Get Mystery Box with random crypto!

#ደስ_የሚል_ታሪክ 'መልካምነት መልሶ ይከፍላል' አንድ ወጣት የዩንቨርስቲ ተማሪ ከፕሮፌሰሩ አስተ | The Motivator

#ደስ_የሚል_ታሪክ
"መልካምነት መልሶ ይከፍላል"
አንድ ወጣት የዩንቨርስቲ ተማሪ ከፕሮፌሰሩ አስተማሪው ጋር መናፈሻው ላይ ቁጭ ብለው ያወራሉ ። አስተማሪው ከተማሪዎች ሁሉ ይህን ተማሪ በጣም ስለሚወደው እንደጓደኛው አድርጎ ነው ሚያየው ።
ፊት ለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻን ጽዶችና ሣሮችን የሚያስተካክል ሰራተኛ አለ፣ ተማሪው የጽዳት ሰራተኛውን እያየ ለአስተማሪው “ ቲቸር ዛሬ አንተም እኔ ደብሮናል ለምን ያኛውን ሰውዬ ትንግርት አንሰራውም?ያወለቀውን ጫማ ደበቅ እናርግና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት እንደሚበረግግ እኛም እዛጋ ደበቅ ብለን እንመልከተው” ይለዋል።
አስተማሪውም “ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን ድሀዎችን እያሰቃየን እኛ መደሰት የለብንም። ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን በገንዘባችን የበለጠ ደስታን ማግኘት እንችላለን ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬው ሳያይህ ባውለቀው ጫማዎች ላይ ገንዘብ ከተህበት ና ከዛም ተደብቀን የሚሆነውን እናያለን” አለው። ተማሪውም አስተማሪው እንዳለው ቀስ
ብሎ የሰውዬው ጫማ ላይ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣና ከአስተማሪው ጋር ደበቅ ብለው የሰውዬውን ሁኔታ መከታተል ጀመሩ።
ሰውዬው ጽዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና ጫማውን ለማድረግ ሲታገል ይቆረቁረውና ጎንበስ ብሎ ጫማውን ሲያራግፈው ብሮችን ያገኛል። ሰውዬው ደነገጠ !!
ዙሪያውን ቢያይ ማንም የለም ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራውን ቢመለከት ማንም ሰው የለም ። ሰውየው በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡን ኪሱ ውስጥ ከተተው በኋላ ሁለተኛ እግሩ ጫማውን ሊያደርግ ሲያነሳ በተመሳሳይ ገንዘብ ያገኛል ሰውዬው አላመነም !! በጉልበቱ ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አድርጎ ጮክ ብሎ“ጌታዬ የሚስቴን መታመም አውቀክ ነው አይደል?
ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳት አውቀክ ነው አይደል?
የልጆቼን ዳቦ ማጣታቸውን አይተህ ነው አይደል? ምስጋና ይግባህ ጌታዬ” አለ።ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከት ልቡን ነካው አይኑ እንቧ አቀረረች። አስተማሪውም “ቅድም ካሰብከው ትንግርት ይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንደፈጠረብክ አልጠራጠርም” አለው። ተማሪው እንቧውን እየጠረገ “ፕሮፌሰር እስካሁን ካስተማሩኝ ትምህርት ሁሉ እንደዚህ ያለ ልብ ሚነካ ትምህርት አስተምረውኝ አያውቁም በህይወቴ የማልረሳው ትምህርት ነው ያስተማሩኝ እውነትም ከመውሰድ መስጠት የተሻለ ነው”ብሎ መለሰላቸው።
"ደግ ደጉን እናስብ መልካምነት መልሶ ይከፍለናልና"


@the_motivators
@the_motivators