Get Mystery Box with random crypto!

ምስጋና እና ደስታ! ዕድሜያችን አጭር ናት፤ በዚህ ሰዓት የሚያሳዝኑህን የሚያናድዱህ | The Motivator

ምስጋና እና ደስታ!

ዕድሜያችን አጭር ናት፤ በዚህ ሰዓት የሚያሳዝኑህን የሚያናድዱህን ጉዳዮች ንገረኝ ብልህ ብዙ እንደምትዘረዝር አውቃለው። አስቂኙ ነገር የተሰጠህ ዕድሜ የሚያስደስቱህን ነገሮች እንኳን አጣጥመህ ለመጨረስ አይበቃም!

ታዲያ ለምንድነው ለደስታ እንኳን የማይበቃ ጊዜህን በሀዘንና ጭንቀት የምታጣብበው? "ያንተን ወጣትነት እኮ የጨረጨሰ ንጉስም ይቀናበታል" ይለናል ደራሲ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር። አንዳንድ ነገሮች እንደነበረህ ራሱ የምታውቀው ከእጅህ ሲያመልጥህ ነው፤ ወዳጄ አሁን ላንተ የሚመጥንም ምስጋና እና ደስታ ብቻ ነው!

ደስታ የሞላበት ህይወት ተመኘንላችሁ

@the_motivators
@the_motivators