Get Mystery Box with random crypto!

'​​አላማህን ለማሳካት ያለህን አቅም ሁሉ ተጠቀም!' አባትና ልጅ በጫካ ውስጥ በመጓዝ ላይ ሳሉ | The Motivator

"​​አላማህን ለማሳካት ያለህን አቅም ሁሉ ተጠቀም!"

አባትና ልጅ በጫካ ውስጥ በመጓዝ ላይ ሳሉ ልጁ አባቱን ጥያቄ ይጠይቀዋል። "አባቴ ይህን ዛፍ ብገፋው ቅርንጫፎቹን ማነቃነቅ አልችልም?" አለው። እንዴታ! ሙሉ አቅምህን ተጠቅመህ ከሞከርክ የማትችለው ነገር የለም።

ሲል መለሰለት። ልጁም ሙከራውን ጀመረ። ይሁንና ግን ዛፉ ትልቅ በመሆኑ ቅርንጫፎቹን ሊወዘውዝ አልቻለም።
"አባቴ ተሳስተሀል። እኔ ይህን ማድረግ አልችልም" አለው።

"እንደገና ሞክር!" አለው አባቱ።
ልጁ የቻለውን ያህል ዛፉን ቢገፋም ቅርንጫፎቹ አልነቃነቅ አሉ። ብዙ ሞከረ ግን አልሆነም። "አባቴ አልችልም!" አለው ተስፋ በመቁረጥ።

አባቱም "ልጄ አቅምህን በሙሉ ተጠቀምና ሞክር ነበር ያልኩህ ግን አላደረከውም" ሲል መለሰለት።
"ከዚህ በላይ?" ልጁ ግራ ተጋባ።
"አዎ! እኔን መች ለእርዳታ ጠየከኝ?" ሲል ልጁ ያልጠበቀውን ምላሽ መለሰለት።

በዙሪያችን ያሉትን አማራጮች፣ እድሎች፣ ድጋፎች፣ ተስፋዎች፣ ብርታቶች...

ሳንጠቀም አንድ ነገር "አልተሳካልኝም!" ብለን ተስፋ መቁረጥ አይገባንም። ማንም በራሱ ሙሉ አይደለም።

ድጋፍ ይፈልጋል፣ እርዳታ ይፈልጋል። በሌላው ተስፋ አለመቁረጥ ውስጥ፣ በሌላው ብርታት ውስጥ፣ በሌላው መጽናናት ውስጥ ሀይላችንን ልናገኘው እንችላለን።

.......እርዳታ የጠየቅናቸው ሰዎች ባይተባበሩን የተሳሳተ ሰው መጠየቃችንን እንጂ፣ ወይም አጠያየቃችንን መለወጥ እንዳለብን እንጂ፣ ወይም በሌላ ጊዜ መጠየቅ እንዳለብን እንጂ እርዳታ መጠየቃችን ነውር ነው ማለት አይደለም።

በዙሪያችን ያለውን እድል ሁሉ አሟጠን መጠቀም ለህልማችን መሳካት መሰረት ነው።

@the_motivators
@the_motivators