Get Mystery Box with random crypto!

ተውኩት ሳልናገር ለሰው ሳላወራ ብሄድ ይሻለኛል በሰለፍ አሻራ ' ዝምታን መረጥኩኝ ለሰው ከማወራ አ | አቡ ሙዓዝ (ሐሰን ኢድሪስ)

ተውኩት ሳልናገር ለሰው ሳላወራ
ብሄድ ይሻለኛል በሰለፍ አሻራ
"
ዝምታን መረጥኩኝ ለሰው ከማወራ
አጉል ላያምኑልኝ ከማጋባ ግራ
"
በጣሙን ይገርማል የኢኽዋኖች ፊክራ
እየሱስ ጌታ ነው ብሎ አጋባን ግራ
"
አትለው ያመነ አትለው አፈንጋጭ
ልቡ ያመጣውን በአፉ ሚያመነጭ
"
አንተ ቅቤ ጠባሽ ኢሳ ጌታ አይደለም
ከኩፍር ካልቶበትክ ቅጣት ነው ዘላለም
"
አንት የሰው ማፈሪያ ኢስላም አሰዳቢ
የስልጣን እጮኛ የነሷራ ዋቢ
"
አንተ ብሎ ኡስታዝ አንተ ብሎ መሪ
በነጋ በመሼ ኩፍር ተናናጋሪ
"
የፈጣ ልጅ ነን ብለህ ተናገርከው
ሱፊይ እንኳ ደፍሮ የማይናገረው
"
ስማማ
ስማማ ልንገርህ የሁዳ የካደው
የፈጣሪ ልጅ ነን ብሎ በማለት ነው
"
እኔን ያሳዘነኝ አላዋቂው ህዝብህ
በጭፍን ሲከተል በታላቅ ሰው ስሎህ
"
ታው አንተ ሰው ቶብት ተመለስ በጧቱ
ቀብር ውስጥ ስትገባ ሳይጠፋህ ብልሃቱ
"

ከቆዩ ግጥሞች ውስጥ

t.me/abumuazhusenedris