Get Mystery Box with random crypto!

አውቶብሱ ••••••••••• በተሳፋሪዎች የተሞላዉ አዉቶብስ ጉዞ ላይ ነዉ ወዲያዉ | The Motivator

አውቶብሱ
•••••••••••
በተሳፋሪዎች የተሞላዉ አዉቶብስ ጉዞ ላይ ነዉ ወዲያዉ የአካባቢዉ የአየር ሁኔታ ተቀያየረና አስፈሪ የነጎድጓድ ድምፅ የመብረቅ ብልጭታ መታየት ጀመረ፡፡

ተሳፋሪዎቹ አዉቶብሱ ከአሁን አሁን በመብረቅ ተመታ እያሉ መጨነቅ
ጀመሩ መብረቁ ግን መኪናዉን እያለፈ ይወድቅ ነበር፡፡
እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ ሁለት ሶስቴ እንደቀጠለ ሾፌሩ አዉቶብሱን ከአንድ ዛፍ ሃምሳ ጫማ ርቀት ሲቀረዉ አቆመና ተሳፋሪወቹን
"ከእናንተ መሃል ዛሬ መሞቱ ግዴታ የሆነ ሰዉ አለ ከአሁን በኋላ አብሮን ከተጓዘ በእሱ ምክንያት ሌሎቻችንም አብረን ልንጠፋ እንችላለን።

ስለዚህ ሁላችሁም በየተራ እየወጣችሁ ያንን ዛፍ እየነካችሁ እንድትመለሱ እፈልጋለሁ መሞት ያለበት ሰዉ ካለም ዛፉን የነካ ጊዜ በመብረቅ ይመታል ሌሎቻችን ግን እንተርፍለን ማለት ነዉ!!" አለ
ሁሉም የመጀመሪያዉን ተሳፋሪ ሄዶ ዛፍን እንዲነካ መጎትጎት ጀመሩ እሱም እየጨነቀዉና በፍርሃት ተዉጦ ሄዶ ዛፍን ነክቶ በሰላም ተመለሰ ምንም ሳይሆን በመመለሱም ልቡ በደስታ ጮቤ ረገጠች፡፡

መጨረሻ ላይ የነበረዉ ተሣፋሪ ተራ እንደደረሰ ሁሉም በበደለኛ(ሟቹ እሱ እንደሆነ በማሠብ) አይኑን እያዩት እንዲሄድ ገፋፉት እሱም በመሞት ፍራቻ ተዉጦ ከአዉቶብሱ ወረደ።

ከዛፉ ደርሶ እንደነካዉም ሃይለኛ ድምፅ ተሠማ አስፈሪ የመብረቅ
ብልጭታም ታየ....መብረቁ
.
.
.
.
ግን የመታዉ አዉቶብሱን ነው። ውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችም ሞቱ፡፡ እነዚያ ቀደም ብሎ አዉቶብሱን ያለፉት አደጋዎች ሁሉ ያለፉትም በመጨረሻዉ ተሣፋሪ ምክንያት ነበር፡፡

አንዳንዴ የስኬቶቻችን ሁሉ አድራጊ ፈጣሪዎች ራሳችን ብቻ እንደሆንን
እናስብና ሽልማቱን ለራሣችን ብቻ እንሰጣለን ለዚያ ያበቁን ብዙ
ባለዉለታወቻችንን ዘንግተን እኮ ነዉ፡፡
ሰው በራሱ ሙሉ አይደለም ክፍተቱን የሚያይ ጎደሎዉን የሚሞላ ሰዉ አንድን ቅርፅ ይዞ ከአጠገቡ ይኖራል፡፡

ምን አልባትም አሁን እኛ ከብዙ ችግሮችና ውጣውረዶች ለመጠበቃችን ምክንያት የሆኑን ብዙ ሰወች በዙሪያወቻችን አሉ።
ወላጆች
አሳዳጊዎች
እህት ወንድሞች..ዘመዶች...ጓደኞች!!

#ሼርርርር

@the_motivators
@the_motivators