Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ እንደሚሰጥ ተገለፀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮ | የ ፍቅር ጥግ

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ እንደሚሰጥ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሆሳዕና ፣ በወራቤና በወልቂጤ ከተሞች የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኚታቸዉ ወቅት ከተማሪዎችና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

እንደሚኒስትሩ ገለጻ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኤሌክትሮኒክስ /online/ መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲ እንዲሰጥ የተወሰነው የፈተና ሰርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ በመሆኑ ተማሪዎች ትምህርት በስራና በታታሪነት የሚገኝ መሆኑን አውቀው በርትተው መማር ፣ማጥናትና ማወቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትን ጥራትን ለማሻሻል በአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፎች ሌሎችንም የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ሶስቱንም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጎበኙ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ ችግኝም ተክለዋል፡፡

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
https://t.me/ye_dessie_lijoci