Get Mystery Box with random crypto!

The Motivator

የቴሌግራም ቻናል አርማ the_motivators — The Motivator T
የቴሌግራም ቻናል አርማ the_motivators — The Motivator
የሰርጥ አድራሻ: @the_motivators
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 498

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-07-15 09:18:53 ደህና አደራችሁ

እንስቃለን እንጂ ሁላችንም ድብቅ ህመም አለብን!!! ሌት ተቀን የሚጠዘጥዘን ያለፈው የህይወት አቦራ በትዝታ እየነፈሰ አይናችንን ዕንባ የሚያስቋጥረው ስንት ነን?
ከሰላምታችን ጀርባ ሰላም ማጣታችን እደተራራ ይገዝፋል የምንወደው ሰው ከምንወደው በላይ ብልጠት አጥቅቶት ያለመታመንን በለስ ጎርሶ የመወደድን ፀጋ እንድናጣው ካለማመን ምድር የተወረወርን ስንት አለን?
የነገ ተስፋችንን የእናታችንን ሳቅ አርገን ግዜ የቀደመን ስንቶች ነን? ስንቶች የወዳጆቻችንን ፎቶ ሰቅለን በቁጭት እያነባን ይሆን? ቤተሰባችን ሲናፍቁን የዕንባ ቧንቦችን ከፍተን ፊታችንን የምናጥብ ስንት አለን? መታመማችን ሳያንስ በህመማችን ለሚጨነቁ የምናዝን ግራ የሚገባን ሞታችንን አቅርበው የምንል ስንቶች ኖረን ይሆን? ሲቃ እየተናነቅን ፈገግ የምንል እሾሁን ጨብጠን የምንስቅ?
ስንቶቻችን ነን?????

መልካም ውሎ!!

@the_motivators
@the_motivators
47 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:17:28 #ምክንያት_አትጠይቂኝ

እሷ፡- ለምን ወደድከኝ? ለምን አፈቀርከኝ?
እሱ፡- ምክንያቱን መናገር አልችልም፤ ነገር ግን የእውነት
እወድሻለው፡፡
እሷ;- ምክንያትህን እንኳን መናገር ሳትችል እንዴት
እወድሻለው፤ አፈቅርሻለው
ለማለት ቻልክ?
እሱ፡- እውነት ለምን እንደወደድኩሽ አላቅም ግን
እንደምወድሽና እንደማፈቅርሽ
ማረጋገጥ እችላለው፡፡
እሷ:- ማረጋገጥ? አይሆንም፤ ለምን እንዳፈቀርከኝ
ምክንያቱን ነው የምፈልገው፡፡
የጓደኛዬ ፍቅረኛ ለምን እንዳፈቀራት ነግሯታል፤ አንተ ግን
ምክንያትህን
አታቀውም፡፡
እሱ፡- እሺ እሺ በቃ እነግርሻለው፡፡ ምክንያቱም ቆንጆ
በመሆንሽ፤ ለጆሮ
በሚለሰልሰው ድምፅሽ፤ እና ስለምትንከባከቢኝ፤ መልካም
አሳቢ ስለሆንሽ፤
በሚያምረው ፈገግታሽ፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴሽ
ምክንያት አፈቅርሻለው፡፡
ልጅቷ በልጁ ምላሽ በጣም ረካች፤ እጅግም ደስ አላት፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ከቀናቶች በኃላ ልጅቷ አደጋ ደርሶባት
# ኮማ ውስጥ ገባች፡፡
መንቀሳቀስ አትችል፤ ማውራት አትችል፤ መሳቅ አትችል፤
ዝም ብቻ፡፡
ልጁ ደብዳቤ ፅፎ እያለቀሰ ከጎኗ አስቀምጦሏት ወጣ፡፡
ደብዳቤውም እንደዚህ
ይላል፡፡
"የኔ ውድ በሚለሰልሰው ድምፅሽ ምክንያት አፍቅሬሻለው፤
አሁን ግን ማውራት
ትችያለሽ? አትችይም፤ ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችልም፡፡
ስለምትንከባከቢኝ እና ስለምታስቢልኝ አፍቅሬሻለው፡፡
አሁን ግን ይህን ማድረግ
አትችይም፤ ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችልም፡፡
በፈገግታሽ ምክንያት አፍቅሬሻለው፤ በእያንዳንዱ
እንቅስቃሴሽ ምክንያት
አፍቅሬሻለው፡፡ አሁን መሳቅ ትችያለሽ? መንቀሳቀስ
ትችያለሽ? አትችይም፡፡
ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችልም፡፡
ፍቅር እውነት ልክ እንዳሁኑ ምክንያት ካስፈለገው ከአሁን
በኃላ አንቺን ላፈቅር
የምችልበት አንድም ምክንያት የለኝም፡፡
ፍቅር ምክንያት ይፈልጋል? አይፈልግም፡፡ ስለዚህ ዛሬም
እንደትናንቱ ካለምንም
ምክንያት አፈቅርሻለው፡፡ ከዘላለሙ ፍቅሬ ጋር ሁሌም
ያንቺ ብቻ ነኝ፡፡" ይላል
ደብዳቤው
መልክሽን አይቶ ያፈቀረሽ መልክሽ የጠፋ እለት የእሱም
ፍቅር አብሮ ይጠፋል፡፡
አንተም እንደዛው ወንድሜ ሀብትህን አይታ ያፈቀረችህ
ካዝናህ ባዶ የሆነ ቀን
የእሷም ልብ ለፍቅር የማይሆን ባዶ ዋሻ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡
ፈጣሪ እውነተኛ ፍቅርን ይስጠን፡፡

@the_motivators
@the_motivators
44 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:10:51 አንተን ሰው ያጣሀል እንጂ አንተ ሰው አታጣም መቼም ቢሆን ለተራ ስብራት ራስህን ዝቅ አታድርቅ ነገ የባሰ ፈተናዎች ይገጥሙሀልና ጉልበትህን ቆጥብ የሰው መኖር ትርጉም ተስፋ ማረጉ ነውና ተስፋህን በፈጣሪ አድርግ

መልካም ቀን
@the_motivators
@the_motivators
43 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 19:00:41


ይህንን ያውቃሉ

ቴሌግራም ላይ በአንድ ላይ የተላኩ ባንዲራዎችን ስትነኩ ቴሌግራማችሁ ለሰከንዶች ይበላሻል (ስልካችሁ ለሰከንዶች Stack አድርጎ ይቆያል) የሚሰራው Android ስልኮች ላይ ብቻ ነው ።

መሞከር ከፈለጋችሁ ከላይ ያለውን ባንዲራውን ንኩት ..... ከተበላሸ ለማስተካከል ቴሌግራማቹን Close app በሉት እና መልሳቹ ክፈቱት ።

@the_motivators
@the_motivators
144 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, edited  16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 20:05:12 ምስጋና እና ደስታ!

ዕድሜያችን አጭር ናት፤ በዚህ ሰዓት የሚያሳዝኑህን የሚያናድዱህን ጉዳዮች ንገረኝ ብልህ ብዙ እንደምትዘረዝር አውቃለው። አስቂኙ ነገር የተሰጠህ ዕድሜ የሚያስደስቱህን ነገሮች እንኳን አጣጥመህ ለመጨረስ አይበቃም!

ታዲያ ለምንድነው ለደስታ እንኳን የማይበቃ ጊዜህን በሀዘንና ጭንቀት የምታጣብበው? "ያንተን ወጣትነት እኮ የጨረጨሰ ንጉስም ይቀናበታል" ይለናል ደራሲ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር። አንዳንድ ነገሮች እንደነበረህ ራሱ የምታውቀው ከእጅህ ሲያመልጥህ ነው፤ ወዳጄ አሁን ላንተ የሚመጥንም ምስጋና እና ደስታ ብቻ ነው!

ደስታ የሞላበት ህይወት ተመኘንላችሁ

@the_motivators
@the_motivators
142 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 14:15:34 ለምን ይሆን?
አንተ በውድ ሆስፒታል ተወልደህ ይሆናል፣ እኔ በቤት ውስጥ ተወልጄአለሁ፤ ሁለታችንም በህይወት እየኖርን ነው።
አንተ በግል ትምህርት ቤት ተምረህ ይሆናል፣ እኔ በመንግስት ትምህርት ቤት ተምሬአለሁ፤ ሁለታችንም በአንድ ዩንቨርስቲ ጨርሰናል።
አንተ ከምቹ አልጋ ላይ ከእንቅልፍህ ነቅተህ ይሆናል፣ እኔ ከመሬት ላይ፤ ሁለታችንም የሰላም ሌሊት አሳልፈናል።
አንተ የለበስካቸው ልብሶች ውብና ውድ ይሆናሉ፣ የኔ ቀላልና ርካሽ ናቸው፤ ሁለታችንም ራቁትነታችንን ሸፍነናል።
አንተ ብዙ የምግብ ዐይነቶችን ከጥሩ መስተንግዶ ጋር አማርጠህ በልተህ ይሆናል፣ እኔ ቤት ያፈራውን ወስጄ በልቻለሁ፤ ሁለታችንም ግን የምግብ ፍላጎታችንን ለማርካት ስንል ተመግበናል።
አንተ Land Cruser TurboV8፣ Range Rover፣ Lexus Jeep፣ Hummer Jeep ወይንም G Wagon...መኪና ትነዳ ይሆናል፣ እኔ የህዝብ ትራንስፓርት እጠቀማለሁ፤ ሁለታችንም ግን ወደፈለግንበት መዳረሻ ደርሰናል።
ምናልባት ይሄንን ልጥፍ (post) እያነበብክ ያለኸው፤ በSamsung Galaxy 8Edge፣ በiPhone7s+፣ በSony Xperia፣ በGoldvish Le Million ወይንም በVertu Signature Cobra...ስልክህ ታግዘህ ይሆናል፣ እኔ ይህንን የምፅፈው ስክሪኑ በተሰበረ ስልኬ ቢሆን እንኳ ሁለታችንም መልእክቱ እኩል ይታየናል።
ይሀውልህ፤ በአእርግጥ ህይወት የፉክክር መድረክ ነች።ነገር ግን ነገሮችን ለማሳካት ብዙ መንገዶች ቢኖሩ እንኳ ሁሉም የህይወት መስመሮች የሚመሩን ወደ አንድ አቅጣጫ ነው። ይኸውም- ሞት። ደግሞ ደስታ ሁሉንም ነገር በማግኘት ውስጥ አይመጣም፣ ካለህ ነገር ውስጥ መልካሙን በማውጣት እንጂ። ትልቁ ቁምነገር ያለው ራስህን የምታይበት መነጽር ነው። ደስታ ማለት የምትወደውን ማግኘትም አይደለም፣ ደስታ ማለት ያገኘኸውን በቂ ነገር መውደድ ነው። ልብ በል፤ ያንተ በዚህ አለም መኖር የሚያስደስተው ሌላውን ሲሆን አንተን የሚያስደስትህም የሌላው መኖር ነው።
የትላንት ትላንት ምንም አልነበረህም፤ ምንም ሳትይዝ፣ ራቁትህን ነው ይችን ዓለም የተቀላቀልከው፤ ይሁንና ትላንት ያጣኸውን ዛሬ አግኝተሃል፣ ዛሬ ያጣኸውን ነገ ታገኘዋለህ፣ ሁሉንም ደግሞ የነገ ነገ ታጣዋለህ። ባጭሩ አንድ ቀን ሁሉንም ትተህ ትሞታለህ።
ከሞትክ በኋላስ?
ከ3 ቀን በኋላ የጣቶችህ ጥፍሮች መወዳደቅ ይጀምራሉ። ከ4 ቀን በኋላ የራስ ቅልህና ሰውነትህ ላይ ያሉ ጸጉሮች በሙሉ ይረግፋሉ። ከ5 ቀን በኋላ አንጎልህ መርገብ ይጀምራል፣ የሰውነትህ ሥጋ ይጠወልጋል፤ መቀመጫህ፣ ጡትና ኃፍረተ-ስጋህ ይበሰብሳል። ከ6 ቀን በኋላ ቆዳህ መሳሳትና ቀስ በቀስም ከአጥንትህ ላይ መለያየት ይጀምራል። ከ7 ቀን በኋላ ሆድህ ይቀልጣል፣ መጥፎ ጠረንም ማውጣት (radiate ማድረግ) ይጀምራል። ከሞትክ ከ60 ቀን በኋላ መላው የሰውነትህ አካል ወዳልነበር ይለወጥና "አንተ" ማለት "አጥንት" ብቻ ትሆናለህ።
ታዲያ፤
• ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ትእቢት?
• ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ራስ ወዳድነት?
• ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ክርክር፣ ጭቅጭቅና ንትርክ?
• ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ቅናት?
• ለምንስ ይሆን ይሄ ሁሉ ጥላቻ?
• እኮ ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ የክፋት ሥራ?
ጥለህ ለምትሄደው አለም?!። እስኪ ለሞት ሩብ ጉዳይ እንደቀረው ሰው እንኑር። ደሃ ሃብታም እያልክ ሳታደላ፣ የተማረ ያልተማረ ብለህ ሳትለይ፣ መልከ መልካም መልከ ጥፉ ሳትል፣ ባለስልጣን ተራ ሰው ብለህ ሳትመርጥ...ሁሉንም በሰው'ነቱ እኩል- ተመልከት፣ ስማ፣ እርዳ፣ አድን

@the_motivators
@the_motivators
304 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 21:58:06 የሁለት ደቂቃ ንባብ

አትተርጉሙ!
አንድ አባት ከልጆቹ ጋር ወደ አንድ ካፌ ይገባል።ካፌው ውስጥ እንደገቡ ብዙም ሳይቀመጡ ልጆቹ መሯሯጥና እየተጯጯሁ መጫወት ይጀምራሉ።ይሄ ሁሉ ሲሆን አባት አንገቱን ደፍቶ በሀሳብ ጭልጥ ብሏል።ይሄን ሁሉ የሚመለከት አንድ ሰው በልጆቹ እንቅስቃሴ ተረብሾ ልጆቹን ስርአት የማያስይዝ ምን አይነት ቸልተኛ ሰው ነው እያለ በአባታቸውን ይናደዳል።በዚህ ብስጭት ውስጥ ሆኖ የሚሯሯጡት ልጆች ድንገት የእሱን ጠረጴዛ ነክተውት ኖሮ ያዘዘው ሻይ ልብሱ ላይ ተደፋ።ይሄን ጊዜ ንዴቱን መቋቋም አቅቶት ውደ አባትየው ሄደ።ለግጭት እየተጋበዘ ሊያንቀውም እየዳዳው”ምን አይነት የማትረባ ሰው ነህ?ልጆችህን ስርአት አታስይዝም?”ብሎ አምባረቀበት።አባትየው በረጅሙ ተንፍሶ በተረጋጋ አንደበት”ወዳጄ የልጅነት ሚስቴ የልጆቼ እናት ታማ ከምትረዳበት ሆስፒታል አሁን ከመግባታችን ተደውሎ መሞቷን ነገሩኝ።ምን ማድረግ እንዳለብኝና ለልጆቼ ምን እንደምል ግራ ገብቶኛል”አለው።ይሄን የሰማው ሰው በትልቅ ድንጋይ እንደተመታ ሰው ራሱን አመመው።

በህይወታችን ከምንሰራቸው ስህተቶች ውስጥ አንዱ ስለ ሁኔታዎች በቂ ግንዛቤ ሳይኖረን በራሳችን መተርጎምና መፈረጅ ነው።ሰዎች የሆነ ነገር ሲያደርጉ ስለማይወደኝ ነው፣ ስለማያከብረኝ ነው፣ ስልክ ሳያነሱ ወይ የሆነ ነገር ሲያደርጉ ሲቀሩ ደግሞ ሆም ብለው ነው ብለን በራሳችን እንተረጉማለን።የትርጉም ዋናው መዘዝ ከእውነታው አለም ያወጣንና የራሳችንን አለም እንደንፈጥር ያደርገናል።በህይወት ያሉትን ሰዎች እንገላቸውና ክፉ ናቸው አያከብሩኝም የምንላቸውን የራሳችንን ሰዎች በአዕምሯችን እንፈጥራለን።ሀሳባችንን ፊት ለፊት የመናገር ልምድ ስለሌለን በራሳችን ትርጉም በውስጣችንን እንበሰለሰላለን እንጎዳለን።መፍትሄው ምንድን ነው?

1.ምቾት ያልሰጡን ነገሮች ሲኖሩ በራሳችን ከመተርጎም ይልቅ ፊት ለፊት መጠየቅን እንለማመድ።

2.ያሰብኩትና የተሰማኝ ሁሉ ትክክል ነው ማለትን እናቁም።

3.ሰዎች በብዙ ችግርና ውስብስብ የህይወት መንገድ ያልፋሉና ለመረዳት እንሞክር።በዚህ መልኩ ጤናማ ግንኙነታችንን ማዳበር እንችላለን።

@the_motivators
@the_motivators
344 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 17:38:23 #ደስ_የሚል_ታሪክ
"መልካምነት መልሶ ይከፍላል"
አንድ ወጣት የዩንቨርስቲ ተማሪ ከፕሮፌሰሩ አስተማሪው ጋር መናፈሻው ላይ ቁጭ ብለው ያወራሉ ። አስተማሪው ከተማሪዎች ሁሉ ይህን ተማሪ በጣም ስለሚወደው እንደጓደኛው አድርጎ ነው ሚያየው ።
ፊት ለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻን ጽዶችና ሣሮችን የሚያስተካክል ሰራተኛ አለ፣ ተማሪው የጽዳት ሰራተኛውን እያየ ለአስተማሪው “ ቲቸር ዛሬ አንተም እኔ ደብሮናል ለምን ያኛውን ሰውዬ ትንግርት አንሰራውም?ያወለቀውን ጫማ ደበቅ እናርግና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት እንደሚበረግግ እኛም እዛጋ ደበቅ ብለን እንመልከተው” ይለዋል።
አስተማሪውም “ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን ድሀዎችን እያሰቃየን እኛ መደሰት የለብንም። ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን በገንዘባችን የበለጠ ደስታን ማግኘት እንችላለን ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬው ሳያይህ ባውለቀው ጫማዎች ላይ ገንዘብ ከተህበት ና ከዛም ተደብቀን የሚሆነውን እናያለን” አለው። ተማሪውም አስተማሪው እንዳለው ቀስ
ብሎ የሰውዬው ጫማ ላይ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣና ከአስተማሪው ጋር ደበቅ ብለው የሰውዬውን ሁኔታ መከታተል ጀመሩ።
ሰውዬው ጽዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና ጫማውን ለማድረግ ሲታገል ይቆረቁረውና ጎንበስ ብሎ ጫማውን ሲያራግፈው ብሮችን ያገኛል። ሰውዬው ደነገጠ !!
ዙሪያውን ቢያይ ማንም የለም ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራውን ቢመለከት ማንም ሰው የለም ። ሰውየው በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡን ኪሱ ውስጥ ከተተው በኋላ ሁለተኛ እግሩ ጫማውን ሊያደርግ ሲያነሳ በተመሳሳይ ገንዘብ ያገኛል ሰውዬው አላመነም !! በጉልበቱ ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አድርጎ ጮክ ብሎ“ጌታዬ የሚስቴን መታመም አውቀክ ነው አይደል?
ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳት አውቀክ ነው አይደል?
የልጆቼን ዳቦ ማጣታቸውን አይተህ ነው አይደል? ምስጋና ይግባህ ጌታዬ” አለ።ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከት ልቡን ነካው አይኑ እንቧ አቀረረች። አስተማሪውም “ቅድም ካሰብከው ትንግርት ይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንደፈጠረብክ አልጠራጠርም” አለው። ተማሪው እንቧውን እየጠረገ “ፕሮፌሰር እስካሁን ካስተማሩኝ ትምህርት ሁሉ እንደዚህ ያለ ልብ ሚነካ ትምህርት አስተምረውኝ አያውቁም በህይወቴ የማልረሳው ትምህርት ነው ያስተማሩኝ እውነትም ከመውሰድ መስጠት የተሻለ ነው”ብሎ መለሰላቸው።
"ደግ ደጉን እናስብ መልካምነት መልሶ ይከፍለናልና"


@the_motivators
@the_motivators
337 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 17:07:48 እውነታን የመቀበል ምርጫ

አንደኛው ምርጫህ በየጊዜው በመንገድህ ላይ የሚደነቀሩ በፍጹም ልታስወግዳቸው የማትችላቸውን እንቅፋቶች ሲታገሉ መኖር ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን እውነታን ተቀብለህ፣ ዝንባሌህንና መንገድህን በመቀየር መገስገስ ነው፡፡

ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1989 ዓ/ም በጸሐፊነቱና በቀስቃሽ ተናጋሪነቱ የታወቀው ዴኒስ (Dennis Waitley) ከሺካጎ ከተማ ወደ ሎስ አንጀለስ የሚሄደውን የበረራ መስመር ቁጥር 191 ለመያዝ በመንገድ ላይ እንዳለ ትንሽ በመዘግየቱ ምክንያት በረራው ለጥቂት ያመልጠዋል፡፡ በአየር ማረፊያው ደርሶ ለመግባት ሲጣደፍ አይኑ እያየ የመቀበያውን ደጆች ሲዘጉት ተመለከተ፡፡ የዘገየው ለጥቂት በመሆኑ ምክንያት ወደ በረራው ለመግባት እንዲፈቀድለት ቢማጸንም እንኳን ስላልተፈቀደለት በጣም ይበሳጫል፡፡ በዚያው ቀን ከምሳ በኋላ ዋና ተናጋሪ ሆኖ ሊቀርብበት የሚገባው ስብሰባ ቀጠሮ በዚህ ምክንያት ተበላሸበት፡፡

ከአካባቢው ዘወር በማለት በመነጫነጭ ላይ እያለ፣ ከሃያ ደቂቃዎች በኋላ አንድ ሰበር ዜና ቀልቡን ይስበዋል፡፡ ለጥቂት ያመለጠው በረራ ገና በመነሳት ላይ አያለ በመከስከሱ በውስጡ ያሉት ሰዎች በሙሉ መሞታቸውን ተመለከተ፡፡ ንዴቱና ቅሬታው ወደ ድንጋጤ፣ ወደ ኃዘንና በኋላም “በረራው እንኳን አመለጠኝ” ወደሚል ሃሳብ ተለወጠ፡፡

ከአየር ማረፊያው ወትቶ ሆቴል በመያዝ ወደ ክፍሉ ገብቶ አረፍ ለማለት ሞከረ፡፡ በእጁ ላይ ያለውን የበረራ ትኬት በመመለስ ገንዘቡን ከመቀበል ይልቅ ትኬቱን ለማስታወሻነት ለማስቀመጥ ወሰነ፡፡ ይህ ትኬት የዘወትር አስታዋሹ ሆነለት፡፡ በአንድ ነገር በሚበሳጭበት ጊዜ ሁሉ ባለቤቱ እጁት ትይዘውና ወደዚያ ለማስታወሻነት ወደተቀመጠ የበረራ መስመር ቁጥት 191 ትኬት በመውሰድ ሁሉም ነገር ለመልካም እንደሆነ ታስታውሰዋለች፡፡

ዴኒስ፣ “እያንዳንዱ ቀን በሙሉ ኃይላችን ልንኖረው የሚገባን ስጦታ ነው” ሲል ይደመጣል፡፡ በዚህም መልእክቱ፣ መለወጥ የማንችለውን እውነታ ከመታገል ይልቅ ለመኖር ስለተፈቀደልን ደስተኞች ልንሆን እንደሚገባን ያስታውሰናል፡፡

ልክ እንደ ዴኒስ ምንም ብታደርግ ልትለውጣቸው የማትችላቸው “አናዳጅ” ገጠመኞች ዘወትር ከመንገድህ ላይ አይጠፉም፡፡ እነዚህ በየጊዜው መንገድህ ላይ የሚደነቀሩና ካሰብከው ሩጫ የሚገቱህ ገጠመኞች የሚሰጡህ ያለመመቸት ስሜት ወደ ስሜታዊነትና በዚያም ስሜታዊነት ተነድቶ ውሳኔን ወደመቀያየር ቀጠና የሚያስገባህ ከሆነ የጥሩ ምርጫ ሰው አይደለህም፡፡ ይህ አይነቱ የየእለት ገጠመኝና “እንቅፋት” በተገቢው ሁኔታ ካልተያዘ ለዋና ዋና የሕይወት አቅጣጫዎችህ እንቅፋት የሚሆንን ምላሽ እንድትሰጥ ሊጋብዝህ ይችላል፡፡

አንተ ከተረጋጋህና ከአቅምህ በላይ የሆኑትን ነገሮች ለፈጣሪ መልቀቅ ከተማርክ አንዳንድ እድል እንኳን አመለጠኝ . . . አንዳንድ ሰው እንኳን ከድቶኝ ሄደ . . . አንዳንድ የጀመርኩት ነገር እንኳን አልተሳካ . . . አንዳንድ ፍቅረኛ እንኳን እምቢ ብሎኝ ሄደ . . . የምትልበት ቀን ሊመጣ እንደሚችል ላስታውስህ!

“ምርጫና ውሳኔ” ከተሰኘው የዶ/ር
ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ

በቅንነት ሼር ያድርጉ
Join: @the_motivators
Join: @the_motivators
292 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 21:51:16
ልክ ነህ!

ሁሌም የምትችለውን ሁሉ አድርግ! አሁን የዘራኸውን ነው ነገ የምታጭደው። አሁን ስትለፋ ወይ አላማህን ስታስቀድም እንደ ሞኝ ሊያዩህ ይችላሉ፤ አንተም ለጊዜው የተሸወድክ ይመስልሀል፤ ልክ ነህ አልተሳሳትክም።

ሰዎችን በብልጠት ሳይሆን በልፋትህ ብለጣቸው ምክንያቱም በልፋትህ ከፍ ስትል ብልጡን ሰው ቀጥረህ ታሰራዋለህ።

መልካም አደር ተመኘን!!!

@the_motivators
@the_motivators
207 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ