጪ ምርት አድርጋ ነበር፤ በ10 አመት ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር ነው የጨመርነው፤
ዘንድሮ በሸቀጥና አገልገሎት 10 ቢሊዮን ዶላር በላይ አግኝተናል፤ ከወጪ ንግዱ የተገኘው ውጤት የለውጡን ስኬት የሚያሳየው ነው፤
ግብርና ከተገኘው ውጤት 20 በመቶ ድርሻ አለው፤
በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ዘንድሮ ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት መጥቷል፤
በፋይናንሻል ሴክተሩም በተወሰደ ማስተካከያ መሰረት ከፍተኛ ለውጥ መጥቷል።