Get Mystery Box with random crypto!

The Motivator

የቴሌግራም ቻናል አርማ the_motivators — The Motivator T
የቴሌግራም ቻናል አርማ the_motivators — The Motivator
የሰርጥ አድራሻ: @the_motivators
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 498

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-12-29 07:50:15 #የፍርሀት_ሰው_ነህ?

ከሮም ሰዎች ሁሉ እጅግ ጥበበኛ የነበረው ማርከስ ኦውሬሊየስ፤ ሕይወታችን የአስተሳሰባችን ውጤት ነው! ብሎ ነበር። አሜሪካዊው ጥበበኛ ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን ደግሞ፣ “ሰው የሚሆነው ቀኑን ሙሉ የሚያስበው ነው!” ብሏል።

አንድ ሰው በቀን ውስጥ ብዙ ነገሮችን እንደሚያስብ ግልጽ ነው። ከእነዚህ ሁሉ ሀሳቦች ስር ግን አንድ መሰረታዊ ወይም የመጀመሪያ ሀሳብ አለ። ሁሉም ሌሎች አስተሳሰቦች የሚጠፉትም ሆነ ቀለማቸውንና ይዘታቸውን የሚወስዱት ከዚህ መሠረታዊ አስተሳሰብ ውስጥ ነው።

ለምሳሌም አንዳንድ ሰዎች ፍርሃት ዋናውና መሠረታዊው ወይም ተቀዳሚው ሀሳባቸው እንዲሆን ይፈቅዳሉ።

በተለምዶ ፍርሃት የሚጀምረው በአብዛኛው በአእምሮ ውስጥ በሚጸነስ ትንሽ ስጋት ወይንም ጭንቀት ነው። ነገር ግን ለቀናት ያህል ሲደጋገም በንቃተ ህሊና መካከል ጥልቅ የሆነ ሰርጥ እስኪያቋርጥ ድረስ የተለመደ ይሆናል።  ይህ የሆነበት ማንኛውም ሰው ስለ ቤተሰቡ፣ ስለ ንግድ ስራው፣ ስለ ጤንነቱ ወይም ስለ ዓለም የሚያስበው በመሠረታዊውና ተቀዳሚው የፍርሃት ሀሳብ ቀለም የተቀባ እና በጭንቀት እና መተማመን በማጣት የተሞላ ነው።

የፍርሃትን የማያቋርጥ ሀሳብ የቱንም ያህል ቢቃወም ማምለጥ አይችልም። ምክንያቱም እርሱ ቀኑን ሙሉ የሚያስበውን ሰው ነው የሚሆነው፤ እርሱ የፍርሃት ሰው ነው።

ይህንን ሁኔታ ለመቀልበስ ጠንከር ያለና ሌላ ዓይነት መሰረታዊ ሀሳብ ወደ አእምሮው ማስረጽ አለበት። ፍርሃትን በተሳካ ሁኔታ የሚቃወመው ብቸኛው መሰረታዊ አስተሳሰብ እምነት ወይም አዎንታዊ አስተሳሰብ ነው።

ከፍርሃት የሚበረታው እምነት ብቻ ነው።

ለመሆኑ ወዳጄ ምን ያስፈራሀል?

ምንም ይሁን... ፍርሀትህን በእምነት አሸንፍ!

@the_motivators
@the_motivators
54 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 21:16:58 #ከሜሲ_ይህን_ተማር!

ታላቁ አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ በአንድ ወቅት ስለምን ሜሲ በጫወታ ውስጥ ብዙ እንደማይሮጥ ተጠይቆ የመለሰው መልስ ነበር።

ፊት ለፊቱ የተከፈተን አንድ የጫወታ ቪዲዮን እየተመለከተም ፔፔ መናገር ጀመረ -

"አያችሁት በቀስታ እየተራመደ ነው... አይሮጥም በቃ አብዛኛውን ሰዓቱን በመራመድ ያሳልፋል። ከጫወታው ውጪ አይደለም፣ ጨዋታውን በአይኖቹ እየተከታተለ ነው። ቀጣይ ምን እንደሚከሰት ያውቃል። አይኖቹን ከግራ ወደ ቀኝ ከላይ ወደ ታች ያንከራታቸዋል። ጭንቅላቱ መንቀሳቀሱን አላቆመም፣ ከግራ ወደ ቀኝ ይመለከታል።

"እየሮጠ አይደለም። ሆኖም ምን እየተከሰተ እንደሆነ በአስተውሎ ይመለከታል። አራቱ ተከላካዮች ላይ ያለው ድክመት ምን እንደሆነ ያነፈንፋል። ከአምስት ወይም አስር ደቂቃዎች በኋላ፣ ሁሉንም ሁኔታ በአእምሮው መዝግቦ ይጨርሳል። ምን ማድረግ እንዳለበት፣ ወዴት መሄድ እንዳለበት በአእምሮው ሰርቶ ጨርሷል። ልክ በጫካ ውስጥ እንዳለ ሁሉ እንዴት ማምለጥ እንዳለበት ያስባል። በዚህ ጋር ብሮጥ ይህ ይሆናል የሚለውን ቀድሞ አውቋልና በቀላሉ ማጥቃት ይችላል። ማንምም አይዘውም።"

#ከሜሲ_ምን_ትማራለህ?- አንተም በህይወትህ ውስጥ ያሉትን ችግሮች በአስተውሎት ተመልከት፤ ችግሩና ክፍተቱ ምን ጋ እንደሆነ አነፍንፍ፤ ሁሉንም ክፍተት በደንብ ቃኝ፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብህና ወዴት መሄድ እንዳለብህ በአእምሮህ ሰርተህ ጨርስ፡፡ ቀጣዩ ታሪክ ነው- ተግባራዊ በማድረግ ማጥቃት ብቻ ነው!

@the_motivators
@the_motivators
79 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 22:49:06 የታማኝነት ጥግ Chuken hachiko ታማኙ ሀቺኮ

ዘመኑ እ.ኤ.አ በ1924 ዝናባማ አመሻሽ ነበር አንድ በቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ በAgricultural ዲፓርትመንት ዘርፍ የሚያስተምሩ ፕሮፌሰር ሂዳስባሮ ኡዩኖ ከሚያስተምሩበት University ወደ ቤታቸው እየሄዱ ሳለ መንገድ ላይ በድንገት አንዲት ቲንሼ ውሻ ሳያስቡት ይረግጣሉ ጎንበስ ብለው ሲያዩም በጣም ውሻው ትንሽዬ ከመሆኑም በላይ በዝናብ በጣም እየተንቀጠቀጠ ስለነበረ ለውሻው አዝነውለት ወደቤታቸው ወስደው ለማሳደግ ያስባሉ..

ነገርግን ሲያሳድጉት የነበረው ውሻ በቅርብ ሞቶ ስለነበር ሌላ ውሻ ላለማሳደግ ከባለቤታቸው ጋር ተነጋግረው ነበር እና ፕሮፌሰሩ ጨነቃቸው ነገር ግን ትንሹን ቡቺ ጥለውት ለመሄድ አልቻሉም በድብቅ ለማሳደግ ወስነው ወስደውት ያሳድጉት ጀመር ከጊዜ በኀላ ግን ባለቤታቸው ውሻ እንደሚያሳድጉ ደረሱበት ነገር ግን መከልከል ስላልቻሉ ከፕሮፌሰሩ ጋር በመስማማት አንድ ላይ ማሳደግ ይጀምራሉ ስሙንም ሀቺኮ አሉት ሀቺኮ ማለት በጃፓንኛ Mr eight ማለት ሲሆን ይህንንም ያሉበት ምክንያት ከዛ በፊት 7 ውሾች አሳድገው ስለነበር ሀቺኮ ለቤቱ ስምንተኛ ስለነበር ነው ፡፡

ትንሹ ቡቺም እየተላመደ ሲመጣ ጠዋት ጠዋት ፕሮፌሰሩ ከቤታቸው ወተው ወደ ስራቸው ሲሄዱ ተከትለው ተሳፍረው እስከሚሄዱበት ባቡር ጣቢያ ድረስ ይሸኛቸዋል፡

ፕሮፌሰሩ ከስራ የሚመለስበትንም ሰአት ጠብቆም ባቡር ጣቢያው ድረስ በመሄድም ይቀበላቸውና አብረው ወደ ቤት ይመለሳሉ
እንዲ እንዲ እያለ ቀናት ተቆጠሩ አንድ ቀን ግን ፕሮፌሰሩ በሚያስተምሩበት University ክፍል ውስጥ በድንገተኛ ህመም ይወድቁና ወዲያው ይሞታሉ ....

ነገር ግን ይህንን ሀሉ ጉድ ያላወቀው ሀቺኮ ሁሌ ፕሮፌሰሩ ከስራ በሚመለሱበት ሰአት ባቡር ጣቢያው ድረስ በመሄድ መጠበቁን ተያያዘው ምስኪኑ ሀቺኮ የሚወደው አሳዲጊው ሞቶ መቀበሩን ማን በምን ቋንቋ ያስረዳው !!.....

ሁሌ በሰአቱ ባቡር ጣቢያው በመሄድ ይጠብቃል በዚ መሀል የፕሮፌሰሩ ቤተሰቦች ወደሌላ ከተማ ሲዘዋወሩ ይዘውት ሊሄዱ ቢሞክሩ ውሻው ግን ከዛ ንቅንቅ አልል አለ

ሰአታት ቀናትን ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን ወራት ደሞ አመታትን እየተካ ታማኙ ሀቺኮ አሳዳጊው ፕሮፌሰሩ ይመጣል ብሎ 9 አመታትን ሙሉ በባቡር ጣቢያው ሲጠብቀው ኖረ ......
በመጨረሻም በ12 አመቱ እ.ኤ.አ 1935 እዛው ባቡር ጣቢያው ሞተ ......

አንድ የፕሮፌሰሩ ተማሪ የነበረ ስለውሻው ታሪክ ያውቅ ነበርና ሀቺኮ ከሞተ በኀላ ስለ ሀቺኮና ስለውሾች ታማኝነት በሚል በጋዜጣ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ የሀቺኮ ዝና በመላው ጃፓን ብሎም በአለም ናኘ ፡፡ የጃፓን ንጉሳዊ አገዛዝም በወቅቱ ለውሻው እውቅና በመስጠት በባቡር ጣቢያው ሀውልት በማሰራት ጭምር ሁሉም ጃፓናዊያን ከውሻው ታማኝነትን እንዲማሩ በሚል ታሪኩን የበለጠ ለጃፓናዊያን አስተምረዋል ፡፡
Chekun hachiko ታማኙ ሀቺኮ
ውሻ

@the_motivators
@the_motivators
17 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 22:48:29
18 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 08:10:03 #ፈጣሪ_በችግር_እየቀጣህ_ነው?

ሕይወትህን የሚያስተጓጉል ነገር ሲገጥምህ (በሽታ፣ ጉዳት፣ እጦት፣ ኪሳራ ወ.ዘ.ተ ያሉ ነገሮች ሲያጋጥምህ) ይህ መጨረሻዬ ወይም መጀመሪያዬ ነው የሚል አስተሳሰብ የመያዝ ዝንባሌ አለህ?

የሆነ ሰው ከተጋፈጠህ ያ ሰው እየሰደበህ፣ እያሰለጠነህ ወይስ ሊጨነቅልህ እየሞከረ እንደሆነ ነው የምታስበው?

ችግር ማለት ፈጣሪ እየቀጣህ ወይስ እየፈተነህ ማለት ነው ለአንተ? ወይስ ይህ ችግር እስከናካቴው ችግር ሳይሆን እድል ሊሆን ይችላል ብለህ ታስባለህ?

ለሕይወት ፈተናዎቻችን የሰጠናቸውን ትርጉሞች ስንቀይር ሕይወት የፈለገችውን መሆን ለመቻል ያላት እድል ወሰን የለውም፡፡ የትርጓሜ ለውጥ ማድረግ እና የትኩረት አቅጣጫን መቀየር ማለት፣ ቃል በቃል በሰከንዶች ውስጥ ስነ ሕይወታዊ ውህዳችንን እና የኑሯችንን ሂደት መቀየር ማለት ነው፡፡

ስለዚህ በጥልቀት ተንፍስና አስታውስ፤ ትርጉም ከስሜት እኩል ነው፤ እንዲሁም ስሜት ከኃይል አቻ ነው፡፡ በብልሃት ምረጥ፡፡ ፈተናዎችህን ዳግም ማስተካከልን ተማር፡፡

በእያንዳንዱ ክስተት ውስጥ አዎንታዊና አበረታች ትርጉሞች ፈልግ፤ እናም ከፊትህ ያለው ምርጡና የተሻለው መንገድ ሁልጊዜም ለመጓዝ የአንተ ነው፡፡  በርታ ተጓዝ!

#የስኬት_አቡጊዳ መጽሐፍ

@the_motivators
@the_motivators
61 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 22:20:17 #ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን እየበረረ የነበረው ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል በዚህ ሰዓት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ከመጸዳጃ ቤቱ ይወጣል። ሁሉም ሰው አንተ የማትረባ ጨርሰኸን ነበር እኮ ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን የለም።
     መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል? ይለዋል  ሰውዬውም አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። አጋጣሚ ነው ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው ይለዋል።
     ብዙ ጊዜ ሰዋች እንደዚ ያስባሉ የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል።
  ዋና ነገሬ ያለው እግዚአብሔር ጋር ነው በማለት በእረፍት እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን

@the_motivators
@the_motivators
74 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 22:49:00 አውቶብሱ
•••••••••••
በተሳፋሪዎች የተሞላዉ አዉቶብስ ጉዞ ላይ ነዉ ወዲያዉ የአካባቢዉ የአየር ሁኔታ ተቀያየረና አስፈሪ የነጎድጓድ ድምፅ የመብረቅ ብልጭታ መታየት ጀመረ፡፡

ተሳፋሪዎቹ አዉቶብሱ ከአሁን አሁን በመብረቅ ተመታ እያሉ መጨነቅ
ጀመሩ መብረቁ ግን መኪናዉን እያለፈ ይወድቅ ነበር፡፡
እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ ሁለት ሶስቴ እንደቀጠለ ሾፌሩ አዉቶብሱን ከአንድ ዛፍ ሃምሳ ጫማ ርቀት ሲቀረዉ አቆመና ተሳፋሪወቹን
"ከእናንተ መሃል ዛሬ መሞቱ ግዴታ የሆነ ሰዉ አለ ከአሁን በኋላ አብሮን ከተጓዘ በእሱ ምክንያት ሌሎቻችንም አብረን ልንጠፋ እንችላለን።

ስለዚህ ሁላችሁም በየተራ እየወጣችሁ ያንን ዛፍ እየነካችሁ እንድትመለሱ እፈልጋለሁ መሞት ያለበት ሰዉ ካለም ዛፉን የነካ ጊዜ በመብረቅ ይመታል ሌሎቻችን ግን እንተርፍለን ማለት ነዉ!!" አለ
ሁሉም የመጀመሪያዉን ተሳፋሪ ሄዶ ዛፍን እንዲነካ መጎትጎት ጀመሩ እሱም እየጨነቀዉና በፍርሃት ተዉጦ ሄዶ ዛፍን ነክቶ በሰላም ተመለሰ ምንም ሳይሆን በመመለሱም ልቡ በደስታ ጮቤ ረገጠች፡፡

መጨረሻ ላይ የነበረዉ ተሣፋሪ ተራ እንደደረሰ ሁሉም በበደለኛ(ሟቹ እሱ እንደሆነ በማሠብ) አይኑን እያዩት እንዲሄድ ገፋፉት እሱም በመሞት ፍራቻ ተዉጦ ከአዉቶብሱ ወረደ።

ከዛፉ ደርሶ እንደነካዉም ሃይለኛ ድምፅ ተሠማ አስፈሪ የመብረቅ
ብልጭታም ታየ....መብረቁ
.
.
.
.
ግን የመታዉ አዉቶብሱን ነው። ውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችም ሞቱ፡፡ እነዚያ ቀደም ብሎ አዉቶብሱን ያለፉት አደጋዎች ሁሉ ያለፉትም በመጨረሻዉ ተሣፋሪ ምክንያት ነበር፡፡

አንዳንዴ የስኬቶቻችን ሁሉ አድራጊ ፈጣሪዎች ራሳችን ብቻ እንደሆንን
እናስብና ሽልማቱን ለራሣችን ብቻ እንሰጣለን ለዚያ ያበቁን ብዙ
ባለዉለታወቻችንን ዘንግተን እኮ ነዉ፡፡
ሰው በራሱ ሙሉ አይደለም ክፍተቱን የሚያይ ጎደሎዉን የሚሞላ ሰዉ አንድን ቅርፅ ይዞ ከአጠገቡ ይኖራል፡፡

ምን አልባትም አሁን እኛ ከብዙ ችግሮችና ውጣውረዶች ለመጠበቃችን ምክንያት የሆኑን ብዙ ሰወች በዙሪያወቻችን አሉ።
ወላጆች
አሳዳጊዎች
እህት ወንድሞች..ዘመዶች...ጓደኞች!!

#ሼርርርር

@the_motivators
@the_motivators
139 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 21:55:17 አዎ! ዛሬ ቁጭ ብለህ በፌስቡክ ላይ ፃፍ፣ #ተሳደብ፣ #ቀስቅስ፣ ሰዎችን #አጋጭ፣ በሆነው ባልሆነው፤ በረባው ባልረባው #ተባላ ... ነገ ሀገር ሲተራመስ -- ኔትዎርኩ ሲዘጋ፤ መብራቱ ሲጠፋ፤ ውሀው ሲቋረጥ፤ #የምትበላው_ስታጣ፤ ገንዘብ በኪስህ ሞልቶ ለሻይ እንኳን ከቤትህ ለመውጣት #ሲያቅትህ የት እንደምትገባ ግራ ይገባሀል። ዛሬ ያቀለልካት ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም። #ዛሬማ_ሰላም_ነው ፎክር እንጂ... የቤትህ አናት ላይ ሲተኮስ፤ የቦንብ ናዳው ሲውርድ፤ ሰው ወጥቶ ሲቀር ስትሰማ፤ #ህፃናት_ሲረግፉ ስታይ፤ ህዝብ #እየተሰደደ የበረሀ ሲሳይ ሲሆን፥ ባህር ውስጥ ሰጥሞ ሲቀር ስታይ... የዛሬዋን ቀን #ትረግማታለህ ። ምነው ጌታ ባልፈጠርከኝ ትላለህ። ብቻህን ያለወንድም፤ ያለእናት አባት፤ ያለዘመድ ስትቀር መፈጠርህን ትጠላለህ። ዛሬ ያቀለልካትን ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም። #ዛሬማ ሰላም ነው ፎ ክ ር... አ ቅ ራ ራ... ህዝብ ቀስቅስ... ተነሳ በለው፣ ግደለው_በል! የለኮስከው እሳት አመድ ሲያደርግህ የሰላምን ዋጋ ያን ጊዜ ትረዳዋለህ...!
.............................................................
#ሀገራችንን_ሰላም_ያርግልን ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር ! Share
@the_motivators
@the_motivators
30 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:47:19 #የምትሰሙትን_ሰው_ለይታችሁ_እወቁ!

አጭርና ግልጽ ምክር፡- ውጤቱን አብሯች በማይሸከም ሰው ወሬ፣ ግፊትና አጉል ምክር ምክንያት አንድን ውሳኔ አትወስኑ፡፡

ከፋም ለማም፣ ሞላም ጎደለም፣ ተሳካም አልተሳካም ውጤቱን እናንተው የምትሸከሙትን የግል ውሳኔያችሁን መወሰን ያለባችሁ እናንተው ናችሁ፡፡

በተለይም የሕይወታችሁን አቅጣጫ እስከወዲያኛው የሚለውጥን ምርጫና ውሳኔ ስታደርጉ የማን ሃሳብና ምክር በሕይወታችሁ ስፍራ ሊያገኝ እንደሚገባው በሚገባ ለይታችሁ እወቁ፡፡ ምንም እንኳን ግራ በገባችሁ ጉዳይ ላይ መካሪ የመፈለጋችሁ ሁኔታ ትክክለኛ ሂደት ቢሆንም፣ ለምን አይነት ሰው ወሬና ግፊት ምላሽ ልትሰጡ እንደሚገባችሁ ግን ራሳችሁ ካላወቃችሁበት በኋላ የምትጸጸቱበትን አቅጣጫ ከመከተል አታመልጡም፡፡

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

*
ቤተሰብ ይሁኑ

@the_motivators
@the_motivators
45 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 00:46:03 ........Continued

4 If your eyes see the front, your heart thinks about the back. Don't forget yesterday so you can reach tomorrow. Don't forget where you came from so you don't lose where you're going.

To be continued............
#like
#share
#comment

@the_motivators
40 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 21:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ