Get Mystery Box with random crypto!

ደህና አደራችሁ እንስቃለን እንጂ ሁላችንም ድብቅ ህመም አለብን!!! ሌት ተቀን የሚጠዘጥዘን ያለፈ | The Motivator

ደህና አደራችሁ

እንስቃለን እንጂ ሁላችንም ድብቅ ህመም አለብን!!! ሌት ተቀን የሚጠዘጥዘን ያለፈው የህይወት አቦራ በትዝታ እየነፈሰ አይናችንን ዕንባ የሚያስቋጥረው ስንት ነን?
ከሰላምታችን ጀርባ ሰላም ማጣታችን እደተራራ ይገዝፋል የምንወደው ሰው ከምንወደው በላይ ብልጠት አጥቅቶት ያለመታመንን በለስ ጎርሶ የመወደድን ፀጋ እንድናጣው ካለማመን ምድር የተወረወርን ስንት አለን?
የነገ ተስፋችንን የእናታችንን ሳቅ አርገን ግዜ የቀደመን ስንቶች ነን? ስንቶች የወዳጆቻችንን ፎቶ ሰቅለን በቁጭት እያነባን ይሆን? ቤተሰባችን ሲናፍቁን የዕንባ ቧንቦችን ከፍተን ፊታችንን የምናጥብ ስንት አለን? መታመማችን ሳያንስ በህመማችን ለሚጨነቁ የምናዝን ግራ የሚገባን ሞታችንን አቅርበው የምንል ስንቶች ኖረን ይሆን? ሲቃ እየተናነቅን ፈገግ የምንል እሾሁን ጨብጠን የምንስቅ?
ስንቶቻችን ነን?????

መልካም ውሎ!!

@the_motivators
@the_motivators