Get Mystery Box with random crypto!

~#ዱኒያ ... ………………… ~ ዱኒያ ማለት ፈተና የበዛባት የውሸት አለም ነች! ዛሬ ተደስተ | አስ–ሱናህ

~#ዱኒያ ...
…………………
~ ዱኒያ ማለት ፈተና የበዛባት የውሸት አለም ነች!
ዛሬ ተደስተህ ነገ ታለቅሳለህ ....ዛሬ አግኝተህ ነገ ታጣለህ!
..........
....
ፈተናውን ሁሉ አልፌ ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሻለሁ ብለህ ኡፎይ
ስትልና የእረፍት ኑሮ መኖር ስትጀምር .... ....ድንገት ሳታስበው
የሰበሰብከው ሁሉ ይበተናል።
በሌላ በኩል ደግሞ .....
....... በቃ ከዚህ ብኋላ ሁሉንም ነገር አላገኘውም ብለህ ተስፋ
ቆርጠህ ስትቀመጥ ...ጀሊሉ ያላሰብከውን ነገር አምጥቶ
ይሰጥህና .....ጨለማ የሆነው ኑሮህ በብርሀን ይደምቅና
፣የቀዘቀዘው ቤትህ ይሞቅና በደስታ ያስፈነድቅሀል።
.......ብቻ ምን ልበልህ ዱኒያ ጤዛ ነች" ስታስከፋህም ሆነ
ስታስደስትህ አልሃምዱሊላህ ብለህ ለጌታህ ምስጋና አቅርብ።
~~ ለዚች ብልጭልጭ አለም ቅንጣት ታክል ሳትጨነቅ ፣ የነገ
የአኼራ ሂወትህ እንዳምርልህ ወደ ጌታህ አልቅስ!
..........ዱኒያ ጊዜያዊ መኖሪያ እንጂ ዘላለማዊ መኖሪያ
አይደለችም። ብዙ አትድከምላት፣ብዙ አታስብላት! ....ይልቅ
ለአኼራህ ድከም፣ለአኼራህ አስብ፣ለአኼራህ ተጨነቅ፣
ለአኼራህ ስራ"
…… እመነኝ!.......ጭንቀትህ ለዱኒያ ሳይሆን ለአኼራ መሆን
ሲጀምር የውስጥ ሰላምና መረጋጋት ታገኛለህ።
ያ አላህ ዱኒያ አኼራችንን አሳምርልን!

https://telegram.me/tewihd