Get Mystery Box with random crypto!

የታማኝነት ጥግ Chuken hachiko ታማኙ ሀቺኮ ዘመኑ እ.ኤ.አ በ1924 ዝናባማ አመሻሽ ነበ | The Motivator

የታማኝነት ጥግ Chuken hachiko ታማኙ ሀቺኮ

ዘመኑ እ.ኤ.አ በ1924 ዝናባማ አመሻሽ ነበር አንድ በቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ በAgricultural ዲፓርትመንት ዘርፍ የሚያስተምሩ ፕሮፌሰር ሂዳስባሮ ኡዩኖ ከሚያስተምሩበት University ወደ ቤታቸው እየሄዱ ሳለ መንገድ ላይ በድንገት አንዲት ቲንሼ ውሻ ሳያስቡት ይረግጣሉ ጎንበስ ብለው ሲያዩም በጣም ውሻው ትንሽዬ ከመሆኑም በላይ በዝናብ በጣም እየተንቀጠቀጠ ስለነበረ ለውሻው አዝነውለት ወደቤታቸው ወስደው ለማሳደግ ያስባሉ..

ነገርግን ሲያሳድጉት የነበረው ውሻ በቅርብ ሞቶ ስለነበር ሌላ ውሻ ላለማሳደግ ከባለቤታቸው ጋር ተነጋግረው ነበር እና ፕሮፌሰሩ ጨነቃቸው ነገር ግን ትንሹን ቡቺ ጥለውት ለመሄድ አልቻሉም በድብቅ ለማሳደግ ወስነው ወስደውት ያሳድጉት ጀመር ከጊዜ በኀላ ግን ባለቤታቸው ውሻ እንደሚያሳድጉ ደረሱበት ነገር ግን መከልከል ስላልቻሉ ከፕሮፌሰሩ ጋር በመስማማት አንድ ላይ ማሳደግ ይጀምራሉ ስሙንም ሀቺኮ አሉት ሀቺኮ ማለት በጃፓንኛ Mr eight ማለት ሲሆን ይህንንም ያሉበት ምክንያት ከዛ በፊት 7 ውሾች አሳድገው ስለነበር ሀቺኮ ለቤቱ ስምንተኛ ስለነበር ነው ፡፡

ትንሹ ቡቺም እየተላመደ ሲመጣ ጠዋት ጠዋት ፕሮፌሰሩ ከቤታቸው ወተው ወደ ስራቸው ሲሄዱ ተከትለው ተሳፍረው እስከሚሄዱበት ባቡር ጣቢያ ድረስ ይሸኛቸዋል፡

ፕሮፌሰሩ ከስራ የሚመለስበትንም ሰአት ጠብቆም ባቡር ጣቢያው ድረስ በመሄድም ይቀበላቸውና አብረው ወደ ቤት ይመለሳሉ
እንዲ እንዲ እያለ ቀናት ተቆጠሩ አንድ ቀን ግን ፕሮፌሰሩ በሚያስተምሩበት University ክፍል ውስጥ በድንገተኛ ህመም ይወድቁና ወዲያው ይሞታሉ ....

ነገር ግን ይህንን ሀሉ ጉድ ያላወቀው ሀቺኮ ሁሌ ፕሮፌሰሩ ከስራ በሚመለሱበት ሰአት ባቡር ጣቢያው ድረስ በመሄድ መጠበቁን ተያያዘው ምስኪኑ ሀቺኮ የሚወደው አሳዲጊው ሞቶ መቀበሩን ማን በምን ቋንቋ ያስረዳው !!.....

ሁሌ በሰአቱ ባቡር ጣቢያው በመሄድ ይጠብቃል በዚ መሀል የፕሮፌሰሩ ቤተሰቦች ወደሌላ ከተማ ሲዘዋወሩ ይዘውት ሊሄዱ ቢሞክሩ ውሻው ግን ከዛ ንቅንቅ አልል አለ

ሰአታት ቀናትን ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን ወራት ደሞ አመታትን እየተካ ታማኙ ሀቺኮ አሳዳጊው ፕሮፌሰሩ ይመጣል ብሎ 9 አመታትን ሙሉ በባቡር ጣቢያው ሲጠብቀው ኖረ ......
በመጨረሻም በ12 አመቱ እ.ኤ.አ 1935 እዛው ባቡር ጣቢያው ሞተ ......

አንድ የፕሮፌሰሩ ተማሪ የነበረ ስለውሻው ታሪክ ያውቅ ነበርና ሀቺኮ ከሞተ በኀላ ስለ ሀቺኮና ስለውሾች ታማኝነት በሚል በጋዜጣ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ የሀቺኮ ዝና በመላው ጃፓን ብሎም በአለም ናኘ ፡፡ የጃፓን ንጉሳዊ አገዛዝም በወቅቱ ለውሻው እውቅና በመስጠት በባቡር ጣቢያው ሀውልት በማሰራት ጭምር ሁሉም ጃፓናዊያን ከውሻው ታማኝነትን እንዲማሩ በሚል ታሪኩን የበለጠ ለጃፓናዊያን አስተምረዋል ፡፡
Chekun hachiko ታማኙ ሀቺኮ
ውሻ

@the_motivators
@the_motivators