Get Mystery Box with random crypto!

#ምክንያት_አትጠይቂኝ እሷ፡- ለምን ወደድከኝ? ለምን አፈቀርከኝ? እሱ፡- ምክንያቱን መናገር አ | The Motivator

#ምክንያት_አትጠይቂኝ

እሷ፡- ለምን ወደድከኝ? ለምን አፈቀርከኝ?
እሱ፡- ምክንያቱን መናገር አልችልም፤ ነገር ግን የእውነት
እወድሻለው፡፡
እሷ;- ምክንያትህን እንኳን መናገር ሳትችል እንዴት
እወድሻለው፤ አፈቅርሻለው
ለማለት ቻልክ?
እሱ፡- እውነት ለምን እንደወደድኩሽ አላቅም ግን
እንደምወድሽና እንደማፈቅርሽ
ማረጋገጥ እችላለው፡፡
እሷ:- ማረጋገጥ? አይሆንም፤ ለምን እንዳፈቀርከኝ
ምክንያቱን ነው የምፈልገው፡፡
የጓደኛዬ ፍቅረኛ ለምን እንዳፈቀራት ነግሯታል፤ አንተ ግን
ምክንያትህን
አታቀውም፡፡
እሱ፡- እሺ እሺ በቃ እነግርሻለው፡፡ ምክንያቱም ቆንጆ
በመሆንሽ፤ ለጆሮ
በሚለሰልሰው ድምፅሽ፤ እና ስለምትንከባከቢኝ፤ መልካም
አሳቢ ስለሆንሽ፤
በሚያምረው ፈገግታሽ፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴሽ
ምክንያት አፈቅርሻለው፡፡
ልጅቷ በልጁ ምላሽ በጣም ረካች፤ እጅግም ደስ አላት፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ከቀናቶች በኃላ ልጅቷ አደጋ ደርሶባት
# ኮማ ውስጥ ገባች፡፡
መንቀሳቀስ አትችል፤ ማውራት አትችል፤ መሳቅ አትችል፤
ዝም ብቻ፡፡
ልጁ ደብዳቤ ፅፎ እያለቀሰ ከጎኗ አስቀምጦሏት ወጣ፡፡
ደብዳቤውም እንደዚህ
ይላል፡፡
"የኔ ውድ በሚለሰልሰው ድምፅሽ ምክንያት አፍቅሬሻለው፤
አሁን ግን ማውራት
ትችያለሽ? አትችይም፤ ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችልም፡፡
ስለምትንከባከቢኝ እና ስለምታስቢልኝ አፍቅሬሻለው፡፡
አሁን ግን ይህን ማድረግ
አትችይም፤ ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችልም፡፡
በፈገግታሽ ምክንያት አፍቅሬሻለው፤ በእያንዳንዱ
እንቅስቃሴሽ ምክንያት
አፍቅሬሻለው፡፡ አሁን መሳቅ ትችያለሽ? መንቀሳቀስ
ትችያለሽ? አትችይም፡፡
ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችልም፡፡
ፍቅር እውነት ልክ እንዳሁኑ ምክንያት ካስፈለገው ከአሁን
በኃላ አንቺን ላፈቅር
የምችልበት አንድም ምክንያት የለኝም፡፡
ፍቅር ምክንያት ይፈልጋል? አይፈልግም፡፡ ስለዚህ ዛሬም
እንደትናንቱ ካለምንም
ምክንያት አፈቅርሻለው፡፡ ከዘላለሙ ፍቅሬ ጋር ሁሌም
ያንቺ ብቻ ነኝ፡፡" ይላል
ደብዳቤው
መልክሽን አይቶ ያፈቀረሽ መልክሽ የጠፋ እለት የእሱም
ፍቅር አብሮ ይጠፋል፡፡
አንተም እንደዛው ወንድሜ ሀብትህን አይታ ያፈቀረችህ
ካዝናህ ባዶ የሆነ ቀን
የእሷም ልብ ለፍቅር የማይሆን ባዶ ዋሻ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡
ፈጣሪ እውነተኛ ፍቅርን ይስጠን፡፡

@the_motivators
@the_motivators