2022-06-26 07:00:36
ከዓለም አቀፍ የዐማራ ጉባኤ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግጫ!
ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ጠብቆ ያኖረው የዐማራ ሕዝብ በተለይ ከትህነግ መምጣት ጀመሮ ሲጨፈጨፍ ሲሳደድ የዘር ማጥፋትና ማፅዳት ሲካሄድበት ቆይቷል። አሁንም የሰሞኑ ጭፍጨፋ ማረጋገጫ ነው። ደግሞ የዐብይ አገዛዝ የዘር ማጥፋትና ማፅዳት ወንጀሎችን ለመስቆም እየሰራ እንዳልሆ እኛ በዓለም ዙሪያ የምንገኝ አማራዎች ይህን ግልጽም-ስውርም ደባ በዝምታ ማለፍ የጥፋት ተባባሪነት ስለሚሆን በተናጠል የምናደርገውን የዐማራ የህልውና ትግል በተቀናጀ ስልታዊ መንገድ ለማካሄድ መሰረት የጣልንበት የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ የዐማራ ጉባኤ እኤአ በሰኔ 18 ቀን 2022 እና 19 ቀን 2022 አካሂደናል።
በዚህ ጉባኤ የዐማራን ዘር ማጥፋትና ማፅዳት በጽኑ አውግዘን ከዚህ ጋር በተያያዘ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎች አሳልፈናል።
፩. ጉበኤው እየተካሄድ እያለ ጊምቢ በሚባል የወለጋ በግምት እስከ 2000 የሚደርሱ ዐማራች በመጨፍጨፋቸዉ በጥልቅ የተሰማንን ሃዘን በመግለፅ፣ የተደረገውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በጥብቅ በማውገዝ፣ ጉባኤው የ“ኦሮሚያ” ገዢ ሽመልስ አብዲሳ እና ጠቅላይ ሚንስትር ተብዬው አብይ አሕመድ በዘር ማጥፋትና ማፅዳት ወንጀል በህግ መጠየቅ አለባቸው እንጠይቃለን።
፪. “እኔም ፋኖ ነኝ” በሚለው መርሆ መሰረት ፋኖነንትን ማዕከል ያደረገ ሁለገብ የትግል ስልት መቀየስና ለዐማራ ህዝብ ህልውና ከሚታገሉ ሃይሎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት መፍጠር አማራጭ የሌለው የትግል ስልት እንደሆነ ወስነናል። ይህንን የወሰንነው የዐማራውን የትግል አቅጣጫ የሚመራ፣ የተለያዩ የዐማራ ማህበራትን ያካተተ የፖለቲካ ማዕከል አስፈላጊ እንደሆነ በመገንዘብ ነው።
፫. በዐማራ ላይ ያነጣጠሩ ብዥታ ፈጣሪ የውጭ እና የውስጥ የሃሰት ትርክቶችን ለመናድና ትክክለኛውን የአማራና የኢትዮጵያ ታሪክ መርምሮ የሚያሳውቅና የዛሬውን የነፃነት ትግል አቅጣጫ የሚያስይዝ ምሁራዊ የጥናት ቡድን አስፈላጊነትን ተገንዝበን ቡድኑ እንዲስማራ ወስነናል።
፬. በዐማራው ላይ በጦርነት፣ በፓለቲካ፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች ለሚደርሱበት ጉዳቶች አስፈላጊውን ሰብአዊ እርዳታ ለማሰባሰብ የተለያዩ የአማራ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ግልጽ በሆነና ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንዲሠሩ ወስነናል።
፭. የሰላማዊው ትግል ዘርፍ የፋኖን ትግል መንፈስና እሴቶች በሚያንጽባርቅ መልክ በዉጭ አገር የሚኖሩ ዐማሮችና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በቆራጥነት ዐብይ አገዛዝ ተቋማት ላይ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አድማ በትብብር ይደረግበት ዘንድ ጉባኤው ጥሪ ያደርጋል።
168 views04:00