Get Mystery Box with random crypto!

አዎ! ዛሬ ቁጭ ብለህ በፌስቡክ ላይ ፃፍ፣ #ተሳደብ፣ #ቀስቅስ፣ ሰዎችን #አጋጭ፣ በሆነው ባልሆነው | The Motivator

አዎ! ዛሬ ቁጭ ብለህ በፌስቡክ ላይ ፃፍ፣ #ተሳደብ፣ #ቀስቅስ፣ ሰዎችን #አጋጭ፣ በሆነው ባልሆነው፤ በረባው ባልረባው #ተባላ ... ነገ ሀገር ሲተራመስ -- ኔትዎርኩ ሲዘጋ፤ መብራቱ ሲጠፋ፤ ውሀው ሲቋረጥ፤ #የምትበላው_ስታጣ፤ ገንዘብ በኪስህ ሞልቶ ለሻይ እንኳን ከቤትህ ለመውጣት #ሲያቅትህ የት እንደምትገባ ግራ ይገባሀል። ዛሬ ያቀለልካት ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም። #ዛሬማ_ሰላም_ነው ፎክር እንጂ... የቤትህ አናት ላይ ሲተኮስ፤ የቦንብ ናዳው ሲውርድ፤ ሰው ወጥቶ ሲቀር ስትሰማ፤ #ህፃናት_ሲረግፉ ስታይ፤ ህዝብ #እየተሰደደ የበረሀ ሲሳይ ሲሆን፥ ባህር ውስጥ ሰጥሞ ሲቀር ስታይ... የዛሬዋን ቀን #ትረግማታለህ ። ምነው ጌታ ባልፈጠርከኝ ትላለህ። ብቻህን ያለወንድም፤ ያለእናት አባት፤ ያለዘመድ ስትቀር መፈጠርህን ትጠላለህ። ዛሬ ያቀለልካትን ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም። #ዛሬማ ሰላም ነው ፎ ክ ር... አ ቅ ራ ራ... ህዝብ ቀስቅስ... ተነሳ በለው፣ ግደለው_በል! የለኮስከው እሳት አመድ ሲያደርግህ የሰላምን ዋጋ ያን ጊዜ ትረዳዋለህ...!
.............................................................
#ሀገራችንን_ሰላም_ያርግልን ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር ! Share
@the_motivators
@the_motivators