Get Mystery Box with random crypto!

በቄለም ወለጋ የጅምላ ግድያው ከመፈፀሙ አስቀድሞ ለስብሰባ ትፈለጋለችሁ በሚል ተጠርተን ነበር ሲሉ | የ ፍቅር ጥግ

በቄለም ወለጋ የጅምላ ግድያው ከመፈፀሙ አስቀድሞ ለስብሰባ ትፈለጋለችሁ በሚል ተጠርተን ነበር ሲሉ የዓይን እማኞች ተናገሩ፡፡

አሻም ያነጋገረቻቸው ከጅምላ ግድያው ያመለጡ የኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ፣ ለምለም ቀበሌ፣ መንደር 20 እና 21 ነዋሪዎች ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ”ጭፍጨፋው ከመፈፀሙ አስቀድሞ ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ” በሚል በማስገደድ ጭምር ከየቤታቸው እንደተወሰዱ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ባነጣጠረው የጅምላ ግድያ 72 ሰዎች ሰርዓተ-ቀብራቸው መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩት የቀብር ስነ ሰርዓታቸው ሲፈፀም ጭምር መመልከታቸውን ለአሻም ነግረዋታል፡፡ ”አሁንም ድረስ የት እንዳሉ፣ ይሞቱ/ይኑሩ የማይታወቁ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንዳሉም” ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡