Get Mystery Box with random crypto!

አቡ ሙዓዝ (ሐሰን ኢድሪስ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ abumuazhusenedris — አቡ ሙዓዝ (ሐሰን ኢድሪስ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ abumuazhusenedris — አቡ ሙዓዝ (ሐሰን ኢድሪስ)
የሰርጥ አድራሻ: @abumuazhusenedris
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.62K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ቻናሉ⬇ መግባት⬇ ከፈለጉ
http:https://t.me/abumuazhusenedris
አሰተያየትና⬇ጥያቄዎች ⬇ካለዎት
https://t.me/abumuazhusen_bot
ይጠቀሙበት!!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 07:54:06 ጉድ ነው የኛ ነገር በኛ ሀገር
<><><>

ሰው መከራ በሚመጣ ሰአት ከፊቱ የተሻለ እገዛ እንዳገኝ ይደረጋል እንጂ ጭራሽ ቀንበር እንድጠበው ሲሰረግ በእጅጉ ይዘገንናል።

እንደሚታወቀው በአሁኑ ሰአት ትንሽ የሰላም መታወክ ያለበት ሰአት እንደመሆኑ መጠን ህዝባችን የተወሰነ ብር በእጁ መያዝ ይፈልጋል

ይሁን እንጂ ንግድ ባንክ ለህዝቡ የሚፈልገውን አንድ አራተኛውን ለመስጠት ፍቃደኛ እየሆነ አይደለም።

ኧረ ይደብራል አያስታውስም እንዴ የዛሬ አመት አንድ ኩንታል ጤፍ አንድ ሺ ሶስት መቶ ብር ሲፈጭ? የ20 ብር ትራንስፖርት 500 ብር ሲከፈልበት? አንድ ኪሎ ጨው መቶ ብር ሲሸጥ? አንድ ኪሎ ሽንኩርትና ቲማቲም 120 ብር ሲሸጥ? አያስታውስም?

ታዲያ ብር መከልከሉ ከምን የመነጨ ይሆን ምን አልባት በእጅ አዙር ለጥላት አጋዥነት ይኖረው ይሆን?

t.me/abumuazhusenedris
194 views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:58:44 ጥቂት ነጥቦች ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ
~
1.  ወገኔ ሆይ! አገርህን አትልቀቅ።

ባለፈው ተፈናቃዮች ላይ የደረሰውን አስታውስ። ደብረ ብርሃንና ባህርዳር ለተፈናቃዮች ከማጎሪያ ካምፕ የማይለዩ እንደነበሩ ሲወራ ነበር። አሁን ደግሞ ነገሮች ከቀድሞው ቢብሱ እንጂ የተሻሉ አይደሉም። ፖለቲከኛውን ተወው። ህዝብ እራሱ ኑሮ ስለከበደው ሊጨካከን፣ ሊሰላች ይችላል። ሩቅ አትሂድ። ደሴ ወልዲያን፣ ወልዲያ ቆቦን ሊሰለች ይችላል። የጎደለበት ደግሞ በትንሽ በትልቁ ይከፋዋል። ስለዚህ በተለየ እፈለጋለሁ ብሎ የሚሰጋ ካልሆነ በስተቀር ጦርነቱ ቀጥታ ከሚካሄድባቸው ቀጠናዎች ለጊዜው ዞር ከማለት ውጭ ካገር ርቆ መሄድ ስቃዩን የከፋ ያደርገዋል።

2.  ወገኔ ሆይ! ንብረትህን ጠብቅ።

ሩቅ ብቻ አትመልከት። እዚያው በዙሪያህ ለዘረፋ ተደራጅተው ከግለሰብ ንብረት እስከ ተቋም ሲዘርፉ የነበሩ እንደነበሩ ይታወቃል። ዛሬም ይኖራሉ። ፍሪጅና ቴሌቪዥን ሳይቀር በግመል እየጫኑ የወሰዱ የገጠር ሰዎች እንዳሉ ሰምቻለሁ። “መብራት የላችሁ ምን ያደርግላችኋል?” ሲባሉ “እንሸጠዋለን” ሲሉ ነበር። ስለዚህ ቅድሚያ ለህይወት ጥንቃቄ ካደረግክ በኋላ በቅርብህ ሆነህ በተቻለህ መጠን ንብረትህን ተደራጅተህ ጠብቅ።

3.  ወገኔ ሆይ! ለፈተና እራስህን አዘጋጅ!

ወደድንም ጠላንም ፈተና ላይ ነው ያለነው። መጠኑ ከህዝብ ህዝብ በእጅጉ እንደሚለያይ ግልፅ ነው። ፈተናው ምን ያህል እንደሚዘልቅም አናውቅም። የሆነች ያክል የምንዘጋጅባት ሰበብ ካለችን ባለችን መጠን ለሚመጣው ሁሉ ራሳችንን እናዘጋጅ። ምግቡ፣ ወፍጮው፣ ባንኩ፣ መብራቱ፣ ቴሌው፣ መድሃኒቱ፣ ... ብዙ ነገር ይቸግራል። እስካሁንም ብዙ የተፈተነ አለ። ልዩነቱ ብዙ ባይሆን እንኳ የተዘጋጁበትና የተዘናጉበት ፈተና አንድ አይደለም። አላህ ለሁሉም ፈረጃውን ያቅርብልን።

4.  ወገኔ ሆይ! ጊዜ አይተህ አትለወጥ!

ለሚያልፍ ቀን ትዝብት ላይ አትውደቅ። የትኛውም ቡድን አጠቃኝ በሚል ማመሃኛ ማንንም ብሄር ለይተህ እንዳታጠቃ። የአማራ ህዝብ ሆይ! ህወሓትን መነሻ አድርገህ ለፍቶ አዳሪ ትግሬን አታጥቃ። “ያው ናቸው” ከሚል ስሜት ወለድ ሂሳብ ራቅ። “ህወኃት እከሌን አካባቢ የተቆጣጠረው ተፈናቃይ ትግሬዎችን ተጠቅሞ ነው” እየተባለ የሚናፈሰው ብታምንም ባታምንም ከንቱ ውሸት ነው። እንዲህ አይነት አሉባልታ ይዘህ ደካሞችን እንዳትጎዳ።
ትግሬው ሆይ! ህወኃት ሲገባ ጠብቀህ አደባባይ ለጭፈራ አትውጣ። ጠቋሚ፣ አፋኝ፣ አሳፋኝ ለመሆን አትሞክር። ሃይማኖት ወይም ሞራል እንኳ ባይገታህ ቢያንስ ለራስህ ፍራ! ነገሮች የተቀያየሩ እለት መግቢያ ታጣለህ። በባለፈው ግጭት አማራውም፣ ትግሬውም፣ ኦሮሞውም፣ አፋሩም ዘንድ ብዙ ደስ የማይሉ ነገሮች ሲወሩ ነበርና አላህን ልንፈራ ይገባል።

5.  ወገኔ ሆይ! ለመጣ ለሄደው አታጨብጭብ።

አንድ ኃይል አንድን አካባቢ ሲቆጣጠር ሆ ብሎ መውጣት፤ ሌላው በግሩ ሲተካ አሁንም ሆ ብሎ መነሳት ይሄ ግልብነት ነው። የሃገራችን ፖለቲካ ቂመኛና ተበቃይ ነው። እንኳን የገባበትን፣ የሌለበትንም ጊዜ ተጠግቶ ያጠቃል። ደግሞም በጣም ተገለባባጭ ነው። እዚች አገር ውስጥ ስንት አይሆንም የተባለ ነገር ሆኗል! መንግስት ትግራይን ሲቆጣጠር ህወኃት ዳግም ያንሰራራል ብሎ የገመተ አልነበረም። ህወኃት ሰሜን ሸዋ ከደረሰ በኋላ በዚያ አሰቃቂ ሁኔታ ይመለሳል ብሎ የገመተም አልነበረም። ስለሆነም ጥንቁቅ መሆን ያስፈልጋል። በሁለቱም አይንህ ዛሬ ላይ ብቻ አታፍጥጥ። በአንድ አይንህ ነገን ተመልከት።

6.  ወገኔ ሆይ! ህይወት አትርፍ።

አጋጣሚዎችን ተጠቅመው የሚጠሉትን ለማጥቃት የማያመነቱ እርኩስ ፍጡሮች ይኖራሉና ቢቻልህ ያለ ጥፋታቸው የበደለኞች ሰለባ ሊሆኑ የሚችሉ ወገኖችን አትርፍ። ከጎናቸው ቁም። በባለፈው ግጭት ህወኃት ሲገባ ጠብቀው ደካሞችን ያጠቁ ሰዎች አሉ። ከነሱ አንፃር ሲታይ ህወኃት በጣም የተሻለ ነበር። መረጃ ያለው ሰው የምለው ይገባዋል። ህወኃት ከወጣ በኋላም እንዲሁ ከየትኛውም ኃይል ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌላቸው ምስኪኖች ተጎድተዋል። ከተቻለን ጊዜ አይተው ከሚያጠቁ ነውረኞች አንድ ነፍስ እንኳ ብናተርፍ ዋጋው የትና የት ነው!! በቅርቡ ኦሮሚያ ውስጥ በነበረውን ግጭት የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው አማራዎችን ያተረፉ ስንት ኦሮሞዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። አማራ ውስጥ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው ትግሬዎችን ያተረፉ ስንት አማራዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው አማራዎችን ያተረፉ ስንት ትግሬዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። ሰው ማለት፣ ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋለት!

7.  ወገኔ ሆይ! ወቅታዊ ግጭቶችንና ተያያዥ ጉዳዮችን ከሃይማኖት ጋር እንዳታጠላልፍ።

የየትኛውም ቡድን ደጋፊ ልትሆን ትችላለህ። የኔ የምትለው ወገን ከሌሎች በተለየ እንደተገፋ ሊሰማህ ይችላል። ግን እወቅ! ሌሎችም መሰል ህመም አላቸው። ቢቻል በፖለቲካውም ሞራል ግብረ ገብነት ቢኖርህ እሰየው። ያለበለዚያ ግን የሃይማኖት ተቋማትም፣ አስተማሪዎች እና የደዕዋ መድረኮችም አንተ በምትፈልገው መልክና መጠን እንዲያወሩ፣ የፖለቲካ ፍጭቶች ማራገፊያ እንዲሆኑ አትፈልግ። ማህበራዊ ሚዲያዎችም ላይ ሆነ መሬት ላይ እየተከተልክ በአክቲቪስት ቋንቋ እንዲያወሩ አጉል አትወትውት። ልትረዳ ቢያቅትህ ቢያንስ አደብ ይኑርህ። ከፖለቲከኛ ጋር የለመድከውን እሰጥ አገባ በየደረስክበት አትድፋ።

8. የሃይማኖት አስተማሪ ሆይ! ከመንጋው ተለይ!

ብሄርህን ተከትለህ ቅስቀሳ ውስጥ አትግባ። ሌላው አካል ለጦር ቢቀሰቅስ አንድ ሁለት ነገር ተመልክቶ ነው። አንተ ተጨማሪ አርቀህ የምትመለከትበት አላህን መፍራቱ ሊኖርህ ይገባል። ያለበለዚያ በምንህ ነው ከሌሎች የምትለየው? ኢን ሻአላህ ነገ ሰላም ይመጣል። እሱን ታሳቢ አድርግ። መንጋው ሊያግባባህ፣ ሊገፋፋህ፣ አልሆን ሲለው ሊያወግዝህ ይችላል። የፈለገውን ይበል እሱ በቀደደው አትፍሰስ። የሃይማኖት አስተማሪ ሆነው በቀጥታ የግጭት ተሳታፊ፣ ወይም ቀስቃሽ፣ ወይም ደጋፊ፣ ወይም የዘር ጥላቻ ጠማቂ የሆኑ መርዘኛ ሰባኪዎች ሁሉም ብሄር ጋር አሉ። እነዚህ አካላት ነገ ችግሩ ቢያልፍ እንኳ የማያልፍ ጠባሳ እየጣሉ ነው። ጦሳቸውም ከራሳቸው አልፎ ለህዝብ ይተርፋል። ከሃይማኖትህ ተማር። እስካሁን ካለፈው ተማር። ከሌሎች ድክመት ተማር። የትኛውንም ውሳኔ ብትመርጥ ከትችት ላታመልጥ ነገር የሰው ስሜት ተከትለህ እንዳትወስን። አላህን አስብ።
በመጨረሻም አደራ የምለው እንተዛዘን፣ እንተሳሰብ፣ ዱዓእ እናድርግ፣ ወደ ጌታችን እንመለስ። አላህ ከገባንበት መከራ አውጥቶ የሰላም አየር የምንተነፍስ ያድርገን። ኣሚን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
734 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:19:51 የምወድሽ ሰለፊያ አውላላ ነሽ ወሰጢያ
ስቶሽ ሂዷል ሀዳዲያ አልነካሺም ኢኽዋኒያ

ማቱሪዲም አሽዓሪያ ሙዕተዚላም ኻሪጂያ
ሽዓም ቢሆን ራፊዲያ አልነካሺም ወሰጢያ

ወሰጢያ

ወሰጢያን ያልያዘ ሰው
ለሱ ማልቀስ ምን አነሰው?

ቁርአን ሐድስ እንደሌለው
ጠርዝ ረግጦ እባብ በላው


t.me/mrkezu_Selefiyah
1.2K views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:57:09 #የኪሳራ_ሁሉ_መነሻ_የሁኑ_ሁለት_ኪሳራዎች_የልብ_ኪሳራና_የጊዜ_ኪሳራ_ናቸው

قال الإمام ابن القيم   رحمه الله

ኢብኑል ቀይም እንድህ ይላሉ

أعظم الإضاعات  إضاعتان

ከማባከኖች ሁሉ ታላቁ ማባከን ሁለት አይነት ብክነቶች ናቸው

         هما أَصل كل إضاعة

እነዚያ ሁለቱ ደግሞ የማባከን ሁሉ መነሻዎች ናቸው

إضاعة القلب
①ልብን ማባከን  ሲሆን
وإضاعة الوقت
②ጊዜን ማባከን ናቸው

فإضاعة القلب مِن إيثار الدنيا على الآخرة

ልብን(ቀልብን)ማባከን ዱንያን ከአኺራ ከማስበለጥ የሚመጣ ሲሆን

وإضاعة الوَقت مِن طُول الأمل

ጊዜን ማባከን ደግሞ (የመኖር)ተስፋን ከማስረዘም የሚመነጭ ነው።

فاجتَمع الفساد كله في اتِباع الهوى وطُول الأمل

ሁሉም የብክለት አይነት ስሜትን በመከተልና ተስፋን በመለጠጥ ላይ ተከማችቷል።


والصلاح كله فى اتِباع الهدى والاستعداد للقَاء

ሁሉም መስተካከል ደግሞ ቅኑን መንገድ በመከተልና ለጌታ መገናኘት በመሰናዳት ላይ ተከማችቷል።


والله المستعان!  [ الفوائد ( ص١١٢ )

t.me/mrkezu_Selefiyah
t.me/mrkezu_Selefiyah
1.2K viewsedited  18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:57:09 እወቅ ተማር አውቆ ተምሮ የተወለደ የለም

تعلم فليسَ المرءُ يولدُ عالماً
وَلَيْسَ أخو عِلْمٍ كَمَنْ هُوَ جَاهِلُ


وإنَّ كَبِير الْقَوْمِ لاَ علْمَ عِنْدَهُ
صَغيرٌ إذا الْتَفَّتْ عَلَيهِ الْجَحَافِلُ

 

وإنَّ صَغيرَ القَومِ إنْ كانَ عَالِماً
كَبيرٌ إذَا رُدَّتْ إليهِ المحَافِلُ

 

اصبر على مرِّ الجفا من معلمٍ
فإنَّ رسوبَ العلمِ في نفراتهِ

 

ومنْ لم يذق مرَّ التعلمِ ساعة ً
تجرَّعَ ذلَّ الجهل طولَ حياته

 

ومن فاتهُ التَّعليمُ وقتَ شبابهِ
فكبِّر عليه أربعاً لوفاته

 

وَذَاتُ الْفَتَى ـ واللَّهِ ـ بالْعِلْمِ وَالتُّقَى
إذا لم يكونا لا اعتبار لذاتهِ

t.me/mrkezu_Selefiyah
974 views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:29:42 * على كل أحد بذل جهده واستطاعته في معرفة ما جاء به محمد ﷺ.*

قال ابن تيمية رحمه الله :

فبمحمد -ﷺ- تبيّن الكفر من الإيمان ، والربح من الخسران والهدى من الضلال، والنجاة من الوبال ، والغي من الرشاد، والزيغ من السداد، وأهل الجنة من أهل النار ، والمتقون من الفجار و ایثار سبيل من أنعم الله عليهم من النبيين والصديقين والشهداء والصالحين ، من سبيل المغضوب عليهم والضالين.

• فالنفوس أحوج إلى معرفة ما جاء به واتباعه منها إلى الطعام والشراب ، فان هذا إذا فات حصل الموت في الدنيا. وذاك إذا فات حصل العذاب.

• فحُقّ على كل أحد بذل جهده واستطاعته في معرفة ما جاء به وطاعته ، إذ هذا طريق النجاة من العذاب الأليم والسعادة في دار النعيم.

• والطريق إلى ذلك الرواية والنقل . إذ لا يكفي من ذلك مجرد العقل . بل كما أن نور العين لايرى إلا مع ظهور نور قدامه ، فكذلك نور العقل لا يهتدى إلا إذا طلعت عليه شمس الرسالة.

•  فلهذا كان تبليغ الدين من أعظم فرائض الإسلام، وكان معرفة ما أمر الله به رسوله واجبا على جميع الأنام 

مجموع الفتاوى (١\٥)

t.me/mrkezu_Selefiyah
t.me/mrkezu_Selefiyah
998 viewsedited  08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:56:49 ማን ማንን ይጎዳል አሏህ እንጂ

قال ابن القيم(رحمه الله تعالى)

ኢብኑል ቀይም እንድህ ይላሉ

‏"لا يغرّك المادحون و لا يضرك القادحون..

"አወዳሾች ሊሸነግሉህ አነዋሪዎች ሊጎዱህ አይገባም"

አሏህ እንዲህ ይላል

قال تعالى

{بَلِ الْإِنسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ}

በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡

https://t.me/abumuazhusenedris
1.1K views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 15:54:24 ተውኩት ሳልናገር ለሰው ሳላወራ
ብሄድ ይሻለኛል በሰለፍ አሻራ
"
ዝምታን መረጥኩኝ ለሰው ከማወራ
አጉል ላያምኑልኝ ከማጋባ ግራ
"
በጣሙን ይገርማል የኢኽዋኖች ፊክራ
እየሱስ ጌታ ነው ብሎ አጋባን ግራ
"
አትለው ያመነ አትለው አፈንጋጭ
ልቡ ያመጣውን በአፉ ሚያመነጭ
"
አንተ ቅቤ ጠባሽ ኢሳ ጌታ አይደለም
ከኩፍር ካልቶበትክ ቅጣት ነው ዘላለም
"
አንት የሰው ማፈሪያ ኢስላም አሰዳቢ
የስልጣን እጮኛ የነሷራ ዋቢ
"
አንተ ብሎ ኡስታዝ አንተ ብሎ መሪ
በነጋ በመሼ ኩፍር ተናናጋሪ
"
የፈጣ ልጅ ነን ብለህ ተናገርከው
ሱፊይ እንኳ ደፍሮ የማይናገረው
"
ስማማ
ስማማ ልንገርህ የሁዳ የካደው
የፈጣሪ ልጅ ነን ብሎ በማለት ነው
"
እኔን ያሳዘነኝ አላዋቂው ህዝብህ
በጭፍን ሲከተል በታላቅ ሰው ስሎህ
"
ታው አንተ ሰው ቶብት ተመለስ በጧቱ
ቀብር ውስጥ ስትገባ ሳይጠፋህ ብልሃቱ
"

ከቆዩ ግጥሞች ውስጥ

t.me/abumuazhusenedris
1.4K viewsedited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:31:59 ታጠቅ የዩቱብ ሚዲያ ዘጋቢ ዜና እየሰራ አዛን ሲሰማ አቆመው

አንዳንዴ በጣም አስገራሚ ነገሮች ካልጠበቅንው አቅጣጫ እናገኛለን

ማንኛውም ሰው የሸሪዓን መገለጫዎች ሲያከብር ስታየው ከልቡ ውስጥ የተወሰነ የተቅዋ ቁራጭ እንዳለው ማሳያ ነው።

ذلك ومن يعظم شعائر الله فإنها من تقوى القلوب

የሸሪዓ መገለጫዎችን የሚያከብር ሰው ትልቅ የሆነ እድል ተችሮታል ዛሬ ላይ ስንቱ ነው ሸሪዓን ማክበሩ ቀርቶ በሸሪዓ ሚያላግጠው?።

አሏህ ጥቅልል አድርጎ የሸሪዓ ተንከባካቢ ያድርገን

t.me/abumuazhusenedris
1.4K viewsedited  03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 13:59:57 خطبة الجمعة


የጁሙዓ ኹጥባ
خطر الشرك وأهمية التوحيد

የሽር አደገኝነትና የተውሒድ አሳሳቢነት

لا سيما ما يفعل فى شهر أغسطس من الشرك والشعوذة

በተለይም በንሓሴ ወር የሚሰራ ሽርክና ማጭበርበር ተጠቅሶበታል


በውስጡ ከተዳሰሱት ነጥቦች ቋጉሜ የሚባል ነገር በሸሪዓ አለ ወይ

እውነት ቋጉሜ የአንድ ወር ያህል አገልግሎት አላትን?

በቋጉሜ 3 ዝናብ ከጣለ የእባቦች አይን ይጠፋል የሚሉት ከምን ይዘው ነው?

መስከረም አንድስ ፌጦ መብላት ከምን ይዘው ነው

#አቡ_ሙኣዝ_ሐሰን_ኢድሪስ_ኣሉ_አባድር
t.me/abumuazhusenedris
1.6K viewsedited  10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ