Get Mystery Box with random crypto!

አስ–ሱናህ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewihd — አስ–ሱናህ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewihd — አስ–ሱናህ
የሰርጥ አድራሻ: @tewihd
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.33K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።
💎እዲሁም የኡለማዎች አጫጭር ፈትዋዎች ይለቀቁበታል إن شاء الله
ስተቴ በቁርአን በሀዲስ ላረመኝ الله ይዘንለት።

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-16 09:16:30 ቀልድ በእስልምና ይፈቀዳል?

ዛሬ ዛሬ ቀልዶች በዝተዋል ሚቀለድበትም ነገር በዝቷል እስኪ እስልምና ስለ ቀልድ ምን ይላል
1) ቀልድ በመሰረቱ ይፈቀዳል።ግን ለራስነቱ ቀልድ ስለሆነ ተብሎ ሚፈለግ ተግባር አደለም ።
- ራስን ነቃ ለማድረግ ፣ ነሻጣ ለማምጣት፣ ሌሎች ሙስሊም ወንድሞቻችንን ለማስደሰት ( ሙስሊም ወንድምን ማስደሰት ኢባዳ ነው) ሸሪያዊ መርሆን ሳይፃረር ሊቀለድ ይችላል።
ነገር ግን አንድ ሰው በቀልድ መታወቅ የለበትም ።ይህ ዳኢ ቀላጅ ነው ተብሎ ሰዎች ዘንድ በሙሉ እስኪታወቅ ድረስ መቀለድ ተገቢ አደለም።ምክንያቱም ይህ እስላማዊ አደብ አደለም ከጨዋ ሰውም ሚጠበቅ አደለም ሰለፎችም እንዲህ አልነበሩም
2)የአላህ መልእክተኛ ከሰሀቦች፣ከቤተሰባቸው እና ከህፃናት ጋር በተለያየ አጋጣሚ እንደቀለዱ ተረጋግጧል።
3)ቀልድ በፍፁም ውሸት ያለበት መሆን የለበትም
የአላህ መልእክተኛ እርሶ ይቀልዳሉ እንዴ ተብለው ሲጠየቁ
: " لا أقول إلا حقا "
እውነት እንጂ አልናገርም ብለዋል
ስለዚህ ለቀልድም ቢሆን መዋሸት አይቻልም
በሌላ ሀዲስ ላይ እንዲህ ብለዋል
‏وقد ورد عنه صلى الله عليه وسلم أنه قال: " ويل للذي يكذب ليضحك الناس ويل له ويل له "
"ወየሁለት ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ የሚዋሽ ወየሁለት ወየሁለት።
4)የክህደት ቃላትን እየተጠቀሙ መቀለድ ከእስልምናም ያስወጣል።
ጌታችን እንዲህ ይላል
قال تعالى {ولئن سألتهم ليقولن إنما كنا نخوض ونلعب ..} الآيات.
"ብትጠይቃቸው እኛማ ስንቀልድ እና ስንጫወት ነበር ይሉሀል።በአላህ በመልእክተኛው እና በአንቀፆቹ ነው ምታላግጡት በላቸው።ምንም ኡዝር አታቅርቡ ከእምነታችሁ በሇላ ክዳችሇል በላቸው።
5) የሙስሊም ወንድሙን ክብር በሚነካ መልኩ መቀለድ፣ወይም በቀልድ አድርጎ የሙስሊም ወንድሙን ቀልብ መስበርም አይፈቀድለትም።
6)በእስልምና ድንጋጌ መቀለድም አይፈቀድም።ለምሳሌ; በሂጃብ፣በፂም ፣በሰላት፣ በሀጅ ፣በፆመ ....በመሳሰሉት
7)በኡለሞች መቀለድም ከባድ ወንጀል ነው
8)እየተሳደቡ ወይም እየተማቱ መቀለድም አይፈቀድም
9)ሰዎች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ እየፈጠሩ ሚደረግም ቀልድ አይፈቀድም።መኪናውን ሰርቆ በማስደንገጥ ሚደረግ ቀልድን ይመስል
10)ሙስሊም ወንድሙ ላይ የጦር መሳሪያ በመደቀን የሚደረግ ቀልድ የተከለከለ በመሆኑ ላይ ሀዲስ መጥቷል
11) የሚፈቀደውን ቀልድም ቢሆን ማብዛት ተገቢ አደለም ። ቀልድ ሲበዛ ቀልብ ያደርቃል

‏قال عمر بن عبد العزيز : " اتقوا المزاح، فإنه حمقة تورث الضغينة "


ቀልድ ልክ እንደ ጨው ነው።መግባት ባለበት ቦታ እና ሰአት ይገባል።ሲበዛ ማጣፈጡን ትቶ ያበላሻል


ጠቃሚ እውቀትን ብቻ ተማሩ

https://telegram.me/tewihd
406 views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 08:14:42 -- كلام يكتب بماء الذهب ويحفظ تحت جفن العين

በወርቅ ብእር የሚፃፍ ንግግር

قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله :(( من لم يقبل الحق أبتلاه الله بقبول الباطل )) مجموع الفتاوى
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሞያህ አላህ ይዘንላቸውና እንድህ ይላሉ:—
((ሀቅን ያልተቀበለ ሰው ባጢልን በመቀበል አላህ ይፈትነዋል))
መጅሙኡል ፈታዋ
------------

ﻗﺎﻝ ﺍﻷﻭﺯﺍﻋﻲ : " ﻋﻠﻴﻚ ﺑﺄﺛﺮ ﻣﻦ ﺳﻠﻒ ﻭﺇﻥ ﺭﻓﻀﻚ ﺍﻟﻨﺎﺱ،ﻭﺇﻳﺎﻙ ﻭﺁﺭﺍﺀَ ﺍﻟﺮﺟﺎﻝ ﻭﺇﻥ ﺯﺧﺮﻓﻮﺍ ﻟﻚ ﺑﺎﻟﻘﻮﻝ" ﺫﻛﺮﻩ ﺍﻟﺬﻫﺒﻲ ﻓﻲﺍﻟﻌﻠﻮ (ﺍﻟﻤﺨﺘﺼﺮ) ﺹ .138
ኢማሙል አውዛኢ አላህ ይዘንላቸው እንድህ አሉ:—
((አደራህን ሰዎች ቢተውህምኳ የቀደምቶችን ጎዳና አጥብቀህ ያዝ, አደራህን ተጠንቀቅ በንግግራቸው ቢያሸበርቁልህና ቢያስውቡልህምኳ የሰዎችን አመለካከት ራቅ))
------------

ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻌﻼﻣﺔ ﺍﺑﻦ ﺍﻟﻮﺯﻳﺮ – ﻭﻟﻮ ﺃﻥّ ﺍﻟﻌﻠﻤﺎﺀ ﺗﺮﻛﻮﺍ ﺍﻟﺬﺏ ﻋﻦﺍﻟﺤﻖ, ﺧﻮﻓﺎً ﻣﻦ ﻛﻼﻡ ﺍﻟﺨﻠﻖ , ﻟﻜﺎﻧﻮﺍ ﻗﺪ ﺃﺿﺎﻋﻮﺍ ﻛﺜﻴﺮﺍً, ﻭﺧﺎﻓﻮﺍ ﺣﻘﻴﺮﺍً.
ﺍﻟﻌﻮﺍﺻﻢ ﻭﺍﻟﻘﻮﺍﺻﻢ (2/223
ታላቁ አሊም ኢብኑ ወዚር እንድህ ይላሉ፡―
((ኡለማኦች ፍጡራንን ፈርተው ከሀቅ ላይ መከላከል ቢተው ኖሮ ብዙዎችን ባባከኑ ነበር ወራዳንም በፈሩ ነበር))
አል አዋሲ ወል ቀዋሲም (2/223)
-------------

قال الإمام الشاطبي رحمه الله :(( وقد زل أقوام بسبب الأعراض عن الدليل والإعتماد على الرجال , فخرجوا بسبب ذلك على جادة الصحابة والتابعين وأتبعوا أهوائهم بغير علم فضلوا عن سواء السبيل )) كتاب الإعتصام
ኢማሙ ሻጢቢ አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ይላሉ: ―
((ብዙ ሰዎች ከደሊል በመሸሻቸውና በመዞራቸው በሰዎችም ላይ በመደገፋቸው ምክናየት ተንሸራተዋል, በዚህም ምክናየት ከሶሀቦችና ከታቢኢዮች ምረኛና ትክክለኛ መስመር ወጡ, ያለ እውቀት ስሜታቸውን ተከተሉ ከትክክለኛውም መንገድ አፈነገጡ ጠመሙ))
አል ኢእቲሷም
------------

قال بلال بن سعد رحمه الله : (( ثلاث لا يقبل معهن عمل , الشرك والكفر والرأي قيل وما الرأي قال : يترك كتاب الله وسنة رسوله ويعمل برأيه )) حلية الأولياء وطبقات الأصفيا
ቢላል ኢብኑ ሰኢድ አላህ ይዘንለት እንድህ ይላሉ: ―
((ሶስት ነገሮች ስራ ከነሱ ጋረ ተቀባይነት የለውም, ሽርክ ኩፍር ረእይ አመለካከት ረእይ ማለት ምን ማለት ነው ተባለ ቁርአንና ሀዲስን ትቶ በራሱ አመለካከት መስራት ነው አለ))
ሂልየቱል አውሊያእ ወጦበቃቱል አስፊያእ
------------

قال الألباني رحمه الله :(( طالب الحق يكفيه دليل , وصاحب الهوى لا يكفيه ألف دليل , الجاهل يعلم , وصاحب الهوى ليس لنا عليه سبيل))
አልባኒ አላህ ይዘንላቸው እንድ ይላሉ: ―
ሀቅን የሚፈልግ አንድ ደሊል ይበቃዋል, የስሜት ሰው ግን ሺ መረጃ አይበቃውም, ጃሂል ያውቃል, ስሜቱን የሚከተል ሰው በሱ ላይ መንገድ የለንም))
------------

قال الإمام ابن القيم رحمه الله تعالى :من عُرض عليه حقٌ فرده فلم يقبله، عُوقب بفساد قلبه وعقله ورأيه مفتاح دار السعادة [١/١٦٠
ኢብኑ ቀይመል ጀውዚ አላህ ይዘንላቸው እንድህ አሉ: ―
((ሀቅ ቀርቦለት ያልተቀበለ, ቀልቡን አቅሉን አመለካከቱን በማበላሸት ይቀጣል))
ሚፍታሁ ዳሪ ሰአዳህ (1/160)
------------

قال الأوزاعي رحمه الله :(( ﺍﺻﺒﺮ ﻧﻔﺴﻚ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﺴﻨﺔ ، ﻭﻗﻒ ﺣﻴﺚ ﻭﻗﻒ ﺍﻟﻘﻮﻡ , ﻭﻗﻞ ﺑﻤﺎ ﻗﺎﻟﻮﺍ ، ﻭﻛﻒ ﻋﻤﺎ ﻛﻔﻮﺍ ، ﻭﺍﺳﻠﻚ ﺳﺒﻴﻞ ﺳﻠﻔﻚ ﺍﻟﺼﺎلح ، ﻓﺈﻧﻪ ﻳﺴﻌﻚ ﻣﺎ وسعهم )) شرح أصول إعتقاد أهل السنة
ኢማም አል አውዛኢ እንድህ አሉ፡―
((እራስህን በሱና ላይ አፅና ቀደመወቶች እቆሙበት ላይ ቁም እነሱ ያሉትን በል ከተቆጠቡት ተቆጠብ የቀደምቶችህን መንገድ ያዝ እነሱን የበቃ ይበቃሀል))
ሸርሁ ኡሱሊ ኢእቲቃዲ አልህሊ ሱነቲ ወልጀማአህ።
-----------

https://telegram.me/tewihd
360 views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 20:22:54 ፍትሃዊነት !

ኢብን ሐዝም አሏህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል:-

አንድን ሰው በሆነ ነጥብ ዙሪያ ተከራከርኩት። ንግግሩን ግልፅ ማድረግ ስለማይችልም (ምላሱን ስለሚይዘው) ክርክሩን አሸነፍኩት። የተዘጋጀው መድረክም በኔ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ወደ ቤት የተመለስኩ ግዜ ግን(በተከራከርንበት ነጥብ ዙሪያ) ነፍሴ ላይ ቅሬታ አደረብኝ እና ከፊል ኪታቦቼን ማገላበጥ ስጀምር ትክክለኛውን ምላሽ ማግኘት ቻልኩ። ኪታቦቹ ላይ ያገኘሁት ምላሽ የኔ ንግግር ስህተት መሆኑን እና የተከራካሪዬ ሃሳብ ትክክል እንደሆነ ነበር። ከእኔ ጋር ክርክሩን ከተጣዱት ባልደረቦቼ አንድ ሰው ነበር፤ ኪታቦቼን ስመለከት ያገኘሁትን ነገርኩትና ወደ ተከራከረኝ ሰው ጋር ሄጄ እርሱ ትክክል መሆኑን እኔ መሣሣቴን እና ወደ እርሱ ንግግር( አቋም) መመለሴን ማሳወቅ እፈልጋለሁ አልኩት። ባልደረባዬም ይህንን ለማድረግ ፍቃደኛ ሆንክ ? አለኝ
እኔም ፦ አዎ! በግዜው ይህን ማድረግ ቢቻለኝ ኖሮ እስከ ነገ አላቆየውም ነበር አልኩት።

ኢብን ሃዝም ይህን ታሪክ ከገለፀ በኋላ እንዲህ አለ፦
" እወቅ! ይህ አይነቱን ድርጊት መፈፀምህ እርሱን ሊፎካከረው ሚችል የሌለ በሆነው "ፍትሃዊነትን መጎናፀፍ" ጋር ውብ የሆነን ማስታወስ ያሸምትሃል ...

በእውነታው አንተ የተሸነፍክ ሆነህ ሳለ ፍላጎትህ አንተ አሸናፊ እንደሆንክ ማሳየት ወይም ካንተ ጋር ለሚጣዱ ባንተ ለሚታለሉና በውሳኔህ ለሚተማመኑት አሸናፊ መሆንክን ማሳየት አይሁን። ርካሽ ፣በጣም የወደቅክ ፣ ደካማ እና ግብ የሌለው ትሆናለህና።"

[ረሳዒል ኢብን ሃዝም 4/337].


https://telegram.me/tewihd
466 views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 10:39:41 ~#ዱኒያ ...
…………………
~ ዱኒያ ማለት ፈተና የበዛባት የውሸት አለም ነች!
ዛሬ ተደስተህ ነገ ታለቅሳለህ ....ዛሬ አግኝተህ ነገ ታጣለህ!
..........
....
ፈተናውን ሁሉ አልፌ ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሻለሁ ብለህ ኡፎይ
ስትልና የእረፍት ኑሮ መኖር ስትጀምር .... ....ድንገት ሳታስበው
የሰበሰብከው ሁሉ ይበተናል።
በሌላ በኩል ደግሞ .....
....... በቃ ከዚህ ብኋላ ሁሉንም ነገር አላገኘውም ብለህ ተስፋ
ቆርጠህ ስትቀመጥ ...ጀሊሉ ያላሰብከውን ነገር አምጥቶ
ይሰጥህና .....ጨለማ የሆነው ኑሮህ በብርሀን ይደምቅና
፣የቀዘቀዘው ቤትህ ይሞቅና በደስታ ያስፈነድቅሀል።
.......ብቻ ምን ልበልህ ዱኒያ ጤዛ ነች" ስታስከፋህም ሆነ
ስታስደስትህ አልሃምዱሊላህ ብለህ ለጌታህ ምስጋና አቅርብ።
~~ ለዚች ብልጭልጭ አለም ቅንጣት ታክል ሳትጨነቅ ፣ የነገ
የአኼራ ሂወትህ እንዳምርልህ ወደ ጌታህ አልቅስ!
..........ዱኒያ ጊዜያዊ መኖሪያ እንጂ ዘላለማዊ መኖሪያ
አይደለችም። ብዙ አትድከምላት፣ብዙ አታስብላት! ....ይልቅ
ለአኼራህ ድከም፣ለአኼራህ አስብ፣ለአኼራህ ተጨነቅ፣
ለአኼራህ ስራ"
…… እመነኝ!.......ጭንቀትህ ለዱኒያ ሳይሆን ለአኼራ መሆን
ሲጀምር የውስጥ ሰላምና መረጋጋት ታገኛለህ።
ያ አላህ ዱኒያ አኼራችንን አሳምርልን!

https://telegram.me/tewihd
481 views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 23:04:46 ማራኪ የቁረዓን ቲለዋ

ቀልብህ ውስጥ ያለውን በሽታ በአለም ላይ አሉ የሚባሉ ዶክተሮች እንዲያስወግዱልህ ብትሯሯ እንደ ቁርኣን ያለ ፈውስ በፍፁም አታገኝም
ሸይኽ ኡሰይሚን ረሒመሁላህ አል-ካፊያ አሻፊያህ(1/198)

https://telegram.me/tewihd
365 views20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 21:22:29 ውብ የሆነው የጌታችን ቃል ( ቁርዐን ) ባማረ ድምፅ ሲቀራ ምንኛ እንደሚያስደስት ተመልከቱ !
እስቲ ከቁርዐን ርቀው በነሺዳ ሱስ ለተተበተቡ እህት ወንድሞችም ይደርስ ዘንዳ #share አድርጉላቸው ፡፡

https://telegram.me/tewihd
374 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 11:41:57 ሸይኽ ፈውዛን እንድህ አሉ፦

【አሁን በኡማው ላይ ከባዱ አደጋ ፣ የነዛ አላዋቂ መሃይም የሆኑ ሰዎች ጥሪ ነው ፣ ሰዎችን በአላዋቂነት ፣ በጥመት ጥሪ ያደርጋሉ።】

ኢዓነቱል ሙስተፊድ (1/337)



ሙሀመድ አማን አል ጃሚ እንድህ ይላሉ፦

《 ቢዚህ ዘመን መቀላቀል ፣ መደባለቅ ፣ ተልቢስ ማድረግና ፣ ማጥመም ስለበዛ ፣ መማር ዒልምን መፈለግ በያንዳንዱ ሰው ላይ ግዴታ ነው።》

ሸርሁል ዋሲጢያ (276)
Telegram
https://telegram.me/tewihd
433 views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 09:04:30 ካነበብኩት...

ምንም ወንጀልህ ቢበዛ ከተውበት(ከንሰሀ)አትሽሽ፡፡
ነገሩ ልብስህ በቆሸሸ ቁጥር አይደለምን ልብስህን የምታጥብ!!
ልክ እንደዚሁ ወንጀልን በሠራህ ቁጥር ጌታህን ምህረት ጠይቅ፡፡

@tewihd
451 views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 09:02:59 በየ ሆስፒታሉ ያንተን አይነት ኑሮ መኖርን ሚመኝ ሞልቷል፡፡
በየእስርቤቱ ያንተን ነፃነት የሚናፍቅ ሞልቷል፡፡
በየ ማስጠለያው ያንተን አይነት ማረፊያ ፈላጊ ሞልቷል፡፡
በቀብር ላይ ያሉ ሁሉ ደግሞ ያንተን ክፍት ሰዓት ናፋቂዎች ናቸው ...

ስለዚህ ያንተ ህይወት(ኑሮ) ምንም እንኳን እንደ አንተ እይታ የተበላሸ ቢሆንም ብዙዎች ግን ያንተን አይነት ህይወት የሚመኙ ሞልተዋል፡፡!!

Copy from Arabic Twitter page.
418 views06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 08:33:14 الله المستعان وعليه التكلان
አስደንጋጭ በጣም አሳሳቢ ዜና


የስልክ ጥሪ መልህክት

ውድ ወንድማችን አቡ ፉረይሓን ከትላንትና ወዲያ ማለትም ቅዳሜ የሆነ ነገር አስነክተውት በንክ ቤት ሄዶ ብር አውጥቶ ለሆኑ ሰዎች ሲሰጥ ነበር አሉ ቤታሰቦቹ ባንክ ቤት ሲጠይቁ ቦሌ ባንክቤት ወደ ቴሌ ወድለው ጠይቀዋሉ ወደ ያለበት አቅጣጫ ተነግሮዋቸው ነበር ከዛ በኋለ ስልኩ አይሰራም እስከ አሁን ዝግ ነው
ወደ ሌላም ባንክ ቤት ሲጠይቁ በዚሁ ተመሳሳይ ነገር ነው የተነገራቸው እጁ እግሩ ሁላ የንቀጠቅጠው ነበር ኣሉ ስንት እንዳወጣ ና ከማን እንደነበረ ለማውራት ግን ኢንቢ ኣሉን አሉ
አላህ ይዘንለት ወንድማችን አቡ ፉረይሓን ለቤት አላህ በሰላም ያብቃው ብላችሁ ዱዓ አድርጉለት።
በያ ቦታው ሼር እና በማፋላለግ ቤተሰቦቹን ተባበሯቸው ያ! ጀማዓ

ወንድሙ አቡ ኡበይዳ አብራር አወል
387 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ