Get Mystery Box with random crypto!

ሸክም የመውደድ አባዜ ---------------------------- ይህቺ ግኝት እኮ እንደነገሩ | The Motivator

ሸክም የመውደድ አባዜ
----------------------------

ይህቺ ግኝት እኮ እንደነገሩ የምትወሳ ናት፤ እኛም እንደነገሩ አንብበን በልቦናችን እንያዛት እስኪ።

* በግማሽ መጠን ውሃ የያዘን ብርጭቆ ለአንድ ደቂቃ በመዳፍህ ይዘህ ብትቆም ምንም ችግር የለውም፡፡

* ለአንድ ሰዓት ያህል ይዘኸው ብትቆይ ግን ክንድህ ይዝላል፡፡

* ሙሉ ቀን ተሸክመኸው ብትውል ደግሞ እጅህ ደንዝዞ መስራት ያቆመ ያህል ይሰማሃል፡፡

* ልብ በል ውሃ የያዘው ብርጭቆ ክብደቱ ያው ነው፡፡ ለብዙ ጊዜ በያዝከው ቁጥር ግን እየከበደህና እየደከመህ የምትመጣው አንተው ነህ፡፡

ወዳጄ
ነገር አትያዝ፤ ኩርፊያ አታክርም፤ ድብርትና ጭንቀትም እንዲህ ናቸው። ሙጭጭ ስትልባቸው ተራራ ታሳክላቸዋለህ፡፡


@the_motivators
@the_motivators