Get Mystery Box with random crypto!

#ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን እየበረረ የነበረው ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት | The Motivator

#ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን እየበረረ የነበረው ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል በዚህ ሰዓት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ከመጸዳጃ ቤቱ ይወጣል። ሁሉም ሰው አንተ የማትረባ ጨርሰኸን ነበር እኮ ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን የለም።
     መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል? ይለዋል  ሰውዬውም አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። አጋጣሚ ነው ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው ይለዋል።
     ብዙ ጊዜ ሰዋች እንደዚ ያስባሉ የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል።
  ዋና ነገሬ ያለው እግዚአብሔር ጋር ነው በማለት በእረፍት እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን

@the_motivators
@the_motivators