Get Mystery Box with random crypto!

'ጭፍጨፋውን እየመሩት ያሉት የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ናቸው።' - አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም የ | የ ፍቅር ጥግ

"ጭፍጨፋውን እየመሩት ያሉት የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ናቸው።" - አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባል ከተናገሩት የተወሰደ

አቶ ሀንጋሳ ትናንት ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ በዚህም፣

አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣ አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር ቤት በማስገባት ሰላም ይስፈን፣ ዶ/ር አብይ ከለማ የቀረበ ወዳጅ አልነበረህም በሱ ላይ የጨከንክ በሽመልስ ላይ መጨከን እንዴት አቃተህ ብሏል።

- እነ ሽመልስ ዙሪያውን ከበው ሊበሉህ ነው፣ ሊጨርሱህ ነው የመጨረሻው ሰዓት ላይ ደርሰሃል አይንህን ግለጥ! አማራን ኦሮሚያ ውስጥ መጨፍጨፍ የሚጎዳው ከአማራ ይልቅ ኦሮሞን ነው፣ መቼ ነው ዶ/ር አብይ ከአትክልት ስራ ወጥተህ ጠንከር ያለ ስራ የምትሰራው፤ መቼ ነው የከበበህ መከራ የሚታይህ፣ መቼ ነው ሊበላህ የተነሳው ጅብ የሚታይህ ብሏል።

- ዛሬ አማራን እየገደለ የሚመጣው ሀይል መቆሚያው አንተ ቤት (አራት ኪሎ) ነው ፣ ሽመልስ እና ፍቃዱ ታደሰን ወደ እስር ቤት ካላስገባህ ከዚህ ጥቃት ጀርባ አንተ አለህ ማለት ነው፣ ለአብዲ ኢሌ ክፍት የሆነ እስር ቤት ለሽመልስ እና ፍቃዱ ዝግ የሆነው ኦሮሞ ስለሆኑ ነው ወይስ አዛዡ አንተ ስለሆንክ ነው ብሏል።