Get Mystery Box with random crypto!

The Motivator

የቴሌግራም ቻናል አርማ the_motivators — The Motivator T
የቴሌግራም ቻናል አርማ the_motivators — The Motivator
የሰርጥ አድራሻ: @the_motivators
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 498

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-19 20:05:25 #ሕይወት_ምንድን_ነው ?
ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:
1. ሆስፒታል
2. እስር ቤት
3. መቃበር
#በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ።
:
#በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ።
:
#በመቃብር ውስጥ ሕይወት ምንም ዋጋ እንደሌለው ትገነዘባለህ።
:
የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው። ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ ሁን። ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን!
መልካም ቀን

@the_motivators
@the_motivators
32 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 13:29:43
የሚበላ ስላለን ሳይሆን በልተው የማያድሩት መሀል ስላልሆንን እናመስግን የምንተኛበት ስላለን ሳይሆን የመተኛትን ጠአም የማያውቁት መሀል ስላልሆንን እናመስግን የሞቀ ቤት ስላለን ሳይሆን ቤተሰብ ከሌላቸው መሀል ስላልሆንን እናመስግን የምንለብሰው ስላለን ሳይሆን ከብርድም ከምንም የማያስጥል ልብስ ከሚለብሱት መሀል ስላልሆንን እናመስግን ያኔ ስሜታቸው ህመማቸው ሁሉ ይገባናል እኔም አንተም አንቺም ነገ የዚህ እጣ ሊደርሰን ይችላል እመኑኝ ትላንት ልብስ የሰጣችሁት አይረሳችሁም ልብስ አጥታችሁ ቢያይ ይሰጣችሁዋል ተርቦ ያበላችሁት ተርባችሁ ቢያይ ያበላችሁዋል መልካምን ከሰፈርን መልካም ይሰፈርልናል



ለደሀ ቸርነትን ያረገ ለፈጣሪው ያበድራል በጎነቱም መልሶ ይከፍለዋል

@the_motivators
@the_motivators
47 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 20:30:00
ዶፍ ሲዎርድብን ሲከርም መከራ ሲቀራመተን
ዘመም አልን እንጂጊዜ እስኪያልፍ
ከመቅደም መች ተለይተን
ጎጇችን ጣራዋ ቢያፈስ ፊቱን ቢነሳን ዘመን
ሐበሻ ድብቅ ሃይል አለን በፍጥረት የማይተመን
( ወደፊት)
ተናነቀኝ እንባ
እንኳን ደስ አለንንንንንንንን!!!
ኢትዮጵያዊያን

@the_motivators
@the_motivators
32 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 18:37:30
36 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 18:32:52
እንኳን ደስ አለን

ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቀ ለሀገራችን ሁለተኛውን እና ሞስነት ገርመው ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አስገኝተዋል
እናመሰግናችኋለንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንን

@the_motivators
@the_motivators
37 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 23:49:13 ኢትዮጵያ ጦቢያዬ..ዳግም ዮጵ ስትለብስ እለተሰንበት በዕለተ ሰንበት ዋዜማ በዓለም አደባባይ ስትነግስ..አረንጓዴ ፣ቢጫ ቀይ ቀለማት ከሰማይ ላይ በተላከ ታላቅ ብዕር ሁሌም እንዲፃፍ ትዕዛዝ የተሰጠ ይመስል..ምንግዜም በሙሉ ልብ እሷን ይዘው እሷን ወክለው ሲቀርቡ በዓለም መድረክ ላይ ከፍ ብሎ ስሟ ይፃፋል ይውለበለባልም!!! መተባበር አንደንት የታየበት ታላቅ ፍልሚያ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቋል!! አንድነት የማይቻለውን ያደርጋል!!..ድህነት እጅጉን በሚደቁሳት ሀገሬ አንድነት ላጠችው ታላቂቷ ሀገሬ ወርቅን ለማግኘት በሚደረገው ጥረት በተደረገው አልሸነፍ ባይነት በልጆቿ ጥረት፣መተባበር አንድነት ወርቁን አግኝታለች!!

#አንድነትን ይስጠን!!

"የመጪው ዘመን ፊት ናት መሪ ዛሬ ዓለም ቢላት ኋላ ቀሪ.."

እንኳን ደስ አለን በድጋሚ


ዮጵ ማለት "ቢጫ ወርቅ"ወይም"እንቁ"ማለት ነው

@the_motivators
@the_motivators
44 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 22:56:54
ለተሰንበት ግደይ ወርቅ !!!

በሴቶች 10 ሺ ሜትር ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

እንኳን ደስ አለንንንንንንንን !!

@the_motivators
47 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 14:24:21 "​​አላማህን ለማሳካት ያለህን አቅም ሁሉ ተጠቀም!"

አባትና ልጅ በጫካ ውስጥ በመጓዝ ላይ ሳሉ ልጁ አባቱን ጥያቄ ይጠይቀዋል። "አባቴ ይህን ዛፍ ብገፋው ቅርንጫፎቹን ማነቃነቅ አልችልም?" አለው። እንዴታ! ሙሉ አቅምህን ተጠቅመህ ከሞከርክ የማትችለው ነገር የለም።

ሲል መለሰለት። ልጁም ሙከራውን ጀመረ። ይሁንና ግን ዛፉ ትልቅ በመሆኑ ቅርንጫፎቹን ሊወዘውዝ አልቻለም።
"አባቴ ተሳስተሀል። እኔ ይህን ማድረግ አልችልም" አለው።

"እንደገና ሞክር!" አለው አባቱ።
ልጁ የቻለውን ያህል ዛፉን ቢገፋም ቅርንጫፎቹ አልነቃነቅ አሉ። ብዙ ሞከረ ግን አልሆነም። "አባቴ አልችልም!" አለው ተስፋ በመቁረጥ።

አባቱም "ልጄ አቅምህን በሙሉ ተጠቀምና ሞክር ነበር ያልኩህ ግን አላደረከውም" ሲል መለሰለት።
"ከዚህ በላይ?" ልጁ ግራ ተጋባ።
"አዎ! እኔን መች ለእርዳታ ጠየከኝ?" ሲል ልጁ ያልጠበቀውን ምላሽ መለሰለት።

በዙሪያችን ያሉትን አማራጮች፣ እድሎች፣ ድጋፎች፣ ተስፋዎች፣ ብርታቶች...

ሳንጠቀም አንድ ነገር "አልተሳካልኝም!" ብለን ተስፋ መቁረጥ አይገባንም። ማንም በራሱ ሙሉ አይደለም።

ድጋፍ ይፈልጋል፣ እርዳታ ይፈልጋል። በሌላው ተስፋ አለመቁረጥ ውስጥ፣ በሌላው ብርታት ውስጥ፣ በሌላው መጽናናት ውስጥ ሀይላችንን ልናገኘው እንችላለን።

.......እርዳታ የጠየቅናቸው ሰዎች ባይተባበሩን የተሳሳተ ሰው መጠየቃችንን እንጂ፣ ወይም አጠያየቃችንን መለወጥ እንዳለብን እንጂ፣ ወይም በሌላ ጊዜ መጠየቅ እንዳለብን እንጂ እርዳታ መጠየቃችን ነውር ነው ማለት አይደለም።

በዙሪያችን ያለውን እድል ሁሉ አሟጠን መጠቀም ለህልማችን መሳካት መሰረት ነው።

@the_motivators
@the_motivators
8 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 13:53:41 ሸክም የመውደድ አባዜ
----------------------------

ይህቺ ግኝት እኮ እንደነገሩ የምትወሳ ናት፤ እኛም እንደነገሩ አንብበን በልቦናችን እንያዛት እስኪ።

* በግማሽ መጠን ውሃ የያዘን ብርጭቆ ለአንድ ደቂቃ በመዳፍህ ይዘህ ብትቆም ምንም ችግር የለውም፡፡

* ለአንድ ሰዓት ያህል ይዘኸው ብትቆይ ግን ክንድህ ይዝላል፡፡

* ሙሉ ቀን ተሸክመኸው ብትውል ደግሞ እጅህ ደንዝዞ መስራት ያቆመ ያህል ይሰማሃል፡፡

* ልብ በል ውሃ የያዘው ብርጭቆ ክብደቱ ያው ነው፡፡ ለብዙ ጊዜ በያዝከው ቁጥር ግን እየከበደህና እየደከመህ የምትመጣው አንተው ነህ፡፡

ወዳጄ
ነገር አትያዝ፤ ኩርፊያ አታክርም፤ ድብርትና ጭንቀትም እንዲህ ናቸው። ሙጭጭ ስትልባቸው ተራራ ታሳክላቸዋለህ፡፡


@the_motivators
@the_motivators
36 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 13:51:01 የማያልፉ የመሰሉ ጨለማዎች አልፈዋል አልችለውም ያልከው ሁሉ ተችሏል ጉዳትህ ያራቃቸው የሌለህን ምክኒያት አርገው የራቁህ በሙሉ እንኳን ራቁህ አስተውል ፈጣሪ አንተን ለታላቅ ነገር ሲያጭህ ደጋግሞ በትናንሽ ነገሮች ይፈትንሀል እመነኝ ይሄ ቀን አልፎ ያ ጊዜ እኮ እያልክ የምታወራበት ጊዜ ይመጣል ወንድ ሴት ጤነኛ በሽተኛ ደሀ ሀብታም ኢትዮጵያዊ አልያም ሌላ ዜጋ መሆንን መርጠህ አልወሰድክምና ባልመረጥከው ነገር አትዘን ፈጣሪ የሚያስፈልግህን እንጂ የምትፈልገውን አይሰጥህም ምናልባት በበሽታዎች አልፈህ መሄድህ የሚያስተምርህ ከሰዎች መርጠህ እንድትቀርብ ሊጠቁምህ ይሆናል በቁምህ ሳይረዳህ ለሞትህ ከሬሳ ሳጥን አንስቶ እስከ መስተንግዶ ለሚያዋጣ ህዝብ ለምን ትጨነቃለህ በስተመጨረሻም ከነብስህ ውጪ ማንም ካንተ ጋር አይሆንምና ነብስህን ተንከባከባት!!

@the_motivators
@the_motivators
35 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ